የአጋዚ ጦር እየተበታተነ ነው ተባለ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ አጋዚ ክፍለጦርን ለቀው የወጡ ወታደሮች ለኢሳት እንደገለጹት ጦሩ ከምንጊዜው በላይ እየተበታተነ ይገኛል። አብዛኛው የሰራዊቱ አባል በክፍለጦሩ ውስጥ የሚታየውን ፍጹም ዘረኝነት በመጥላት እየጠፋ ፣ ክፍለጦሩን አመናምኖታል። በአሁኑ ሰአት 2 ሺ የሚሆኑ አባላት ብቻ የቀሩ ሲሆን፣ ከ2007 ዓም ጀምሮ እስካሁን ወደ 3 ሺ የሚደርሱ የአጋዚ ወታደሮች ጥለው ጠፍተዋል። በተለይ ጦሩ ...

Read More »

በምዕራብ ጎጃም በፍኖተሰላም ዙሪያ ወረዳ ጫካ የገቡ ወጣቶችን ለመያዝ ወታደሮች ወደ አካባቢው መንቀሳቀሳቸው ታወቀ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ራሳቸውን አደራጅተው ወደ ገጠር በመውጣት በወታደሮች ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ የሰነበቱ ወጣቶችን ለመያዝ በሚል በሶስት ኦራል መኪኖች የተጫኑ ወታደሮች ወደ አካባቢው አምርተዋል። ባለፈው ሳምንት ከፍተኛ የተኩስ ለውውጥ ይሰማ እንደነበር የገለጹት የአካባቢው ምንጮች፣ ዛሬም የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር ተናግረዋል። ይህንኑ ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ተይዘዋል። ወታደሮች ህዝቡን እያወከቡት መሆኑንም ነዋሪዎች ...

Read More »

በእንግሊዝ ውስጥ የሚገኙ አስጎብኚ ድርጅቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ መሰረዛቸውን አሳታወቁ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቱሪዝም አስጎብኚነት የተሰማሩ የእንግሊዝ ድርጅቶች ለክብረ በዓላት እና ለጉብኝት ወደ ታሪካዊቷ አገር ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞዎች ሙሉ ለሙሉ መሰረዛቸውን አስታውቀዋል። ድርጅቶቹ የጉዞ እገዳቸውን አስመልክቶ በምክንያትነት ያቀረቡት ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን ሕዝባዊ አመጽ አድማሱን በማስፋቱ የደኅንነት ስጋት በአገርቱ በመፈጠሩ ነው። የእንግሊዝ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ዜጎቹ ወደ ኢትዮጵያ ...

Read More »

በሃረር ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የመንግስት ሰራተኞች የአንድ ወር ደሞዝ እንዲያስረክቡ ተገደዱ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰራተኞች ለኢሳት እንደገለጹት ለበአሉ የተመደበው 500 ሚሊዮን ብር በማለቁ ፣ የመንግስት ሰራተኛው የአንድ ወር ደሞዙን እንዲያስረክብ እየተገደደ ነው። መመሪያው ከላይ አመራሮች የወረደ ሲሆን፣ ታች ያሉት አመራሮች በስራቸው ላሉ ሰራተኞችን እንዲነግሩ ታዘዋል። ሰራተኞች “ አገዛዙን ይወረድ እያልን እየጠየቅን ባለበት በዚህ ወቅት ፣ ደሞዛችሁን እንወሰዳለን መባሉ ድፍረት ነው” በማለት ተቃውሞአቸውን እያገለጹ ...

Read More »

አፍሪካውያን ስደተኞች ባህር ውስጥ ሰጠሙ

ጥቅምት ፲፰ (አሥራ ስምንት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መነሻቸውን  የሊቢያዋ ታጁራ የባህር ዳርቻዎች አድርገው ወደ አውሮፓ ሲጓዙ ከነበሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች መካከል ቁጥራቸው ከ90 በላይ የሚሆኑት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የሊቢያ ባሃር ሃይልን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል። የሊቢያ የባሕር ሃይል ቃል አቀባይ የሆኑት አዩብ ቃሲም ፣  ስደተኞቹ እርዳታ እንዲደረግላቸው በጠየቁት መሰረት ቁጥራቸው 126 ከሚገመቱት ተጓዦች መካከል የተወሰኑትን ታድገናል ብለዋል። በያዝነው ዓመት ...

Read More »

የተለያዩ ኩባንያ ዘበኞች ነጻ እርምጃ እንዲወስዱ ታዘዙ

ጥቅምት ፲፯ (አሥራ ሳባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በተለያዩ የህወሃት/ኢህአዴግ እና የውጭ አገር ባለሃብቶች የገነቡዋቸውን ኩባንያዎች የሚጠብቁ ዘበኞች ከ12 ሰአታት በሁዋላ ወደ ኩባንያው በሚመጡ ሰዎች ወይም በኩባንያዎች ላይ አደጋ ሊያደርሱ ይችላሉ ብለው በጠረጠሩዋቸው ሰዎች ላይ ማንኛውንም እርምጃ እንዲወስዱ እንዲፈርሙ ተገደዋል። ይህንን እርምጃ መውሰድ ያልቻሉ ዘበኞች ለሚደርሰው ጉዳት ሃላፊነቱን ይወስዳሉ። ዘበኞቹ በማንኛውም ሰው ላይ የግድያ ...

Read More »

ሶማሊያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር መካከል ያለው አለመግባባት እየጨመረ ነው

ጥቅምት ፲፯ (አሥራ ሳባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ስር በሚገኘውና ከሰላም አስከባሪው ውጭ በሚንቀሳቀሰው የኢትዮጵያ ጦር መካከል ያለው ልዩነት እየሰፋ በመሄዱ ጦሩ በተለያዩ ጊዜያት እርስ በርስ ተዋግቶ የበርካታ ወታደሮች ህይወት ማለፉን ምንጮች ገልጸዋል። በአሚሶም ስር ያሉ ወታደሮች ክፍያ የሚያገኙት ከአለማቀፍ ለጋሾች ከሚሰበሰበው ዶላር ሲሆን፣ ገዢው ፓርቲ ከአሚሶም እውቅና ውጭ ያስገባቸው የጦሩ አባላት ግን ክፍያ ...

Read More »

ወጣት ብሌን መስፍን በድጋሜ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ተሰጣት

ጥቅምት ፲፯ (አሥራ ሳባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሕግ አግባብ ውጪ ተይዛ በስቃይ ላይ የምትገኘው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው ወጣት ብሌን መስፍን በአስር ሽህ ብር ዋስትና መብቷ ተፈቅዶላት ውጪ ሆና ጉዳይዋን እንድትከታተል ሲል የሰባራ ባቡሩ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወቅቱ ውሳኔ ቢያሳልፍም፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም አቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። አቃቤ ሕግ ...

Read More »

ካድሬዎች “አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል ትፈልጋለህ?” የሚል ጥያቄ በማቅረብ ወጣቶችን እያሰሩ ነው። 

ጥቅምት ፲፯ (አሥራ ሳባት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት ካድሬዎች በመለመሉዋቸው ካድሬ ወጣቶች አማካኝነት ስልክ በማስደወል እንዲሁም ቀርቦ በማናገር፣ አርበኞች ግንቦት7 ትን መቀላለቀል ከፈለክ ልናገናኝህ እንችላለን በማለት ካነጋገሩዋቸውና ሃሳባቸውን ካወቁ በሁዋላ፣ አወንታዊ መልስ የሰጡትን ወጣቶች ይዘው እንደሚያስሩ ለማወቅ ተችሎአል። ወጣቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመከሩት የደህንነት ምንጮች፣ ከማንኛውም አካል ፣ አርበኞች ግንቦት 7ትን መቀላለቀል ትፈልጋላችሁ ተብሎ ጥያቄ ከቀረበ ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአፍሪካ ህብረት አመታዊ ጉባዔ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተነገረ

ኢሳት (ጥቅምት 27 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ በቅርቡ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት አመታዊ ጉባዔ ላይ ስጋት ማሳደሩ ተነገረ። የአዋጁ መውጣትን ተከትሎ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የውጭ ሃገራት ተወካዮች ከመዲናይቱ 40 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀው መሄድ ከፈለጉ መንግስት ማሳወቅ እንዳለባቸው መደንገጉ ይታወሳል። ይሁንና ለስድስት ወር ይቆያል የተባለው የአስቸኳይ ጊዜ ዋጅ በቅርቡ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የሚበጠቀው ...

Read More »