ጷግሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኞ ዕለት በሶማሊያ ጌዶ ግዛት የቀድሞ አስተዳዳሪ የነበሩት ሞሃመድ አብዲ ከሊል ከባድ መሳሪያ ከታጠቁ አጃቢዎቻቸው ጋር በመሆን ጋርባሃሬ ከተማ ሲገቡ አካባቢው የጦርነት ድባብ ውስጥ መውደቁን የከተማዋ ነዋሪዎች እማኝነታቸውን ሰጡ። የገርባሃሬ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ሰራዊት የሚደገፈው አዲሱ የጁባላንድ አስተዳዳሪ አህመድ ማዶቤ በከተማዋ በኃላፊነት መሾሙ እየታወቀ የሞሃመድ ከሊል ወደ ከተማዋ ተመልሶ መምጣት እንዳስገረማቸው ገልጸዋል። የቀድሞ ...
Read More »ለ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ምላሽ አልተገኘም
ኢሳት ዜና (ጳጉሜ 2, 2007) የኢትዮጵያ መንግስት በሃገሪቱ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ወደ አምስት ሚሊዮን ሰዎች ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ምላሽ አለማግኘቱን ገለጠ። ከእርዳታ ሰጪዎች የታየውን ዝምታም ተከትሎ መንግስት ከአገር ውስጥ ገበያ የእህል ግዥ ለማከናወን መገደዱን የግብርና ሚኒስትር ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። የእርዳታ ሰጪዎች በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ችግር ውስጥ ለገቡ እንዲሁም በመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ የኔፓል ህዝብ እርዳታ በማቅረብ ላይ ...
Read More »ህወሃት/ ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ወራራ ሊፈጽም ይችላል ተባለ
ኢሳት ዜና (ጳጉሜ 2, 2007) የኤርትራ መንግስት ከጎረቤት ኢትዮጵያ ወታደራዊ ወረራ ሊፈጸምብኝ ይችላል ሲል ዛሬ ሰኞ ገለጠ። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ (ህወሃት) ፓርቲ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገሪቱ ላይ እያቀረበ ያለው ፀብ-ጫሪ መግለጫና ንግግር እየጨመረ መምጣቱን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ማመልከቱን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የተለያዩ ሃይሎችን ድርጊት ከኤርትራ ጋር ለማቆራኘት ጥረት ሲያደርግ የቆየው የህወሃት ገዢ ፓርቲ ከተያዘው ክረምት ...
Read More »ኤርትራ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች
ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤኤፍፒ የአገሪቱን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በመጥቀስ እንደዘገበው፣ የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ የሚያሰማው የጦርነት ዛቻና አገሪቱን እወራለሁ እያለ የሚያሰማው መግለጫ ጨምሯል። የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት /ህወሃት በተለየ ሁኔታ በኤርትራ ላይ ዛቻ እያሰማ ነው። በክረምቱ ወር ይሰማ የነበረው ፉከራ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ተጠናክሮ መቀጠሉን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ገልጿል። የህወሃት አገዛዝ ኤርትራን እንዲወር ከአሜሪካ ፈቃድ ...
Read More »በጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ የክለሳ ምዝገባ መታሰቡ ሕዝብን አስቆጣ
ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ መኩሪያ ኃይሌ የሚመራው የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ2005 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የራራ መኖሪያ ቤቶችን ለማግኘት በድጋሚ የተካሄደውም ምዝገባ ዳግም እከልሳለሁ ማለቱ አብዛኛዎችን ነዋሪዎች አስቆጣ፡፡ ሚኒስቴሩ በመጋቢት 2007 ዓ.ም የወጣው 10ኛ ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ነዋሪው ከአቅሙ በላይ መሆኑን መግለጹን መነሻ በማድረግ ተመዝጋቢዎች አቅማቸውን የፈቀደውን እንደሚዘገቡ ዳግም ዕድል ለመስጠት ...
Read More »የምግብ እና የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ
ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማእከላዊ ስታትስቲክስ መስሪያ ቤት ባወጣው ሪፖርት በነሃሴ ወር ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዋጋቸው ጨምሯል። የጭማሪዎች መጠን ከክልል ክልል ሲለያይ አዲስ አበባ ፣ አፋርና ኦሮምያ ከፍተኛ ጭመሪ ታይቶባቸዋል። የምግብ ዋጋ ከአምናው ጋር ሲተያይ 11 ነጥብ 6 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ምግብ ነክ ያልሆኑ ደግሞ በ8 ነጥብ 9 ጭማሪ አሳይተዋል። በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላና አትክልት ...
Read More »አርበኞች ግንቦት7 የተሳኩ ስብሰባዎች ማድረጉን አስታወቀ
ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንቅናቄው ለኢሳት በላከው መረጃ እንደገለጸው በተለያዩ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በተካሄዱ የአገርን አድን ጥሪዎች ህዝቡ ለንቅናቄው ያለውን ድጋፍ ገልጿል። ብጹ አቡነ መቃርዮስና አቶ ብዙነህ ጽጌ በእንግድነት በተገኙበት በስዊዘርላንድ በተካሄደው ስብሰባ፣ ሴቶች በውድ ገንዘብ የተገዙ የእጅ አምባራቸውን ሰይቀር ለግሰዋል። በዝግጅቱም ከፍተኛ ገንዘብ ተሰብስቧል። የቶሮንቶ፣ ካልጋሪና ኦክላንድ ስብሰባዎችም እንዲሁ በጥሩ ውጤት መጠናቀቃቸው ተገልጿል።በኖርዌይ ስታቫንገር ...
Read More »አስራ አንድ ኢትዮጵያዊያን በኬንያ ካለሕጋዊ ቪዛ በመግባታቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ
ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ፓንጋኒ ውስጥ አስራስምንት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ካለፍቃድና ሕጋዊ ቪዛ ኬንያ ውስጥ በመግባት የተከሰሱ ሲሆን ሰባቱ ፓሊስ በእጃችን ላይ የነበረውን ሕጋዊ ዶክመንቶች ወስዶብናል በማለት ክሱን ያስተባበሉ ሲሆን ሌሎች አስራ አንዱ ግን በአስተርጓሚ በኩል በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል የቀረበባቸውን ክስ ማመናቸውንና ለፍርድ ውሳኔው ለሴፕቴንበር 8 ቀን መቀጠራቸውን ዘስታር ዘግቧል።
Read More »አልሸባብ ሁለተኛዋን ስትራቴጂክ ከተማ ተቆጣጠረ
ጷግሜን ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሶማሊያ የአፍሪክ ሕብረት ሰላም አስከባሪ ጦር አሚሶም በኡጋንዳና በኢትዮጵያ ወታደሮች ቁጥጥር ስር የነበረው በመሃከላዊ ሂራን ግዛት ቡቅአበል ሁለተኛው ስትራቴጂካዊ ከተማ በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ውሏል። እስላማዊ ታጣቂዎቹ በስተደቡብ ሶማሊያ የምትገኘውን ኩርቱዋሬንና ከሞቃዲሾ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኘውን የጃናሌን ከተሞች ባለፈው ሶስት ቀናት በቁጥጥራቸው ስር ማድረጋቸው ይታወሳል። በሶማሊያ ከ6,200 በላይ የሚሆኑ የኡጋንዳ ወታደሮች የሚገኙ ሲሆን ...
Read More »በአርባምንጭ የአንድ ቤተሰብ አባላት በስቃይ ላይ ናቸው
ነኅሴ ፳፰ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ የአንድ ቤተሰብ አባላት ልጆቻችሁ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት ናቸው በሚል ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ለኢሳት ገለጹ። ፈቃዱ አበበ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወንድምህ አርበኞች ግንቦትን እንዲቀላቀል አድርገኸዋል በሚል ካለፈው አንድ አመት ጀምሮ በማእከላዊ እስር ቤት ታስሮ እየተሰቃየ ሲሆን፣ የእርሱ ታናሽ ወንድም ደግሞ በፖሊሶች ከፉኛ ተደብድቧል። ይህም አልበቃ ብሎ፣ ...
Read More »