ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ150 ላላነሱ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በኦህአዴድ በኩል ተቀባይነት እንደሌለው መገለጡን ተከትሎ የአዲስ አበባ መስተዳድር በአስተዳደር ክልሉ ስር በሚገኙ ቦታዎች ላይ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ቢጀመርም፣ እንቅስቃሴው ከእልህና ከግራ መጋባት የመጣ በመሆኑ ውጤታማ አይሆንም ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ። ከመጀመሪያው ጀምሮ በእቅዱ የተለያዩ ደረጃዎች የተሳተፉ ...
Read More »ለኪሳራ የተዳረጉ መለስተኛ ፋብሪካዎች ሰራተኞችን መቀነስ ጀመሩ
ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግር እጅግ ተባብሶ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ በተለይ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቁዋማት ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረጉ፣ ሰራተኞችም እየቀነሱ ነው። የሃይል እጥረቱ ተባብሶ በአሁኑ ወቅት በእየለቱ ቢያንስ ለግማሽ ቀን ወደመጥፋት ደረጃ ተሸጋግሯል። ት/ቤቶች፣ሆስፒታሎች ፣ዳቦ ቤቶችና የመሳሰሉ ስራቸው እየተስተጉዋጎለ ሲሆን አምራች ተቁዋማት ሰራተኞችን እየቀነሱ ነው። አንድ በዳቦ መጋገር ስራ የተሰማሩ ባለሀብት ሀይል ...
Read More »እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው
ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው ነጻ የተባሉትና እንደገና ይግባኝ የተጠየቀባቸው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ አብርሃም ሰለሞን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም እንደገና ሌላ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ፍርድ ቤቱ ፣ አቃቤ ህግ በስር ፍርድ ቤት አልተመረመረልኝም ያለው ከብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማዕከል የተገኘው ማስረጃ፣ ማስረጃ ሳይሆን ...
Read More »በዓለምአቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ቢያሽቆለቁልም በኢትዮጵያ አሁንም የዋጋ ማሻሻያ አልተደረገም
ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመላው ዓለም የነዳጅ ዋጋ አሽቆልቁሏል። በኢራን ላይ የተጣለው የኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ መነሳቱን ተከትሎ የነዳጅ አቅርቦት ምርት መትረፍረፉን የምጣኔ ሃብት ጠበብቶች እየገለፁ ነው። በየቀኑ ከግማሽ ሚሊዮን በርሜል በላይ ድፍድፍ የነዳጅ ዘይት የማቅረብ አቅሙ ያላት መሆኑን የኢራን ምክትል የነዳጅ ሚንስቴር የሆኑት ሮኬንዲ ጃቫዲ ማስታወቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅት የአንድ በርሜል የነዳጅ ዘይት ዋጋ በአማካኝ ...
Read More »በሶማሊያ በአሸባሪዎች የተገደሉት የኬኒያ ወታደሮች አስከሬን በክብር ወደ አገሩ ተመለሰ ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ሕብረት ጦር አሜሶን ስር በመሆን በሶማሊያ ሰላም ለማስከበር ተሰማርተው የነበሩ የኬንያ ወታደሮች ባለፈው ሳምንት በአሸባሪዎች በተሰነዘረ ጥቃት መገደላቸውን ተከትሎ አስከሬናቸው ናይሮቢ ደርሷል። የኬኒያ መከላከያ ሚንስትር የሆኑት ራቼሎ ኦማሞ ”በጣም ወሳኝ ዜጎቻችን! የወደቁ ጀግኖቻችን” ሲሉ ሟቾቹን አሞካሽተዋል።መንግስት የሟች ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በህጻናት ላይ ከጦርነት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ጉዳት እያደረሰ ነው ተባለ
ኢሳት (ጥር 09 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣው የድርቅ አደጋ በህጻናት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ጦርነት በሶሪያ ህጻናት ላይ እያደረሰ ካለው አደጋ ጋር ተመሳሳይ እየሆነ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቁ። ይኸው በስድስት ክልሎች ጉዳትን እያደረሰ ያለው የድርቅ አደጋ ከ 400ሺ በላይ በሚሆኑ ህጻናት ላይ ክፉኛ የአካልና የጤና ችግርን እያስከተለ እንደሚገኝ ድርጅቱ ገልጿል። ድርቁ በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ጦርነት በሶሪያ ህጻናት ...
Read More »በሆሳዕና ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋረጠ
ኢሳት (ጥር 09 ፥ 2008) በሆሳዕና ከተማ ከመንጃ ፈቃድ ቅጣት እና አስተዳደር ብልሹነት ጋር በተያያዘ የህዝብ የትራስፖርት ማመላለሻ አገልግሎት ለሁለት ቀን ተቋርጦ መዋሉት ዛሬ ሰኞ ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። አንድ ሆሳዕና ወደሌላ ወረዳ ወይም ከወደ ዋና ዋና ከተሞች የሚያጓጉዙ የትራንስፖት መገናኛ አገልግሎቶች በመቋረጣቸው ህዝቡ ከፍተኛ የትራንስፖርት ችግር ውስጥ ላይ እንደሆነ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ በሆሳዕና የሚኖሩ ሰው ለኢሳት በስልክ ተናግረዋል። ...
Read More »አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ተቋርጠው የነበሩት ከ80 በላይ የሚሆኑ ክሶች እንደገና እንዲታዩ ተወሰነባቸው
ኢሳት (ጥር 09 ፥ 2008) ከመንግስት ጋር ያደረጉት ስምምነት ተከትሎ በቅርቡ ወደሃገር የተመለሱትና ከቀናት በፊት ለእስር የተዳረጉት የአክሰስ ሪል ስቴት መስራች የተቋረጡባቸው ከ 80 በላይ ክሶች እንደገና እንዲታዩ ተወሰነ። የኩባንያው መስራችና አመራር አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ወደሃገር ከተመለሱ በኋላ ሊተገብሩ ቃል የገቡትን ስራ ባለማከናወናቸው ምክንያት ክሳቸው እንዲቀጥል መደረጉን የፍትህ ሚኒስቴር ገልጿል። ከመንግስት ጋር ድርድር አድርገው ባለፈው አመት ወደሃገር ቤት የተመለሱት የአክሰስ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሏል
ኢሳት (ጥር 09 ፥ 2008) ከ150 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት እንደሆነ የተነገረለት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ በሳምንት መገባደጃና ሰኞ በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች መቀጠሉ ተገለጸ። እሁድ በትንሹ ለስድስት ሰዎች መገደል መንስዔ የሆነው የመኢሶ ከተማ ተቃውሞ ሰኞ መቀጠሉንና በአካባቢው ያልተለመደ የጸጥታ ስጋት መንገሱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በምስራቅ ወለጋ ዳግም ያገረሸው የነዋሪዎችና የተማሪዎች ተቃውሞም በጨንጊ አካባቢ የቀጠለ ሲሆን ቁጥሩ ...
Read More »ታንዛኒያ 83 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሏን አስታወቀች
ኢሳት (ጥር 09 ፥ 2008) ታንዛኒያ በህገ-ወጥ መንገድ ወደሃገሪቱ ገብተዋል ያለቻቸውን 83 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ሰኞ አስታወቀች። የምቤያ ግዛት ፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ፒተር ከካምፓ ስደተኛ ኢትዮጵያውያኑ ወደጎረቤት ማላዊ ለመጓዝ እቅድ እንደነበራቸውና ያለምንም የጉዞ ሰነድ ወደ ታንዛኒያ መግባታቸው ገልጸዋል። 83ቱ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በአንድ የጭነት ተሽከርካሪ ውስጥ በመሆን በጉዞ ላይ እንዳሉ በጸጥታ ሃይሎች ሊያዙ መቻሉን ዘ-ሲቲዝን የተሰኘ የሃገሪቱ ጋዜጣ ዘግቧል። ...
Read More »