ካድሬዎች “አርበኞች ግንቦት7ትን ለመቀላቀል ትፈልጋለህ?” የሚል ጥያቄ በማቅረብ ወጣቶችን እያሰሩ ነው። 

ጥቅምት ፲፯ (አሥራ ሳባት ) ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት ካድሬዎች በመለመሉዋቸው ካድሬ ወጣቶች አማካኝነት ስልክ በማስደወል እንዲሁም ቀርቦ በማናገር፣ አርበኞች ግንቦት7 ትን መቀላለቀል ከፈለክ ልናገናኝህ እንችላለን በማለት ካነጋገሩዋቸውና ሃሳባቸውን ካወቁ በሁዋላ፣ አወንታዊ መልስ የሰጡትን ወጣቶች ይዘው እንደሚያስሩ ለማወቅ ተችሎአል።

ወጣቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የመከሩት የደህንነት ምንጮች፣ ከማንኛውም አካል ፣ አርበኞች ግንቦት 7ትን መቀላለቀል ትፈልጋላችሁ ተብሎ ጥያቄ ከቀረበ እንዳይቀበሉ መክረዋል።