ኢሳት (መጋቢት 8 ፥ 2009) ሰሞኑን በደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ኢትዮጵያ የልዑኩ ቡድን ወደ ደቡብ ሱዳን መላኳን የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አርብ አስታወቀ። የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት ማዊን ሚሎል የሃገሪቱ የቦማ ግዛት የብሄራዊ መንግስቱ ታጣቂዎቹ ወደ ጋምቤላ ክልል ሰርገው በመግባት በሰዎች ላይ ግድያና አፈና መፈጸማቸውን ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ይህም ሆኖ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ “ቆሼ” አካባቢ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 200 ሊደርስ ይችላል ተባለ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 200 አካባቢ ሊደርስ እንደሚችል ነዋሪዎች አስታወቁ። ለአምስተኛ ቀን በተካሄደ ቁፋሮ የሟቾች ቁጥር 115 የደርሰ ሲሆን፣ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች በበኩላቸው 80 ነዋሪዎች አሁንም ድረስ የገቡበት አለመታወቁን ለሮይተርስ የዜና ወኪል ገልጸዋል። አስከሬን የማፈላለግ ስፍራው ተጓትቷል ሲሉ ቅሬታቸውን ሲገልጹ የቆዩ ነዋሪዎች መንግስት ...
Read More »በአዲስ አበባ የተከሰተውን አደጋ አስመልክቶ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች የሃዘን መግለጫ አወጡ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ላይ በደረሰው አደጋ የሃይማኖት ተቋማትና የፖለቲካ ድርጅቶች መግለጫ በማውጣት ሃዘናቸውን ገለጹ። በውጭ አገር የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በምክትል ዋና ጸሃፊው በአቡኑ ሚካዔል ስም ባወጣው መግለጫ፣ ለሞቱን ሃዘኑን ገልጾ፣ ለቤተሰብ መጽናናንትን ተመኝቷል። ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሞቱትን በጸሎት እንዲያስቡና ለሟች ቤተሰቦች ደግሞ ድጋፍን እንድያደርጉ ጥሪ አቅርቧል። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ የአፋር ...
Read More »የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንዲቀጥል ተወሰነ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተወሰኑ ማሻሻያዎች ተደርገውበት እንዲቀጥል ተወሰነ። የጸጥታ ሃይሎች ያለ-ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በጠረጠሯቸው መኖሪያ ቤቶች ላይ ሲያካሄዱ የቆዩት ፍተሻና ብርበራ በአዲሱ ማሻሻያ መነሳቱን ሮይተርስ የመንግስት ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። ህጉ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን አካትቶ አንዲቀጥል ቢወሰንም ለአዋጁ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ አልተገለጸም። አመጽ ያነሳሳሉ የተባሉ የተለያዩ ጽሁፎችንና መልዕክቶችን ማዘጋጀትና ማሰራጨት ...
Read More »ለልማት ተነሺዎች ተመድቦ የነበረው 100 ሚሊዮን ብር ለግል ጥቅም መዋሉን አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገለጹ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ለልማት ተነሺዎች መድቦት የነበረው 100 ሚሊዮን ብር በአመራሮችና በጎሳ መሪዎች ለግል ጥቅም ውሏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ሃሙስ ለፓርላማ አባላት ገለጹ። በሃገሪቱ የተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለፓርላማው የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስሙን መጥቀስ ባልፈለጉት ክልል 100 ሚሊዮን ብር ለተነሺዎች እንዲደርስ ቢመደብም ለግል ጥቅም ውሏል ሲሉ አስታውቀዋል። አቶ ...
Read More »በጋምቤላ ክልል በሙርሌ ታጣቂዎች ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው
ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ድንበርን ዘልቀው በጋምቤላ ክልል ጥቃት የፈጸሙ የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የገደሏቸው ሰዎች ቁጥር 28 ደረሰ። ወደ 1ሺ አካባቢ የሚጠጉ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በክልሉ ጎግ እና ጆር ተብለው በሚጠሩ አካባቢዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናቶች በፈጸሙት በዚሁ ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ህጻናት ቁጥርም 43 መሆኑን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ ታይምስ ጋዜጣ የክልሉ ቃል አቀባይ ቶል ቻኒን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በአካባቢው በተፈጸመው ...
Read More »ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ማሻሻያ አድርገውበት በድጋሚ በስድስት ሃገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እገዳ በፌዴራል ዳኞች ታገደ
ኢሳት ( መጋቢት 7 ፥ 2009) የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ማሻሻያ አድርገውበት በድጋሚ በስድስት ሃገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እገዳ ለሁለተኛ ጊዜ በፌዴራል ዳኞች ታገደ። ፕሬዚደንቱ ሃሙስ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ያወጡትን የጉዞ እገዳ የሜሪላንድና የሃዋይ ግዛቶች የፌደራል ዳኞች ውድቅ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፈውበታል። ፕሬዚደንቱ በድጋሚ ያስታወቁት ደንብ ሃገሪቱን ከሽብር ጥቃት ለመታደርግ ነው ቢሉም የሁለቱ ግዛቶች ዳኞች እገዳው አስተማማኝ አለመሆኑን እና አንድን ...
Read More »የጎንደር ፖሊስ አዛዥና የኮማንድ ፖስቱ አባል ታሰሩ
ኢሳት (መጋቢት 7 ፥ 2009) የጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ እና የኮማንድ ፖስቱ አባል ታሰሩ። የጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር አሰፋ ሹሜ ረቡዕ መጋቢት 6 ፥ 2009 መታሰራቸው ቢረጋገጥም፣ ስለታሰሩበት ምክንያት የታወቀ ነገር የለም። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀበት ጊዜ ጀምሮ በዚህ ኮማንድ ፖስት ስር መቀጠላቸው የተገለጸው ኮማንደር አሰፋ ሹሜ፣ ረቡዕ ከስራና ስልጣናቸው ተነስተው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ ...
Read More »የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰራተኞች በቆሼ ለደረሰው አደጋ መስተዳድሩን ተጠያቂ አደረጉ
መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ ቆሼ ተብሎ በሚታወቀው የቆሻሻ መጣያ ስፍራ በመሙላቱ ምክንያት፣ ቆሻሻ መጣያ ስፍራውን በመዝጋት ወደ ታሪካዊ መናፈሻነት ለመቀየር እየሰራ መሆኑንና ሥራውም ከ80 በመቶ በላይ መጠናቀቁን ከአራት ዓመት በፊት በወቅቱ ከንቲባ በነበሩት በኩማ ደመቅሳ ሪፖርት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም፣ ባለፉት አራት ዓመታት ግን ቆሻሻ መድፊያውን በተግባር መዝጋት ባለመቻሉ የአሁኑ አደጋ መከሰቱን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ...
Read More »የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች ተጨማሪ ጥቃት መፈጸማቸውን ገለጹ
መጋቢት ፯ (ሰባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታጋዮቹ ለኢሳት እንደተናገሩት በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓም ጀምሮ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን፣ የዚሁ የዘመቻ አካል የሆነ ጥቃት በአምባጊዮርጊስ ከተማ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ከምሽቱ 6 ሰአት አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት የወረዳው እስር ቤት ከጥቅም ውጭ መሆኑን ተናግረዋል። አምባጊዮርጊስ የመከላከያ ሰራዊት እና የሚሊሺያ አባላት በብዛት የሚገኙበት ከተማ ሆኖ ሳለ ...
Read More »