ፍርድ ቤቱ ለሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የሰጠው የዋስትና መብት በፖሊስ ታገደ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው ነሃሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም. እያንዳንዳቸው በ15 ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ተጠይቀው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ፣ ዋስትናቸው በአቃቤ ህግና በፖሊስ መታገዱን የፓርቲው የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በአመራሮቹ ላይ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ነሃሴ ...

Read More »

በመጪው አመት ከፍተኛ የምግብ እጥረት ሊከሰት ይችላል ተባለ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአለም ላይ የሚታየውን የአየር መዛባት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም እንደሚችል የአሜሪካ እና የእንግሊዝ መንግስታት እየገለጹ ነው። በምግብ እጥረቱ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራትና ሌሎች ድሃ አገሮች ክፉኛ ሊጎዱ ይችላል ብለዋል። ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረው የምግብ እጥረት በባሰ ሁኔታ በያዝነውና በመጪው አመት ሊከሰት እንደሚችል ያስጠነቀቁት መንግስታቱ፣ የምግብ እጥረቱ ግጭቶችን ሊያባብስ እንደሚችል ...

Read More »

የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ስደት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተነገረ

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 8, 2007) ከኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ወጣት ከሀገር በመሰደድ ላይ መሆኑ ስጋት እንዳሳደረበት መንግስት አስታወቀ። የወጣቶቹን ስደት ለመቆጣጠር ጠንካራ የተባሉ ደንቦችና መመሪያዎች ተግባራዊ ቢያደርጉም፣  ከዚህም በፊት ስደት በማይታወቅባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ቁጥሩ ከፍተኛ ወጣት በመሰደድ ላይ እንደሚገኝ በመንግስት የተቋቋመው የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። በድንበር በኩል ከሚደረጉ ስደተኞች በተጨማሪ በቱሪስት ቪዛ እየተሰደዱ ያሉ ...

Read More »

ኢትዮጵያ በኑሮ ደረጃ ስሌት ከ38 የአፍሪካ አገሮች 32ኛ ደረጃ ያዘች

ኢትዮጵያ በኑሮ ደረጃ ስሌት ከ38 የአፍሪካ አገሮች 32ኛ ደረጃ ያዘች ኢሳት ዜና (ነሓሴ 7, 2007) ከአፍሪካ የተሻለ የማህበራዊና የኢኮኖሚ አገልግሎት እንዲሁም የዜጎች አጠቃላይ የኑሮ ደረጃቸው በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ተብለው ከተቀመጡት 38 የአህጉሪቱ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ በ32ኛ ደረጃ ላይ መገኘቷን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ ባደረገው አመታዊ ረፖርት ገለጸ። ሃገሪቱ ለዜጎቻቸው የሚያቀርቡት የጤና፣ የትምህርት፣ ኢኮኖሚያዊና፣ የማህበራዊ አገልግሎቶች በመስፈርትነት በተወሰዱበት በዚሁ ...

Read More »

በደቡብ ወሎ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰዎች ተገደሉ

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ፣ ነሃሴ 7 ፣ 2007 እኩለ ቀን ላይ በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ፣ ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ እስካሁን ባለው መረጃ 2 ሰዎች ሲገደሉ፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች ቆስለዋል። ረብሻው እስከ አመሻሽ ቀጥሎ ከደሴ የተነሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ አካባቢው ደርሰው ጥበቃ እያደረጉ ነው። በተቃውሞ ሰልፉ ላይ ሁለት ፖሊሶች ...

Read More »

በሆሳዕና የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ታሰሩ

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከገንዘብ ዝውውር ጋር በተያያዘ ትናንት ነሃሴ 6፣ 2007 ዓም በሃድያ ዞን በሆሳእና ከተማ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ክፉኛ ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ደግሞ መታሰራቸውን የአይን እማኖች ገልጸዋል። በርካታ ወጣቶች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መደብደባቸውን የሚገልጹት ነዋሪዎች፣ ሆስፒታል የተኙት አመሻሹ ላይ ወደ እስር ቤት በፖሊሶች ተደግፈው መወሰዳቸውን ማየታቸውን ገልጸዋል። ...

Read More »

የዲያስፖራ በዓል በታላቅ ፌሽታ ተጀመረ

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰበት የዲስፖራ ክብረበዓል ትላንት በአዲስአበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በታላቅ ፌሽታ ተጀምሯል፡፡ ዝግጅቱ በተለያዩ ክንውኖች ለተከታታይ አምስት ቀናት ይቆያል ተብሎአል፡፡ ዲያስፖራ በልማት ለማሳተፍ በሚል ሽፋን የዲስፖራውን ህብረተሰብ ለመያዝ እንዲመች ታስቦ በተዘጋጀው በዚህ በዓል ላይ በግምት 2ሺ ገደማ የዲያስፖራ አባላትና በሀገር ውስጥ ስራ የጀመሩ የዲያስፖራ ባለሃብቶች የተገኙ ...

Read More »

በጋሞጎፋ ዞን ድርቅና የማዳበሪያ እዳ ገበሬውን ለስቃይ እየዳረገው ነው ተባለ

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን ከዝናብ እጥረት ጋር በተያያዘ በተነሳው ድርቅ በርካታ ገበሬዎች ለችግር የታገለጡ ሲሆን፣ ይህም ሳያንስ የዞኑ ካድሬዎች አርሶአዳሪው ህዝብ ማዳበሪያ በብድር በግድ እንዲወስድ እያስገገደዱት መሆኑ ችግሩን አባብሶታል። የዝናብ መጠኑ መዋዠቅ ገብሬውን በስጋት ላይ የጣለው መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ዝናብ ጭራሽ በመጥፋቱ አርሶአደሩ ለችግር ተጋልጦ የእርዳታ ...

Read More »

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የጦርነት ቀጠና ወደሆነችው የመን መፍለሳቸውን አላቋረጡም

ነኅሴ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች ለሕገወጥ አሸጋጋሪዎች የሚከፍሉት ከ150 እስከ 200 ዶላር ስለሌላቸው፣ ከ600 ኪሎሜትር በላይ ለሁለት ሳምንታት አንዲት የፕላስቲክ ኮዳ ውሃ ብቻ ይዘው በእግራቸው ድንበር አቋርጠው በፑትላንድ ራስገዝ የቦሳሶ የወደብ ዳርቻዎች ይደርሳሉ። የመን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አደገኛ በመሆኑ በሌሎች ሕገወጥ አጋቾች እጅ የሚወድቁት ስደተኞች፣ ለአጋቾች የሚከፍሉት ገንዘብ የሌላቸው የአካል ጉዳቶች፣መደፈርና ኢሰብዓዊ ድርጊቶች እንደተፈፀሙባቸው ...

Read More »

የህወሃት አመራሮች በዲሲ ከደጋፊዎች ጋር  ውይይት አደረጉ

ኢሳት ዜና (ነሐሴ 7, 2007 ዓም) በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት መቋጫ እንዳላገኘ በሚገለጽበት በአሁኑ ወቅት የህወሃት አመራሮች በዋሽንግተን ዲሲ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያይተዋል። ባለፈው እሁድ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ በሚል በተደረገው ጥሪ መሰረት ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተካሄደው ስብሰባ የመሩት ከኢትዮጵያ የመጡት ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማሪያምና አቶ ዳንኤል አሰፋ የተባሉ የህወሃት  አመራር አባላት መሆናቸውን መረዳት ተችሏል። ቁጥሩ ...

Read More »