ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተቃውሞው ሰልፍ መንስኤ ከገንዘብ ምንዛሬ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰአት ተኩል ላይ በተፈጠረው ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች ተደብድበው ሆስፒታል ገብተዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች በነጋዴዎች በኩል የሚልኩትን ገንዘብ ለማስቀረት ከፌደራል የመጡ ፖሊሶች እርምጃ መውሰዳቸው፣ ለተቃውሞ ሰልፉ መነሻ ምክንያት መሆኑን የሚናገሩት የአካባቢው ተወላጆች፣ ነዋሪዎቹ ነጋዴዎቹ ካልተፈቱ ተቃውሞአችንን አናቆምም ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በርካታ የአዲስ አበባ የወረዳ አመራሮቹን ሊቀንስ ነው
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢህአዴግ የድርጅት አባለት ግምገማ መጠናቀቁን ተከትሎ የግምገማ ውጤት እየወጣ ሲሆን፣ በዚህም ግምገማ መሰረት በርካታ የከተማዋ ወረዳ አመራሮች ከሃላፊነታቸው እንደሚነሱ ታውቋል። በጉለሌ ክ/ከተማ ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ከ50 በላይ አመራሮች ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ከ20 በላይ የወረዳ አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ክ/ከተሞች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ተገምግመው እጅግ ዝቅተኛ ...
Read More »የፎገራ አካባቢ ሩዝ አምራች አርሶአደሮች ስጋት ላይ ናቸው
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሩዝ በማምረት የሚታወቀው የፎገራ መስክ ለሸንኮራ አገዳ ተክል ሊውል ነው መባሉን ተከትሎ ፣ ሩዝ በማምረት ኑሮአቸውን የሚገፉ አርሶአሮች ስጋት ላይ ወድቀዋል። በጣና ሃይቅ ዳር የሚገኘው ሰፊው የፎገራ ረግራጋማ ሜዳ ከማዳበሪያ ነጻ ሆነ ሩዝ በማምረት የሚታወቅ ቢሆንም፣ ገዢው ፓርቲ በአገሪቱ የሚታየውን የስኳር እጥረት ለመፍታት በሚል ሰበብ አርሶአደሮችን በማፈናቀል ቦታውን ለሸንኮራ አገዳ ተከል ...
Read More »ለዲያስፖራው የሚሰጠው ትኩረት አገር ቤት ባለው ህዝብ ላይ ቅሬታ እየፈጠረ ነው
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ መንግስት በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለመያዝ በሚል ስሌት የሚሰጠው የቤት መስሪያ ቦታ፣ ተመሳሳይ ጥያቄ ላቀረቡ ፣ በአገር ውሰጥ ለሚኖሩ ዜጎች ባለመስጠቱ፣ ቅሬታ እየተፈጠረ መሆኑን ዘጋቢአችን ገልጿል። መንግስት የዲያስፖራ ቀን ለማክበር በሚል ሰሞኑን በክልሎችና በአዲስ አበባ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በተነሱት ውይይቶች ላይ ይህ የቅሬታ ስሜት መንጸባረቁን ገልጿል። የኦሮምያ ክልል ...
Read More »የዝናብ መዛባቱ ቀጣይ ነው ተባለ
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ኤልኒኖ ከግንቦት ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ በመከሰቱ በኢትዮጵያ በአብዛኛዎቹ አካባቢዎች የዝናብ ስርጭት መዛባት መከሰቱን፣ ከዚሁ ችግር ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሁለት ወራትም የዝናብ መዛባቱ እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል። የኤጀንሲው ሃላፊዎች ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በግንቦትና በሰኔ ወራት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተሻለ ዝናብ የነበረ ቢሆንም በሐምሌ ወር የክረምት ዝናብ ሰጪ ክስተቶች ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በእያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀባቸው
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ ተጠይቆባቸዋል፡፡ አመራሮቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ በሽብርተኝነት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ፖሊስ ‹‹ለግንቦት 7 አባላትን እየመለመሉ ይልካሉ፣ኤርትራ ድረስ ሄደው ስልጠና ወስደዋል፡፡›› የሚል ክስ አቅርቦባቸው የነበር ቢሆንም ለክሱ ምንም ...
Read More »በስዊዘርላንድ በርን የሚኖሩ የኢሳት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሳካ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ሰራ
ነኅሴ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በተካሄደው አፍሪካ ፎረም ፌስቲቫል ላይ የተገኘው አስተባባሪ ኮሚቴ፣ ከምግብ፣ ከቡና፣ ከመጠጥ ሽያጭና ከተለያዩ ገቢዎች ያገኘውን ገንዘብ በኢሳት አካውንት ማስገባቱን ገልጿል። በእለቱ የኢሳት አላማ ለውጭ አገር ዜጎች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ፣ ለኢሳት በቋሚነት ድጋፍ የሚያደርጉ አባላትንም መዝግቧል። በምግብ ዝግጅት ሴቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረጋቸውን የገለጸው አስተባበሪ ኮሚቴው፣ በተለይ አገሪቱን ባህል ለውጭ አገር ...
Read More »በምእራብ ሸዋ ባለስልጣናት ” የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችው ለቃችሁ ውጡ ” የተባሉት የአማራ ተወላጆች አደጋ ውስጥ ናቸው
ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ አሎ ቀበሌ የሚገኙ ባለስልጣናት እና የጸጥታ ሃላፊዎች ‘ እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጆች ሳትሆኑ ሀብት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጆች ግን ከናንተ ያነሰ ገቢ ነው ያላቸው…ይህን ገቢ ያገኛችሁት በኛ መሬት ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ’ በማለት ቤታቸውን በማቃጠልና ንብረታቸውን በመንጠቅ ያፈናቀሉዋቸው የአማራ ተወላጆች በከፍተኛ ችግር ...
Read More »የኢህአዴግ መንግስት በድርቅ ለተጎዱት ወገኖች የእርዳታ ጥሪ አቀረበ
ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚታተመው ሳምንታዊ የሰብአዊ እርዳታ መጽሄት እንደዘገበው መንግስት በአገሪቱ ውስጥ የታየውን የምግብ እጥረት ለመቅረፍ ለጋሽ አጋራት አስቸኳይ እርዳታ እንዲለግሱ ጥሪ አቅርቧል። ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ ሊፈጠርባቸው ይችላል ተብሎ ለተሰጋባቸው ቦታዎች መንግስት 700 ሚሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል። ዞን 3 በሚባለው የአፋር አካባቢ እንዲሁም ስቲ ዞን በሚባለው የሶማሊያ ክልል አስቸኳይ የምግብ ...
Read More »የፖለቲካ እስረኞች ፍትሕ ሳያገኙ በቀጥሮ እየተንገላቱ ነው
ነኅሴ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አይ ኤስ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን አሰቃቂ ግድያ ለመቃወም መንግስት በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት እነ ማቲያስ መኩሪያ፣ ፖሊስ በጊዜ ቀጠሮ ወቅት ‹‹የቪዲዮ ማስረጃም አለን›› በማለቱና ተከሳሾቹ ‹‹ቪዲዮው ይቅረብልን፣ የቪዲዮ ማስረጃው ለእኛም የመከላከያ ምስክርነት ይጠቅመናል›› ብለው በመጠየቃቸው፣ ፍርድ ቤቱ የቪዲዮ ማስረጃው መቅረብ እንዳለበትና እንደሌለበት ብይን ለመስጠጥ ለዛሬ ነሃሴ 5 ቀን ...
Read More »