በአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ብሶታቸውን አሰሙ

መጋቢት ፳፫( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከነባር እራሻ መሬታቸው የተፈናቀሉ አርሶአደሮች በቂ ያልሆነ ካሳ ሳይከፈላቸው ከቀያቸው በመነሳታቸው ሳቢያ በራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው ላይ የደርሰባቸውን አስከፊ ሰቆቃ የአዲስ አበባ መስተዳድር በጠራው ስብሰባ ላይ በምሬት ተናግረዋል። መንግስት ትንሽ ቦታ እንኳን ሳይሰጣቸው ከይዞታቸውን እንዲነሱ በመደረጋቸው ለአስከፊ ሕይወት መዳረጋቸውንና ለወደፊቱም ልጆቻችንን ምን እናብላቸው? እንደ እቃ ሜዳ ላይ ተጥለናል ሲሉ ተፈናቃይ አርሶ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጡ ተጠቃሚዎችን እያስመረረ ነው

መጋቢት ፳፫( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክልሎች ዜጎች ለከፈሉበት የኢንተርኔት መስመራቸው ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት እንዳልቻሉ አስታውቀዋል። ችግሩ በመላው የአገሪቱ ክፍሎች ተባብሶ በመቀጠሉ ደንበኞች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው። የአንድሮይድ ፕሮግራም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በመቋረጡ የፌስ ቡክ፣ የቫይበር፣ ትዊተርና ዋትስ አፕ አገልግሎት ተጠቃሚዎች እየተቸገሩ ነው።

Read More »

በአዲስ አበባ የሚፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም የሚሰሩ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች ሊቋቋሙ ነው ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2008) በአዲስ አበባ የሚፈናቀሉ አርሶ አደሮችን ለማቋቋም የሚሰሩ ፕሮጄክት ጽ/ቤቶች ሊቋቋሙ እንደሆነ ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የአዲስ አበባ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በረቂቅ ደንቡ ላይ የህዝብ ውይይት ለማድረግ በተጠራ ስብሰባ ላይ ሲሆን፣ በውይይቱ ላይ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ግዛው እንደተናገሩት የፕሮጄክት ጽ/ቤት አላማ በልማት ተነሺ ሆነው በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር የተጋለጡ አርሶ ...

Read More »

በቢሾፍቱ (ደብረዘይት) በአንድ ሆቴል ውስጥ የተወረወረ ቦንብ ጉዳት አደረሰ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2008) በቢሾፍቱ ወይንም ደብረዘይት ከተማ በዛሬው ዕለት መጋቢት 22/2008 በአንድ ሆቴል ላይ በተወረወረ የእጅ ቦንብ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ታወቀ። በቦምቡ በትንሹ አንድ ህጻን መገደሉት የአይን እማኞችና የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በቢሾፍቱ ጥበቃውም ተጠናክሮ መቀጠሉም ተመልክቷል። አዋሽ በተባለ ሆቴል ላይ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የሶስት ዓመት ህጻን  የተገደለ ሲሆን፣ የህጻኑ ወላጆችም መቁሰላቸውም ታውቋል። ...

Read More »

የስፔይ ኩባንያ በኢትዮጵያ የቆላ ዝምብ በሽታን ለመከላከል ሰው አልባ አውሮፕላን ሊጠቀም ነው

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2008) አንድ የስፔን ኩባንያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በመጠቀም በቆላ ዝንቦች አማካኝነት የሚመጣውን የእንቅልፍ በሽታ በማይራቡ የቆላ ዝምቦች ለመከላከል እንደሚቻል ገለጸ። የእንስሳት ደም የሚመገበው የቆላ ዝምብ፣ በሰዎች ላይ የድካምና ትኩሳት መለያ ባህርይ ያለው የእንቅልፍ በሽታ እንደሚያመጣና፣ በጊዜው ህክምና ካላገኘ በሰውና በእንስሳት ላይ ሞት ሊያስከትል እንደሚችል ተነግሯል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት በብዛት የሚገኘው የቆላ ዝምብ፣ በየአመቱ ...

Read More »

በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ የኢንቨስትመንት ፍላጎት ጨምሯል ሲሉ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2008) በኦሮሚያ ከተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያየዘ በአጠቃላይ የወደመው ንብረት ከመቶ ሚሊዮን ብር ስለማይበልጥ ብዙ ጉዳት አልደረሰም ሲሉ አቶ ሃይለማሪያ ደሳለኝ ገለጹ። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማሪያም ይህንን የተናገሩት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ሲሆን፣ በጸጥታ ሃይሎች ስለተገደሉ ሟቾች እንዲሁን ታጣቂዎች ዘረፋ ተፈጸመብን ስላሉት ወገኖች አስተያየት አልሰጡም። በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ በቀጣዩ በሃገሪቱ ኢንቨስትመንት ላይ የሚያመጣውን ጉዳት በተመለከተ ...

Read More »

የአሜሪካ ልዑካን በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ በተመለከተ ማብራሪያ ጠየቁ

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ለመመልከትና ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ለመምከር ወደኢትዮጵያ የተጓዘው የአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ልዑካን በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ያሉ ግጭቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ባለው የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ማብራሪያ ጠየቁ። በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲሞራሲያ የሰብዓዊ መብቶች ረዳት ሚኒስቴር ቶም ማሊኖዊስኪ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የአሜሪካ አምባሳደር ፓትሪሺያ ሃስላክ ጋር በመሆን፣ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ...

Read More »

የመሃመድ አልአሙዲን ሆራይዘን እርሻ ሃላፊነቱ የግል ማህበር ግማሽ ቢሊዮን ብር ቅጣት ተጣለበት

ኢሳት (መጋቢት 22 ፥ 2008) የቢሊኒየሩ ባለሃብት የሼህ መሃመድ አላሙዲን ንብረት የሆነው ሆራይዘን እርሻ ሃላፊነቱ ይተወሰነ የግል ማህበር ግማሽ ቢሊዮን ብር ቅጣት ተጣለበት። ገንዘቡም ለማህበራዊ አገልግሎት መስሪያ ቤት ገቢ እንዲደረግ ውሳኔ ተላልፏል። የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ተዘዋዋሪ ከፍተኛ ችሎት የመሃመድ አልአሙዲን ንብረት በሆነው ሆራይዘን እርሻ ሃላፊነቱ የግል ማህበር ላይ ቅጣቱን የወሰነው ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ለፈጸመው ግዢ ክፍያ ባለመፈጸሙ እንደሆነ ...

Read More »

እነ አቶ አለማየሁ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

መጋቢት ፳፪( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት ኩባንያዎችና አባላት በደቡብ አሞ ዞን ከፍተኛ መሪዎች መውሰዳቸው ከተጋለጠ በሁዋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት የደቡበ አሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ መኮንን፣ የፓርቲው አባል አቶ አብረሃም ብዙነህ እንዲሁም አቶ ስለሺ ጌታቸው ከጅንካ እስር ቤት ወደ አዋሳ እስር ቤት እንዲዛውሩ ከተደርጉ በሁዋላ ረቡእ ክሰአት በሁዋላ ...

Read More »

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አምባሳደሮችን እየተማጻኑ ነው

መጋቢት ፳፪( ሃያ ሁለት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃቱ አመራር አባልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ለተመድ የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ቦታ ለመወዳደር የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን መንግስታቸውን አሳምነው ድጋፍ እንዲሰጡ ያደርጉላቸው ዘንድ በመማጸን ላይ መሆናቸው ታውቁዋል። ሰሞኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑ የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን አምባሳደሮች መንግስቶቻቸው በምርጫው ድጋፋቸው እንዲሰጡዋቸው ያደርጉላቸው ዘንድ ሲማጸኑ ...

Read More »