ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ ሰበብ አስባቦች የሚጣልብን ቅጣትና እገዳ ተገቢ አይደለም በሚል ሰኔ 8፣ 2007 ዓም ለአንድ ቀን የስራ ማቆም አድማ አድርገው የነበሩት የሰሜን ጎንደር ዞን ሾፌሮች፣ ፣ ከአድማው በሁዋላ ችግራቸውን የሚሰማ እና መፍትሄ የሚሰጥ አካል ይኖራል ብለው ሲጠብቁ፣ በተቃራኒው ከስራ መታገዳቸውን ተናግረዋል። ሾፌሮች እና ባለሃብቶች እንደሚናገሩት “የመንግስትን ትእዛዝ አላከበራችሁም ፣ የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊዎች ...
Read More »በቴፒ የወረዳው አዛዥና ፖሊሶች ታሰሩ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ለመብት የሚታገሉ የከተማዋ ወጣቶች በአንድ የፖሊስ ጣቢያ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና የጸረ ሽብር ግበረሃይል አባላት በከተማዋ ተገኝተው እጃቸው አለበት ብለው የጠረጠሩዋቸውን የቴፒ ወረዳ አስተዳዳሪን ጨምሮ 7 ፖሊሶችን ይዘው አስረዋል። ባለስልጣኖቹ የከተማውን ህዝብ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ህዝቡ በነጻነት እጦት እየተሰቃየ መሆኑንና ወጣቶች እርምጃ የሚወስዱት ከዚህ ተነስተው መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በአካባቢው የሚታየውን ...
Read More »በርካታ ቁጥር ያላቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ነው
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንት በፊት አልሸባብ የተባለው የሶማሊያ ታጣቂ ሃይል በቡርካባ ግዛት ጃሚዮ በሚባል ቦታ ላይ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ከ30 በላይ ወታደሮችን ከገደለ በሁዋላ፣ በርካታ ቁስለኞች ሞቃዲሹ በሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ቁጥር ሁለት ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው። አሚሶም በመባል የሚታወቀው በሶማሊያ የሰፈረው የአፍሪካ ህብረት ጦር በአልሸባብ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዟል። የአፍሪካ ህብረት ...
Read More »በጋምቤላ የመሬት ኪራይ እዳ ካልከፈሉ 150 ባለሀብቶች መካከል እጅግ አብዛኞቹ የትግራይ ብሄር ተወላጆች መሆናቸውን አንድ ሰነድ ጠቆመ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጋምቤላ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት በጋምቤላ እርሻ ስራ ተሰማርተው የሚፈለግባቸውን የመሬት ኪራይ እዳ ባልከፈሉ 150 ባለሀብቶች ላይ ያወጣው የማሳሰቢያ ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፤ የጋምቤላን መሬት የተቀራመቱት ከ90 በመቶ የሚልቁት የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ባለሀብቶቹ ከ2006 እስከ 2007 ሰኔ ወር ድረስ ያለባቸውን ውዝፍ እዳ አጠቃለው እንዲከፍሉ በወጣው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ላይ ስማቸው በዝርዝር ተቀምጧል። ...
Read More »የአዲስ አበባ ፖሊስ አባሎቹን እየገመገመ ነው
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ አንድ ተጀምሮ ሰኔ 20 የሚጠናቀቀው ግምገማ ከፍተኛ አመራሮችን፤አዛዦችን እንዲሁም ተራ የፖሊስ አባሎችን አካቷል። ከጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የግምገማው ይዘት በፖሊስ ስነምግባር ዙሪያ ነው። በግምገማው ወቅት አንድ ባለ ሳጅን ማዕረግ ያለውና አንድ ኮንስታብል ፖሊስ በስልካቸው ውስጥ የግንቦት ሰባት፤የሰማያዊ ፓርቲና የሌሎች ተዛማጅ ድርጅቶች መረጃዎች በስልካቸው ውስጥ ተገኝቷል በሚል ተይዘው ወደ ማዕከላዊ ...
Read More »በባህር ዳር ከተማ ለመኖሪያ ቤት ባለ ይዞታዎች ተሰጥቶ የነበረው የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ተመልሶ ተሰበሰበ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምርጫ 2007 ቅስቀሳን ተንተርሶ በህዝቡ ዘንድ የሚቀርቡትን ጥያቄዎች ለመመለስ በሚል ሲንቀሳቀስ የነበረው ኢህአዴግ፤ በከተማዋ በልዩ ልዩ ክፍለ ከተሞች ለረዢም አመታት ለኖሩ የይዞታ ባለመብቶች ከምርጫው በፊት ሰጥቶት የነበረውን በባለ ቀለም የብአዴን አርማና የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ ያሸበረቀ የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ መልሶ በመውሰድ ውሳኔውን ለመሻር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡ ኢህአዴግ “በየክፍለ ከተማው ከ380 በላይ አባወራዎችን የይዞታ ...
Read More »አንድ የአረና ፓርቲ አባል ተገደሉ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአረና ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው አምዶም ገብረስላሴ በፌስ ቡክ ገጹ እንደጻፈው ፣ የ48 አመቱ አቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገድለዋል። አቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ...
Read More »በደብረማርቆስ የሰማያዊ እጩ ተወዳዳሪ ተገደለ
ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃያዎቹ መጨረሻ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ጸሃፊ ሳሙኤል አወቀ ሰኔ 8/2007 ዓም ምሽት ላይ ሁለት ግለሰቦች ወደ ቤቱ ሲገባ ጠብቀው በፈጸሙበት ድብደባ ህይወቱ አልፎአል። የሳሙኤል ጓደኞችና የስራ ባልደረቦች ድርጊቱን የመንግስት ሃይሎች እንደፈጸሙት ምንም ጥርጣሬ እንደሌላቸው ተናግረዋል። ሳሙኤል ጀግና እና ለአገሩ የሚቆረቆር ጠንካራ ወጣት ነበር የሚሉት ጓደኞቹና የትግል ...
Read More »አንድ የፌደራል ፖሊስ 3 ባልደረቦቹንና አንድ ቻይናዊ ገደለ
ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትውልድ ቦታው አሶሳ አከባቢ የሆነ የፌዴራል ፖሊስ አባል ሌሎች ሶስት የፌዴራል ፖሊስ አባላትን እና አንድ ቻይናዊን በምዕራብ ሀረርጌ ሚኤሶ ወረዳ ልዩ ስሙ ቦርደዴ በተባለ ቦታ በጥይት ተኩሶ ከገደላቸዉ በሃላ መሰወሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል:: የፌደራል ፖሊሶችና የኦሮምያ ፖሊስ ገዳዩን ለመያዝ በጭሮ፣ ሚኤሶ፣ በዴሳ፣ ገለምሶና አዋሽ ከተሞች ቤት ለቤት እየገቡ ፍተሻ በማካሄድ ላይ ናቸው። ...
Read More »በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ የዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ አደራጅ በድብደባ ሆስፒታል ገባ
ሰኔ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጊምቦ ገዋታና በቦንጋ የተራዘመው ምርጫ ባለፈው ሳምንት ከተጠናቀቀ በሁዋላ፣ የግል ተወዳዳሪው ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የምርጫ ቀስቃሽና አደራጅ የሆነው ምትኩ ወልዴ ፣ ትናንት ከቀኑ 6 ሰአት ከ 30 ደቂቃ ላይ ፖሊሶች ከቤት አውጥተው የደበደቡት ሲሆን፣ ግለሰቡ በደረሰበት ከፍተኛ ድብደባ ቦንጋ ሆስታል ከገባ በሁዋላ፣ ወደ ጅማ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል። ግለሰቡ የደረሰበት ድበደባ ከፍተኛ በመሆኑ ...
Read More »