ኢሳት (ጥር 12 ፥ 2012) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ያገረሸ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቋውሞ በምዕራብና በምስራቅ የኦሮሚያ ክልሎች በሚገኙ ከተሞች መቀጠሉ ተገልጿል። የሰሞኑ በመኢሶ ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ እልባት ያላገኘ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞዎችም በወለጋ አካባቢ በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የተቋረጡ የከፍተኛ ትምርት ተቋማት ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ እየተደረገ ያለው ጥረትም ተማሪዎች በሚያቀርቡት ጥያቄ ምክንያት አለመሳካቱ ተገልጿል። በእስር ላይ የሚገኙ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት ጠንካራ የተባለውን ውሳኔ በኢትዮጵያ ላይ አሳለፈ
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 7ቱ ዋና ዋና የአውሮፓ ህብረት የፖለቲካ ድርጅቶች ኢትዮጵያን በተመለከተ የቀረበውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽድቀዋል። አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቀኝ አክራሪዎች ብቻ ውሳኔውን ተቃውመውታል። ለህጉ መጽደቅ ከፍተኛ ትግል ሲያካሂዱ የሰነበቱት የህብረቱ የፓርላማ አባል ሚስ አና ጎሜዝ በውሳኔው መደሰታቸውን ተናግረዋል። “በጣም ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው፣ በተለይ ዋና ዋና የሚባሉት የፖለቲካ ድርጅቶች የውሳኔው ሰነድ ...
Read More »በጋምቤላ በተነሳው ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎዱ
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማዋ ምንጮች እንደገለጹት ጥር 11 ፣ 2008 ዓም 11 ሰዓት አካባቢ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ በተነሳው ግጭት በርካታ ተማሪዎች ተጎድተዋል።ግጭቱ ወደ ከተማው በመስፋፋቱ በርካታ ሰዎች ሲቆስሉ ፣ መኪኖችም ተሰባብረዋል። የግጭቱ መንስኤ በትክክል አልታወቀም። የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና የፈደራል አባላት ከተማዋን መቆጣጠራቸውን የገለጹት ነዋሪዎች፣ ግጭቱ ለጊዜው የቆመ ቢመስልም በማንኛውም ሰአት ...
Read More »ኢትዮጵያ ያወጣችው የጸረ ሽብርተኝነት ህግ እንዲሰረዝ አለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ጠየቁ
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦክላንድ ኢንስቲቲዩት እና ኢዲኤል ሲ የተባሉት መንግስታዊ ድርጅቶች በጋራ ባስጠኑት ጥናት፣ የኢትዮጵያ የጸረ-ሽብርተኝነት ህግ አለማቀፍ መስፈርቶችን ያላሟላ በመሆኑ ለውጥ እሰከሚካሄድበት ጊዜ ድረስ ጥቅም ላይ እንዳይውል ጠይቀዋል። ድርጅቶቹ ጥናቱን ያወጡት የአፍሪካ ህብረት 26ኛ ጉባኤ በሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርጎ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን ምክንያት በማድረግ ነው። ጥናቱ በአለማቀፍ ህግ እውቅና ...
Read More »መንግስት ከፍያ የተፈጸመባቸውን ቤቶች ሰርቶ ማስረከብ አልቻለም ሲሉ ደንበኞች ተናገሩ
ጥር ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ2005 ዓም መንግስት 40 በ 60 በሚል ላወጣው መርሃ ግብር ከ163 ሺ በላይ ህዝብ የተመዘገበ ቢሆንም፣ እስካሁን ቤቶችን ሰርቶ ለማስረከብ አልቻለም። በፕሮግራሙ መሰረት 40 በመቶውን ቤት ፈላጊዎች ሲከፍሉ፣ ቀሪው 60 በመቶ በባንክ ብድር ይሸፈንላቸዋል። ሆኖም መቶ በመቶ ለከፈሉ ቅድሚያ ይሰጣል በመባሉ ከ8 ሺ በላይ ነዋሪዎች የተጠየቁትን መቶ በመቶ ከፍለው ቤቱን ...
Read More »ጅቡቲ ወደኢትዮጵያ በሚገቡ እቃዎች ላይ የጨመረችው የፍተሻ ታሪፍ በሁለቱ ሃገራት መካከል አለመግባባት መፍጠሩ ተገለጠ
ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) የጎረቤት ጅቡቲ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዕቃዎች ላይ በዘመናዊ ማሽን ፍተሻን በማካሄድ በአንድ ኮንቴንይነር እስከ 35 ዶላር ለማስከፈል የያዘውን እቅድ በሁለቱ ሃገራት መካከል አለመግባባት መፍጠሩ ተገለጠ። ጅቡቲ የወሰደችውን አቋም ተከትሎም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተቋቋመ ቡድን ከሃገሪቱ ጋር ድርድር እያካሄደ እንደሚገኝ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ጅቡቲ አዲሱን መመሪያዋን ከተያዘው ወር ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በገፍ ወደ የመን እየተሰደዱ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) ከ80ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብቻ በጦርነት እልባት ወደላገኘባት የመን መሰደዳቸውንና የኢትዮጵያውያኑ የየመን ስደት እሳስቦት እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረቡዕ ይፋ አደረገ። በየመን የተቀሰቀሰው ጦርነት ቀጥሎ ቢገኝም ባለፈው የፈረንጆች አመት ብቻ 82 ሺ 268 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ህይወታቸውን ለአደጋ በሚጥል ጉዞ ወደየመን መግባታቸው ድርጅቱ ገልጿል። ስደተኞቹ በጀልባዎች የሚያደርጉትም ጉዞ ሆነ የመን ከገቡ በኋላ ...
Read More »በጥምቀት በዓል አከባበር ወቅት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ተቃውሞ ተካሄደ
ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) ዳግም በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ረቡዕ በጥምቀት በዓል አከባበር ወቅትም በተለያዩ ቦታዎች ቀጥሎ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከቀናት በፊት በምስራቅ ሃረርጌና በምስራቅ ወለጋ አካባቢዎች ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ አልባት አለማግኘቱንና የጸጥታ ሃይሎች በስፍራው እርምጃ መውሰድ መቀጠላቸውም ታውቋል። የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ትምህርት ያቋረጡ ዩኒቨርስቲዎች ትምህራትቸውን እንዲቀጥሉ ጥረታቸውን ቢቀጥሉም ተማሪዎች በሚያነሷቸው ጥያቄዎች ምክንያት ...
Read More »የጥምቀት በዓል በመላው አለም በደማቅ ስነስርዓት ተከበረ
ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ዘንድ በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የዘንድሮ የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል ረቡዕ ኢትዮጵውያንን ጨምሮ በተለያዩ የአለማችን ሃገራት ተከበረ። የበአሉ አከባባር ከዋዜማው ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማና በጎንደር ከተማ በርካታ የእምነቱ ተከታዮችና የውጭ ሃገር ጎብኚዎች በተገኙበት በድምቀት መከበሩን ከሃገር ቤት ይተገኘ መረጃ አመልክቷል። እየሱስ ክርስቶስ በዮሃንስ እጅ የተጠመቀበትን እለት በማሰብ የሚከበረው ይኸው አመታዊ በዓል በተለይ በአዲስ ...
Read More »የአውሮፓ ፓርላማ በኢትዮጵያ በተከሰተው ተቃውሞና ሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ሃሙስ ሊመክር ነው
ኢሳት (ጥር 11 ፥ 2008) የአውሮፓ ፓርላማ በኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ እና በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ለመምከር ሃሙስ ልዩ የውይይት መድረክ ሊያካሄድ መሆኑን ይፋ አደረገ። ከ700 በሚበልጡ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የሚካሄደው ይኸው ውይይት የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው እንደሆነም ተገልጿል። በአውሮፓ ፓርላማ አባላት ዘንድ ሃሙስ በብራሰልስ የሚካሄደው ይኸው ልዩ ...
Read More »