በለጋምቦ ወረዳ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ ለጋምባ ወረዳ ከዩኒቨርስቲ ግንባታ መቋረጥ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ለውጥ የተጀመረው ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች እየቀጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለያዩ አጎራባች ወረደዎችና ቀበሌዎች ህዝቡ መኪና መንገዶችን በድንጋይ በመዝጋትና መኪና እንዳይተላለፍ በማድረግ እንዲሁም በጋራ በመሰባስብና ድምጻቸውን በማሰማት ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ የነበቱ ሲሆን፣ ዛሬም ዩኒቨርስቲው በሚገነባበት አካባቢ ተቃውሞ እንደነበር፣ ጉጉፍቱ አካበባ ...

Read More »

በሽብር ወንጀል የተከሰሱት ድርጊቱን ፈጽመናል ወንጀለኞች ግን አይደለንም አሉ

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ ልደታ ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ፣ የተጠቀሰውን ድርጊት መፈጸማቸውን ነገር ግን ወንጀለኞች አለመሆናቸውን ተናግረዋል። በወጣቶቹ ላይ የቀረበው ክስ ግንቦት 7 የተባለውን አሸባሪ ቡድን ለመቀላቀል ሲሄዱ ማካይድራ በተባለው የድንበር ከተማ ላይ ተይዘዋል የሚል ነው። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ‹‹ሀገሬ ...

Read More »

20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተከሰሱ

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፍርድ ቤት በቅርቡ ከፍተኛ ቅጣት የጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ የጠየቁ 20 ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸዋል። ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ላይ እንዲነሳ ቀስቅሰዋል በሚል በ14ኛ ወንከል ችሎት የተከሰሱት ከድር መሃመድ፣ ነዚፍ ተማም፣ ካሊድ መሃመድ፣ ፉአድ አብዱልቃድር፣ ኢብራሂም ካሚል፣ አብዱ ጁባር፣ ሁሴን አህመድ፣ ሃሚድ ሙሃመድ፣ ቶፊቅ ሚስባህ፣ ዑስማን አብዱ፣ ...

Read More »

በአዋሳ ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ ተሰማ

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን በላከው ሪፖርት በከተማ ውስጥ ባለፉት 3 ቀናት ከፍተኛ ሆነ የነዳጅ እጥረት በመከሰቱ ፣ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት ሲቸገሩ ታይቷል። በርካታ ባጃጅ ተሽከርካሪዎች ቀኑን ሙሉ በየማደያዎች ተሰልፈው የታዩ ሲሆን፣ ይህንን ተከትሎ የታየው የዋጋ ጭማሪ ህዝቡን ለምሬት ዳርጎታል። በባህርዳርም እንዲሁ በቅርቡ ተመሳሳይ የነዳጅ እጥረት መከሰቱ መዘገቡ ይታወሳል።

Read More »

የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር በመካሄድ ላይ ነው

ነኅሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ባለው ድርድር፣ ፕ/ት ሳልቫኪርና ተቀናቃኛቸው ሪክ ማቻር ተገኝተዋል። የድርድሩ የመጨረሻው ቀን ዛሬ ሲሆን፣ ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ፊርማቸውን የማያኖሩ ከሆነ ማእቀብ ይጠብቃቸዋል ተብሎአል። የተለያዩ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ድርድሩን በተመለከተ የሚጋጩ መረጃዎችን እየለቀቁ ነው። የዩጋንዳው መሪ ዩዎሪ ሙሰቬኒ ድርድሩ ሳይጠናቅ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

Read More »

በለጋምባ ወረዳ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነሃሴ 7 ፣ 2007 በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ አድማ በታኝ ፖሊስ በአካባቢው የሰፈረ ሲሆን፣ ውጥረቱ አሁንም ድረስ መኖሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ዩኒቨርስቲው ይገነባበታል ተብሎ በሚታሰበው ቦታ አካባቢ ዛሬም ግጭት እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል። በትናንቱ ግጭት የወረዳውን አስተዳዳሪ ጨምሮ፣ ሌሎች አመራችም የተደበደቡ ሲሆን፣ እስካሁን ...

Read More »

የልዩ ሃይል ፖሊሶች በማንዱራ አንድ ሰው ገደሉ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመተከል ዞን በማንዱራ ወረዳ ቴዎድሮስ ስሜነህ የተባለ ሰው በፌደራል ፖሊስ አባላት ተደብድቦ ተገድሏል። ቴዎድሮስ ከትናንት በስቲያ በፌደራል ፖሊስ አባላት ከቤቱ ተይዞ ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ሲደበደብ አርፍዷል። ድብደባውን ተከትሎም ህይወቱ ወዲያውኑ ማለፉን ፣ የቀብሩ ስነስርዓት ትናንት መፈጸሙን ለማወቅ ተችሎአል። ቴዎድሮስ የተቃዋሚ ሃይሎች አባል ነህ ተብሎ ክትትል ሲደረግበት ቆይቷል። ወጣት ቴዎድሮስ ...

Read More »

የጣልያኑ የመረጃ መረብ ጠላፊ ድርጅት ሃኪን ቲም ከኢትዮጵያ የስለላ ድርጅት ጋር ያለውን ግንኙነት አላቋረጠም ሲል ሂውማን ራይትስ ወች ወቀሰ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሃኪን ቲም ሰብዓዊ መብትን ከሚያፍኑ መንግስታት ጋር አብሮ መስራቱ ይፋ ከሆነ በሁዋላ፣ ከዚህ ዕኩይ ተግባሩ ይታቀብ ዘንድ በተደጋጋሚ ጊዜ ማሳሰቢያ ቢደርሰውም ፣ አሁንም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት አላቋረጠም ሲል ሂውማን ራይትስ ወች በሪፖርቱ ገልጿል። የጣልያኑ የመረጃ መረብ ጠላፊ ድርጅት ሃኪን ቲም ለተለያዩ መንግስታት የመገናኛ መረብ መጥለፊያ ቴክኖሎጂዎችን በመሸጥና ስልጠና በመስጠት ጭምር ...

Read More »

አንድ ኢትዮጵያዊ በአውሮፕላኑ በዕቃ መጫኛ ክፍል ውስጥ ተደብቆ ስዊድን ገባ

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያዊው ከአዲስ አበባ ተነስቶስ ስዊዲን ስቶኮልም አየር ማረፊያ መድረሻውን ባደረገው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው አውሮፕላን ውስጥ በዕቃ መጫኛ ውስጥ ለስምንት ሰዓታት ተደብቆ ስዊድን አራንዳ አየር ማረፊያ ገብቷል። የስዊድን ፖሊስ እንዳስታወቀው አውሮፕላኑ ጣሊያን ሮም ላይ አርፎ ነበር። የአየሩ ሁኔታ በጣም ቀዝቃዛ የነበረ ቢሆንም የጤንነቱ ሁኔታ ግን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል ያለው ፖሊስ፣ ...

Read More »

ከረዢም አመታት በፊት የተጀመረው የባህርዳር ሞጣ ብቸና መንገድ አሁንም ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ፡፡

ነኅሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአመታት በፊት ተጀምሮ በማዝገም ላይ ያለው የባህርዳር ሞጣ ደጀን መንገድ አሁንም በንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ በትራንስፖት ቢሮ የትራንስፖርት አገልግሎት የስምሪት ተተኪ የስራ ሂደት ውስጥ የሚገኙ ባለሙያ እንደተናገሩት መንገዱ በተደጋጋሚ በመበላሸቱ እና ለረዢም ጊዜ ባለመሰራቱ ህብረተሰቡ መቸገሩን ገልጸው፤ለመንገድ ስራ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤቶች ስራውን እንዲያጠናቅቁ ...

Read More »