ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ሲታኮሱ መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አንድ ሻለቃ ጦር እና የፌደራል አባላት ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ በወሰዱት እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች አደጋ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ።
ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር በሚያደርገው ቀጣይ ትግል ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲቆምም ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል። የፓርቲው አመራሮች “‹‹ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!›› በሚል ርእስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምርጫው ሂደት በመቆየታቸው የኢህአዴግን አውሬነት ማሳየታቸውን በመጥቀስ፤ ‹‹በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስት በህዝብ ተቀባይነት የለውም››ብለዋል። ‹‹ምርጫው ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ...
Read More »የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በያዝነው 2007 በጀት ዓመት 10 ወራት ከኤሌክትሪክ ኃይል ኤክስፖርትና ከሀገር ውስጥ ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ፡፡
ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባና በክልሎች የኤሌክትሪክ ኃይል በየዕለቱ እየተቆራረጠ ምርታማነት ባሽቆለቆለበት በዚህ ወቅት ሚኒስቴሩ ለጎረቤት ሀገራት ባለፉት 10 ወራት ብቻ 606 ነጥብ 5 ሚሊየን ኪ.ዋ. የኤሌክትሪክ ኢነርጂ በመሸጥ ዳጎስ ያለ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡ በሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር ከጊዜ ወደጊዜ ተባበሶ በቀን በአማካይ አንድ ጊዜ የሚጠፋበትና ምርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መደበኛ ...
Read More »ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው የአንድ ሳምንት ጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባት፡፡
ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቄራ ምድብ ችሎት የቀረበችው ወ/ሮ ንግስት፣ መንግስት በሊቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ በአይ.ኤስ.አይ.ኤስ የሽብር ቡድን የተፈጸመውን የሽብር ድርጊት ለማውገዝ ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና ሰላማዊ ሰልፍን በማወክ›› ተጠርጥራ እንደታሰረች ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ፍርድ ቤት ...
Read More »በምርጫ ቦርድ ውጤት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል
ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ የግንቦት15ቱን ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉ ከተገለጸ በሁዋላ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል። ምንጮች እንደገለጹት በርካታ ፊደል ቀመስ አባሎቹ ኢህአዴግ አሸነፍኩ ያለበትን የድምጽ ልዩነት አልተቀበሉትም። ውጤቱን የሚቃወሙ የግንባሩ አባላት ” ህዝቡ ከእንግዲህ በሰላም መንግስት እቀይራለሁ የሚለው እምነቱ ተሟጦ የሃይል አማራጭን ብቻ እንዲመለከት ከማድረጉም በላይ፣ የሃይል አማራጭን የሚከተሉ ሃይሎች በህዝቡም ሆነ በአለማቀፉ ማህበረሰብም የተሻለ ...
Read More »የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ለመሆን ሲወዳደሩ ከነበሩት እጩዎች መካከል የኢትዮጵያው የገንዘብ ሚኒስትር ሶፊያን አሕመድ ተሰናበቱ።
ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ አዲስ ስታንዳርድ ዘገባ እየተካሄደ ባለው ዓመታዊው የባንኩ የቦርድ ስብሰባ ላይ ነው ለፕሬዚዳንትነቱ ሲወዳደሩ ከነበሩት ስምንት ዕጩዎች መካከል የገንዘብ ሚኒስትሩ ሶፊያን አህመድ የሴራውሊዮኗን ሳሞራ ሚሸል ካማራን ተከትለው ሁለተኛው ተሰናባች ሆነዋል። ቦርዱ እንደ አውሮፓያኑ አቆጣጠር ባለፈው ፌብሩዋሪ 11 ቀን አቢጃን በሚገኘው የባንኩ ዋና ጽህፈት ቤት ባደረገው ስብሰባ ባንኩን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትርን ...
Read More »አለም አቀፍ ስደተኞች ተቋም ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደአገራቸዉ አጓጓዘ
ኢሳት ዜና ግንቦት 18 2007 በየመን መዉጫ አጥተዉ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን መካከል በጦርነት ጉዳት የደረሰባቸዉን ጨምሮ ከሁለት እሺ በላይ ሰደተኞችን ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ማጓጓዙን አለም አቀፉ የስደተኞች ተቋም ገለጠ። ድርጅቱ የሳዉዲ አረቢያ፥ ሱዳንና፥ ጂቡቲን የድንበር ግዛት በመጠቀም ስደተኞቹን ወደአገራቸዉ መመለስ መቻሉን አስታዉቋል። በየመን መዉጫን አጥተዉ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መንግስት ዜጎችን ለመታደግ በቂ ጥረት አላደረገም ሲሉ ቅሬታቸዉን ሲገልጹ መቆየታቸዉ ይታወሳል። የኢትዮጵያዉያኑን ...
Read More »በሃመር ወረዳ የሚገኙ አርብቶ አደሮች “ድምጻችን ተዘረፈ” በሚል ተቃውሞ አስነሱ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመታ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ከሰኞ ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር መጋጨታቸው ታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ነዋሪዎቹ በምርጫው ማግስት የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲጀመሩ በጸጥታ ሃይሎች የተከለከሉ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ አርብቶአደሩ በወሰደው እርምጃ 3 ፖሊሶች ቆስለዋል። ...
Read More »ወ/ሮ ንግስት ወንድይፍራው ታሰረች
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወ/ሮ ንግስት በደቡብ ክልል የምርጫ ቅስቀሳ አድርጋ ስትመለስ መታሰሩዋን ባለቤቱዋ ለኢሳት የገለጸ ሲሆን፣ የ3 አመት ህጻን ልጇም አብራ ከታሰረች በሁዋላ እንደመለሱለት አክሏል። ለምርጫ ቅስቀሳ ወጥተው የነበሩ ብዙ ወጣቶች እየተፈለጉ መሆኑን መረጃው እንደደረሳትና እርሱዋም እንደምትታሰር አውቃ ወደ አዲስ አበባ መመለሱዋን ባለቤቱ ገልጿል። በአዲስ አበባ አይ ኤስ ኤስ የጠባለው አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚገኙ ...
Read More »የዞን 9 ጸሃፊዎች በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ...
Read More »