ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሰው በ19ኛው ወንጀል ችሎት ነጻ የተባሉት የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሃብታሙ አያሌው፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ል ሰብሳቢ የነበረው የሽዋስ አሰፋ፣ የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ም/ል ስብሳቢና የደቡብ ተወካይ የነበረው ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም አብርሃም ሰለሞን ፣ ዛሬ ጠ/ፍርድ ቤት ቀርበው፣ በአቃቢ ህግ የተጠየቀባቸው ይግባኝ ትክክል አይደለም በማለት ለመከራከር ቀጠሮ ...
Read More »በፍቼ ከተማ ባጃጅ አሽከርካሪዎች የስራማቆም አድማ አደረጉ
ጥቅምት ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በፍቼ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት መስሪያ ቤትስራችንን በአግባቡ ሊያሰራን አልቻለም በሚል ምክንያት የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከትናንት ጀምረው የስራማቆም አድማ አድርገዋል። የከተማው መንገድ ትራንስፖርት ባጃጅ ለመንዳት የታክሲ አንድ ፈቃድ መያዝ ያስፈልጋል የሚል መመሪያ ያወጣ ሲሆን፣ በሶስተኛ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክር የተገኘ ሹፌር 2 ሺ 500 ብር ይቀጣል። የቅጣቱን መጠንና መመሪያውን የተቃወሙት ሹፌሮች አድማቸውን ለምን ...
Read More »ህወሃት ያገለላቸውን የቀድሞ አባላቱን እየመለሰ ነው ተባለ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2015) የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ህወሐት ) ማእከላዊ ኮሚቴ ከአመታት በፊት በጡረታ የተገለሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች በድጋሚ እንዲደራጁ አዘዘ። ባለፈው እሁድ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመቀሌ ከተማ ጉባኤ ያካሄደው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ፣ በትጥቅ ትግሉ ወቅት እንዲሁም በጡረታ ሰበብ የተሰናበቱ ታጋዮች ዳግም የማደራጀት ስራ እንዲካሄድ ወስኗል። ከአመታት በፊት በእድሜና በተለያዩ ምክኒያቶች በሺዎች የሚቆጠሩ የህወሀት ታጋዮች እንዲሰናበቱ ...
Read More »የግብፅ ልዑካን ቡድን በአባይ ግድብ ዙሪያ ከሱዳን ጋር ለመምከር ካርቱም ገባ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2 ፣ 2008 ዓም) በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል በአባይ ግድብ ዙሪያ ሊካሄድ የነበረው ድርድር መዘግየትን ተከትሎ፣ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ከሱዳን ጋር የሚመክር የልዑካን ቡድን ወደ ሃገሪቱ ላኩ። በሃገሪቱ የመስኖ ልማት ሚኒስትር ሆሳም ሞግሃዚ የተመራው ይኸው ልዩ የልዑካን ቡድን፣ ከፕሬዚዳን አልሲሲ የተላከን ልዩ መልዕክት በመያዝ ከሱዳን ባለስልጣናት ጋር ለመምከር ካርቱም መግባቱን አል-አህራም የተሰኘ የግብጽ ጋዜጣ ዘግቧል። ግብፅ ...
Read More »በሶማሊያ በኢትዮጵያ ሰራዊትና አልሻባብ መካከል ከፍተኛ ውጊያ መካሄዱ ተገለጸ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 2, 2008ዓም) በቅርቡ ወደሶማሊያ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በደቡባዊ የሃገሪቱ ክፍል ለሁለተኛ ሳምንት ከባድ ውጊያ ኣያካሄደ ኣንደሚገኝ የሶማሊያ ወታደራዊ ባለስልጣናት ትናንት ገለጹ። ለሁለተኛ ሳምንት ቀጥሎ የሚገኘው ግጭት ልዩ ስሙ አልዩ ዲዮ በተባለ ደቡባዊ ምዕራብ የሶማሊያ አካባቢ እየተካሄደ እንደሚገኝ እነዚሁ ወታደራዊ ባለስልጣናት ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ በአካባቢው እየተካሄደ ባለው ውጊያ፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይልና የሶማልያ ብሄራዊ ጦር ...
Read More »በኢትዮጵያ የእለት ደራሽ ዕርዳታ የሚሹ ወገኖች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ አሻቀበ፡፡
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስትና አለማቀፍ ድርጅቶች በሰጡት መረጃ መሰረት የተረጂው ጠቅላላ ቁጥር 8 ነጥብ 2 ሚሊየን ደርሷል፡፡ መረጃዎች ግን ከዚህ በላይ መሆኑን ያመለክታሉ። የተጠቀሰው አሃዝ ቀደም ሲል በሴፍቲኔት ፕሮግራም ታቅፈው የሚረዱ ወደ 3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኢትዮጵያዊን ወገኖችን ይጨምራል ተብሎአል። ይሁን እንጅ መንግስት ያዘጋጀው እና አለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የሚጠቅሱት ሰነድ በምግብ ለስራ የታቀፉ ዜጎች ቁጥር ...
Read More »በአዳ- በርጋ ወረዳ 30 ወጣቶች ታሰሩ
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳ በርጋ ወረዳ 30 ወጣቶች በኦሮምያ ልዩ ሃይሎች በሌሊት ታፍነው መወሰዳቸውን ሂውማን ራይትስ ሊግ ኦፍ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ ገለጸ። ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ አብዛኞቹ የታሰሩት ወጣቶች የናይጀሪያዊው ባለሀብት ንብረት የሆነው የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች እና ለእረፍት ወደ ቤተሰቦቻቸው የሄዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው። ወጣቶችን በማፈን መመሪያ የሰጠው ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አያያዙ አስከፊ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ገለጹ
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሶ በእስር ላይ የሚገኘው ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የእስር ቤት አስተዳዳሪዎች በሚያሳድሩበት ጫና ለተጨማሪ ስቃይ እየተዳረገ መሆኑን የሙያ አጋሮቹ ተናግረዋል። የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ ውቤ እንደገለጹት፣ እስክንድርን ከሁለት የቅርብ የቤተሰብ አባላት ውጭ ሌሎች ሰዎች እንዳይጥቁት ተከልክለዋል። በሃይማኖት አባቶችም ሆነ በጠበቃ እንደማይጎበኝ የገለጸው ጋዜጠኛ አበበ፣ በእስር ቤት ውስጥ ...
Read More »አዳማ በ6 አመታት ውስጥ 7ኛው ከንቲባ ተሾመላት
ጥቅምት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ ላለፉት 2 አመታት ከተማዋን ሲመሩ የነበሩትን አቶ አብርሃም አዱላን ወደ ክልል ቢሮ በማዛወር የሻሸመኔ ከንቲባ የሆኑትን ለከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አዲሱ ከንቲባ በሻሸመኔ የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በማሰቃት የሚወነጀሉ ሲሆን፣ ለአዳማ የተወሳሰበ ችግር መፍትሄ ያመጣሉ ተብሎ እንደማይታመን ምንጮች ይገልጻሉ። ነባሩ ከንቲባ፣ በደባል ሱሶች በመጠመድ ያለፉትን ሁለት አመታት ይህ ነው የሚባል ስራ ሳይሰሩና ...
Read More »በቴፒ አንድ የፖሊስ አባል ሲገደል አምስት ፖሊሶች መታገታቸው ተሰማ
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአመት የዘለቀው የቴፒ ግጭት በአካባቢው ለሰፈረው የፌደራል ፖሊስ እና ለፌደራል ባለስልጣናት እንቆቅልሽ ሆነ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ ባለፈው ቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ሚሊኒየም ጎዳና ላይ ወይም ሚካኤል አካባቢ ካሳሁን የተባለ የከተማው ፖሊስ አባል ተገድሏል። ፖሊሱ በቅርቡ ለከተማው ተመድቦ የመጣ ነበር። እርምጃውን የወሰዱት ራሳቸውን የቴፒ ወጣቶች ብለው የሚጠሩ ታጣቂዎች ናቸው። ታጣቂዎቹ ...
Read More »