ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሪፖርቱ ኢህአዴግ ምርጫውን ለማሸነፍ መልካም እድል መኖሩን ጠቅሷል። ኢህአዴግ መንግስት መሆኑና የመንግስትን ንበረቶችና ጽህፈት ቤቶች መጠቀሙ እንዲሁም በቅስቀሳ ወቅት አንድ ለአምስት በሚል አሠራር በተጠቀመበት የቅስቀሳና የማሳመን አሠራር በርካታ ድምፆችን ለመውሰድ የሚያስችል እድል መፍጠሩን በ2002 ቱ ምርጫ ወቅት መታየቱን አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሚኒስትሮች ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል። በቅድመ ውጤት ትንበያው ኢህአዴግ በከፍተኛ ድምጽ ...
Read More »ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ፕሬሱን ማዳከሙን ቀጥሏል
ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ነጻ ፕሬሱን በማዋከብ፣ በማሳደድ፣ በማሰር ከሚያደርገው ቀጥተኛ ጥቃት በተጨማሪ ስልታዊ ጥቃትን በተጠናከረ መልኩ ስራ ላይ እያዋለ ነው። በነገው ዕለት የሚከበረው የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጵያ ታስቦ የሚውለው የፕሬሱ ስልታዊ አፈና በተጠናከረበት ወቅት መሆኑም ያነጋገርናቸው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ምንም ዓይነት ትችትና የተለየ አስተያየት ለመስማት ዝግጁ ያልሆነው የኢህአዴግ ...
Read More »የመንግስት ኮሚኒኬሽን ምክር ቤት የኢሳትን የመረጃ ጥንካሬ ገመገመ
ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የኮምኒኬሽን ምክር ቤት የኢሳት አባሎችን እና ቁልፍ የግንቦት ሰባት አመራሮችን የግል ላፕቶፓቸውን እና ለመረጃ መሰብሰብ የሚጠቀሙባቸውን ስልኮች ለማግኘት የሚያስችል እቅድ ማውጣቱ ታውቋል። በግምገማው ወቅት ኢሳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መሆኑ ተገልጿል። ኢሳት በመንግስት ላይ እየሰነዘረ ያለው ጥቃት ጉልህ ለውጥ የማምጣት አቅም ፈጥሯል ሲል በውይይቱን ላይ ተነስቷል፡ ...
Read More »በሀድያ ዞን አምቡላንሶች ለምርጫ ቅስቀሳ እየዋሉ በመሆኑ ህመምተኞች በተለይም ነፍሰ ጡር እናቶች ህክምና ሳያገኙ ለሞት እንደሚዳረጉ ነገረ ኢትዮጵያ ዘገበ።
ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዝያ 20/2007 ዓ.ም አንዲት ምጥ የተያዙ እናት በአቅራቢያቸው በሚገኝ የጎምበራ የጤና ጣቢያ በሄዱበት ወቅት ‹‹ከአቅማችን በላይ ነው!›› ተብለው ወደ ሆሳና ሪፈራል ሆስፒታል ሄደው እንዲታከሙ ሪፈር ቢጻፍላቸውም በትራንስፖርት ችግር ነፍሳቸው ማለፉን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ ለጎምበራ ጤና ጣቢያ የተመደበችው አምቡላንስ በጎምበራ ወረዳ ኦሌ ቀበሌ ለገዥው ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በመውጣቷ ቤተሰብ ነፍሰጡሯን ከጎምበራ ጤና ጣቢያ ...
Read More »የኢትዮጵያ ቤተእስራኤላውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቤተእስራኤላዊያኑ የተቃውሞውን ሰልፍ ያደረጉት ደማስ ፈቃደ የተባለ ቤተእስራኤላዊ ወታደር በፖሊሶች መደብደቡን ተከትሎ ነው። አንድ ፖሊስ ወታደር ደማስን መደብደቡን የሚያሳይ በሚስጢር የተቀረጸ ቪዲዮበማህበራዊ ሚዲያዎች ይፋ ከሆነ በሁዋላ ፣ ቤተ እስራኤላውያኑ ቁጫቸውን በአደባባይ ገልጸዋል። ሰልፈኞቹ ከፖሊስ ጋር ግጭት ፈጥረው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን የፈጸመውን ፖሊስ ከስራ አግዶ ክስ ሊመሰርትበት መሆኑ ...
Read More »18 የቃሊቲ ጠባቂ ፖሊሶች ተባረሩ
ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ፣ የማረሚያ ቤቱ ሹሞች ፖሊሶችን ለአስቸኳይ ስብሰባ እንደሚፈልጓቸው ከገለጹላቸው በሁዋላ፣ በስብሰባው ላይ የተገኙትን ፖሊሶች የሞባይል ስልኮች ተቀብለው ፍተሻ አድርገዋል። በፍተሻው ወቅት 18 ፖሊሶች ከኢንተርኔት የተለያዩ ፎቶዎች፣ ጽሁፎችንና ቀስቃሽ ዘፈኖችን በማውረድ በስልኮቻቸው ላይ አስቀምጠው የተገኘ ሲሆን፣ ፖሊሶቹም ወዲያዉኑ እንዲባረሩ ተደርጓል። በተለይ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፎቶ ግራፍ በተገኘባቸው ፖሊሶች ላይ ...
Read More »በስደት በችግር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን መፍትሄ እንዲሰጣቸው የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ በጀኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፊት ለፊት ባደረጉት ሰልፍ በሊቢያና የመን በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ጥያቄያቸውን በተወካዮች አማካኝነት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣኖች ያቀረቡ ሲሆን፣ የፖለቲካ ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአፋጣኝ ወደ ሶስተኛ አገር እንዲሸጋገሩ፣ ሌሎችም እንዲሁ አሁን ካሉበት አገር ወጥተው በሶስተኛ አገር ቆይታ አድርገው ምርጫቸው እንዲጠበቅላቸው ጠይቀዋል።
Read More »በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ከምርጫው በፊት ውሳኔ አያገኙም ተባለ
ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደህንነት ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚያዚያ 30 ፣ 2007 ዓም ከፍተኛው ፍርድ ቤት በእነ አቶ አቡበክር አህመድ በተከሰሱት ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት በተሰጠትእዛዝ፣ ውሳኔው ከምርጫው በፊት አይሰጥም። ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የተባሉት የደህንነት ባለስልጣን ይህንኑ አቋም በቅርቡ ተደርጎ በነበረው የኢህአዴግ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። ውሳኔው በተያዘለት ቀን እንዳይሰጥ ...
Read More »ከ3 ሺ 500 በላይ ሜዳ ላይ የወደቁ አባወራዎች መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም
ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አለም ባንክ አካባቢ የሚገኙ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ3 ሺ በላይ አባወራዎች ያለፉትን 11 ወራት በስቃይ ቢያሳልፉም ፣ እስካሁን መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም። የመንግስት ባለስልጣናት ከዚህ ጊዜ በሁዋላ ለምርጫ ቅስቀሳ መምጣታቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ያሉበት ህይወት ከሞቱት በታች መሆኑን በምሬት ገልጸዋል። ቤታቸው ከፈረሰባቸው መካከል ከ5 ያላነሱ ሰዎች በጅብ ...
Read More »የመተማ ነዋሪዎች በመዋጮ መማረራቸውን ገለጹ
ሚያዝያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተማ ዮሃንስ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች እና የከተማዋ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ አመራሮች የመሳሪያ ፈቃድ የሚያወጡትን ነዋሪዎች፣ ለመሳሪያ ፈቃድ 260 ብር ፣ ለግዳጅ ቦንድ ግዢ 1 ሺህ ብር እንዲሁም ለቀበሌ መታወቂያ 300 ብር በማስከፈል ላይ መሆናቸውን ህዝቡን ምሬት ላይ ጥሎታል። በሱዳኗ የጠረፍ ገበያ ማዕከል በሆነችው የገላባት ቀበሌ በሱቅ እና ምግብ ቤቶች ...
Read More »