ለኢትዮጵያውያን የእርዳታ እህልን የጫኑ መርከቦች በበርበራ ወደብ ላይ ሊያራግፉ ነው

ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2008) በጅቡቲ ወደብ ለኢትዮጵያ የምግብ ተረጂዎች ሊደርስ የታሰበን የእርዳታ ዕህልን እንደያዙ ለቀናት ወረፋን ሲጠባበቁ የነበሩ መርከቦችን የጫኑትን የእርዳታ እህል ለማውረድ (ለማራገፍ) ወደ ጎረቤት ሶማሊላንድ በርበራ ወደብ አቀኑ። አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በበኩላቸው ለተረጂዎች ሊደርስ የነበረው ድጋፍ በመዘግየቱ ምክንያት ድርቁ የሚያደርሰው ጉዳት እየከፋ መምጣቱን በድጋሚ ገልጿል። የመንግስት ባለስልጣናት የጅቡቲ ወደብ ከአቅሙ በላይ በመጨናነቁ ሳቢያ ለተረጂዎች የእርዳታ እህልንና ...

Read More »

ኢሳት  ወደ አየር ተመለሰ!  

ኢሳት (መጋቢት 26 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ እንደገና ወደ አየር ተመለሰ። በቴሌቪዥን ስርጭቱ ከአንድ ወር በላይ እንዲሁም በሳተላይት ሬዲዮ ስርጭት ከአንድ ሳምንት ያህል የኢትዮጵያ ስርጭቱ የተቋረጠው ኢሳት፣ ከእሁድ መጋቢት 25, 2008 ጀምሮ ስርጭቱ መቀጠሉን የኢሳት አስተዳደር አስታውቋል። አዲሱ የስርጭት መስመር The new frequency is as follows: Satellite                                 Tel Star T12 Transponder                        TXP K33 15 Degrees ...

Read More »

ህወሃቶች ስልጣኑን እሰከ ያዙት ድረስ አማራ ክልል ሊለማ አይችልም ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

መጋቢት ፳፮( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በደባርቅ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ከደባርቅ በየዳ ላይ የሚሰራው መንገድ መዘግየቱ በርካታ ችግር እየፈጠረባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸው፣ በክልሉ ለሚታየው የስራ መጓተትና ሁዋላ ቀርነት ህወሃትን ተጠያቂ አድርገዋል። “የመንገዱ ስራ የሚከናወነው አኪር ኮንስትራክሽን በተባለ ተቋራጭ ሲሆን ድርጅቱ ለረዢም ጊዜ ስራውን ቢያዘገይም ማንም እንዲጨርስ ያስገደደው የለም፡፡” የሚሉት ቅሬታ አቅራቢዎች የከተማዋና የወረዳው ...

Read More »

በጅጅጋ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተነገረ

መጋቢት ፳፮( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ መጋቢት 26፣2008 ዓም ሌሊት የጣለውን ዝናብ ተከትሎ ከ100 በላይ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲገልጹ፣ መንግስት በበኩሉ 13 ሰዎች መሞታቸውንና ከ55 በላይ ደግሞ የደረሱበት ባለመታወቁ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል። እሁድ እኩለሌሊት ላይ የጣለው ድንገተኛ ዝናብ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 8 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል። በርካታ ...

Read More »

ኬንያ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሰረች

መጋቢት ፳፮( ሃያ ስድስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 13 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ-ታንዛኒያ ድንበር መታሰራቸውን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል። እንደ ፖሊስ መግለጫ ኢትዮጵያውያኑ የታሰሩት በኩዋሌ ካንትሪ በምትገኘው በሉንጋ- ሉንጋ ውስጥ እሁድ ማታ ነው። የሳብዌኒ ፖሊስ ኃላፊ ጆሴፍ ኦሚጃህ ህገወጥ የውጪ ሀገር ስደተኞቹን በህንድ ውቅያኖስ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚያስወጡ አሻጋሪዎች እየተጠየቁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ባለፈው መጋቢት ወር በናይሮቢ -ምዕራብ ካሀዋ ...

Read More »

በምስራቅ ሸዋ ቢሾፍቱ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

ኢሳት (መጋቢት 23 ፥ 2008) ሃሙስ በምስራቅ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል በምትገኘው ቢሾፍቱ ከተማ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ የደረሰውን የቦንብ አደጋ ተከትሎ አርብ በከተማ ተቃውሞ በመቅረብ ላይ መሆኑም ታውቋል። በከተማዋ ያልተለመደ የጸጥታ ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ የሚናገሩት ነዋሪዎች የመንግስት አካላት ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በክልሉ እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጋር በተገኛኘ በዩኒቨርስቲዎችና በተለያዩ ከተሞች ተመሳሳይ የቦንብ ጥቃቶች ሲደርሱ መቆየታቸው ይታወሳል።

Read More »

በኦሮሚያ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ  ከሶስት ሺ በላይ ሰዎች ታሰረዋል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 23 ፥ 2008) አራተኛ ወሩን የያዘው በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ መቀጠሉንና ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸውን ሮይተርስ የተለያዩ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አርብ ዘገበ። የመንግስት ባለስልጣናት በክልሉ ተፈጽሞ ለነበረው ሞትና ጉዳት ይቅርታን ቢጠይቁም በክልሉ እስራቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን የተለያዩ አካላት ለዜና አውታሩ አስታውቀዋል። የዚሁ የጸጥታ ሃይሎች የእስር ዘመቻ 2ሺ 600 ሰዎች ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ ...

Read More »

የአጣዳፊ ተቅማት በሽታ በኦሮሚያ፣ ደቡብና ሶማሊ ክልሎች እየተዛመተ ነው

ኢሳት (መጋቢት 23 ፥ 2008) በቅርቡ በሶማሊና ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ተቀስቅሶ የነበረው የአጣዳፊ ተቅማት በሽታ ወደሌሎች አጎራባች ስፍራዎች በመዛመት ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። በኦሮሚያ ሞያሌ ወረዳ ተከስቶ የነበረው ይኸው በሽታ፣ ገላና እና አባያ ወደተባሉ ወረዳዎች የተዛመተ ሲሆን፣ በሶማሊ ክልል በሚገኘው የሃደት ወረዳም የአጣዳፊ ተቅማት በሽታው እየተዛመተ መሆኑ ታውቋል። በደቡብ ክልል ደግሞ የአማሮ ወረዳና የአርባምንጭ ከተማ አካባቢዎች ...

Read More »

በድርቅ የተጠቁ 106 ወረዳዎች ልዩ ክትትል ይፈልጋሉ ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 23 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለውን የድርቅ አደጋ መባባስ ተከትሎ 186 ወረዳዎች ልዩ ክትትልን የሚፈልጉ ሆነው መፈረጃቸውን የተባባሩት መንግስታት ድርጅት አርብ ዕለት አስታወቀ። በሶማሊ፣ አፋር፣ ትግራይና አማራ ክልል በሚገኙ ወረዳዎች አሳሳቢ የሆነ የምግብ እጥረት ከፍተኛ ጉዳትን እያደረሰ እንደሚገኝም ታውቋል። የእርዳታ ተቋማት በበኩላቸው እርዳታ በወቅቱ እየደረሰ አለመሆኑ ችግሩን እንዳሳሰበው ገልጿል። በዚሁ የሃገሪቱ የድርቅ አደጋ ዙሪያ ሪፖርቱን ያቀረበው ...

Read More »

በወልቃይት ጉዳይ የአማራ ህዝብ እንዳይወያይበት ብአዴን እገዳ በመጣሉ አፍረናል ሲሉ ነዋሪዎች ገለፁ

መጋቢት ፳፫( ሃያ ሦስት ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በደባርቅ ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የተሳተፉ የከተማዋ ልዩልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተናገሩት ውይይቱ በከተማዋ ጉዳይ ላይ ብቻ እንዲነጋገሩ መገደቡ፤ በዙሪያቸው የሚካሄዱ ጉዳዮችን ሰምተው እንዳልሰሙ እንዲሆኑ መጠየቁ ህገመንግስታዊ መብትን የጣሰ አካሄድ ነው በማለት ክልሉን አስተዳድረው አለሁ በሚለው ብአዴን ማፈራቸውን ገልጸዋል፡፡ ተሰብሳቢዎቹ “እንዲያውም መነጋገር የነበረብን በወልቃይት ጉዳይ ነው፡፡ የወልቃይት ጉዳይ አሁን የሁላችን ...

Read More »