የአስቴር ስዩም እና የንግስት ይርጋ የፍርድ ቤት ሂደት ከሚገባው በላይ እየተጓተተ ነው

መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ያለምንም ማስረጃ በሽብር ወንጀል ተከሰው በቃሊቲ ማጎሪያ ቤት የሚገኙት፥ አስቴር ስዩም እና ንግስት ይርጋ፥ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2009 ዓ.ም በልደታ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም አሁንም ሌላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስር ቤት ተመልሰዋል። አስቴር ስዩም እና ንግስት ይርጋ የቀረቡት አቶ ሄኖክ ከተባሉ የሕግ ጠበቃ ጋር ሲሆን፥ በንግስት ይርጋ የክስ መዝገብ አጠቃላይ የቀረቡት ስድስት ...

Read More »

20 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዚምባቡዌ ውስጥ ተያዙ

መጋቢት ፳ (ሃያ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቆራርጠው ወደ ግዛቴ ገብተዋል ያላቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መያዙን የዚምባቡዌ የድንበር ጠባቂ ፖሊስ አስታወቀ። ቁጥራቸው 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቶዮታ ፒካፕ መኪና ተጭነው ማትሳይ መንደር ውስጥ የተያዙ ሲሆን ወደ ዚምባቡዌ የሚያስገባ ማንነታቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ ሰነዶች አለመያዛቸውንም ፖሊስ አክሎ ገልጿል። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች እድሜያቸው ከ12 እስከ 18 የሚገመት ወጣቶች ሲሆኑ ከመሃከላቸው እንግሊዝኛ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተእስራዔላውያን ወደ እስራዔል ለማጓጓዝ የተገባው ቃል በድጋሚ መዘግየት አጋጠመው

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) በጎንደርና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራዔላውያን ወደ እስራዔል ለማጓጓዝ የተገባው ቃል በድጋሚ መዘግየት እንዳጋጠመው ተገለጸ። ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ጉብኝትን ያደረጉት የእስራዔሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ወደ 9ሺ አካባቢ ከሚጠጉት ቤተ እስራዔላዊያን መካከል የ1ሺ 3 መቶዎቹ ጉዞ በተያዘው አመት እንደሚጠናቀቅ የተቀሩትም በአምስት አመታት ውስጥ ተጠናቀው ወደ እስራዔል እንደሚገቡ ቃል መግባታቸው ይታወሳል። የቤተ-እስራዔላውያኑ ጉዞ ...

Read More »

የውጭ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራት ከታቀደው ገቢ 1 ቢሊዮን ብር ጉድለት አስመዘገበ

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ውጭ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራቶች ብቻ ሊያስገኝ ከታቀደው ገቢ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉድለት አስመዘገበ። ሃገሪቱ በተያዘው በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከውጭ ንግድ ዘርፍ 4.2 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት እቅድ የነበራት ቢሆንም፣ ሊገኝ የቻለው ግን 1.4 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ መሆኑን የንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፉት ስድስት ወራቶች የውጭ ንግድ ገቢው ከታቀደው በታች  ማስመዝገቡ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴውና ...

Read More »

በአራት ክልሎች በድርቅ የተጠቁት ህጻናትና በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ልዩ የምግብ እንክብካቤን የሚሹ መሆኑን ፋኦ (FAO) አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አራት ክልሎች በመባባስ ላይ ባለው አዲስ የድርቅ አደጋ በ192 ወረዳዎች በአንደኛ ደረጃ በመመደብ አፋጣኝ የምግብ አቅርቦት እንደሚፈልጉ አስታወቀ። በእነዚሁ ክልሎች የድርቁ አደጋ መልኩን እየቀየረ በመሄድ ላይ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ በአራቱ ክልሎች ስር በሚገኙ በርካታ ዞኖች ዕድሚያቸው ከአምስት አመት በታች የሆነ 198 ሺ ህጻናትና 120ሺ በእርግዝና ላይ ያሉ ሴቶች ልዩ የምግብ እንክብካቤን ...

Read More »

በቅርቡ በጎንደር በሚከበረው የከተሞች ቀን በክልሉ ያለውን ድባብ እንዲቀይር ብዓዴን ሃላፊነት ተሰጠው

  ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) በሚመጣው ሚያዚያ ወር በጎንደር የሚከበረው የከተሞች ቀን የክልሉን ገጽታም ሆነ በአጠቃላይ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን ድባብ እንዲቀይር ለብዓዴን ሃላፊነት ተሰጠው። ምክትል ጠ/ሚ/ ደመቀ መኮንን ሂደቱን በበላይነት እንዲያስተባብሩ መሾማቸውም ታውቋል። ዝግጅቱ እንደ መስቀልና ጥምቀት በዓላት የፈዘዘ እንዳይሆን ሁሉም የብዓዴን አባላት የክልሉ መንግስት በሙሉ አቅማቸው እንዲንቀሳቀሱም ከፌዴራል መንግስት መመሪያ መተላለፉን መረዳት ተችሏል። ከሚያዚያ 21 ቀን 2009 ጀመሮ ...

Read More »

ከኦነግ ጋር በመሆን የሽብር ተግባር ለመፈጸም ተንቀሳቅሰዋል በተባሉት ስዎች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የእስር ቅጣት አስተላለፈባቸው

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በመሆን የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ ውለዋል ተብለው ለእስር ከተዳረጉ 21 ሰዎች መካከል 16ቱ ከአራት እስከ 13 አመት በሚደርስ ፅኑ ዕስራት እንዲቀጡ ማክሰኞ ወሰነ። ተከሳሾቹ በአዲስ አበባና በሶስት የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ነዋሪዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ሁሉም ግለሰቦች የሃገሪቱን ህዝቦች አንድነት የማፈራረስና የኦሮሚያ ክልልን ከፌዴሬሽኑ የመገንጠል አላማ ይዘው ተንቀሳቅሰዋል ...

Read More »

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ለእስር ከተዳረጉት ውስጥ 5 ሺ የሚሆኑት ክስ ሊመሰርትባቸው መሆኑ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ መደረግን ተከትሎ ለእስር ከተዳረጉ ከ20ሺ በላይ ሰዎች መካከል አምስት ሺ የሚሆኑት ክስ ሊመሰርትባቸው መሆኑ ተገለጸ። በጥቅምት ወር በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ ለመቆጣጠር ተግባራዊ የተደረገውን ይህንኑ አዋጅ ምክንያት በማድረግ 26ሺ 130 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው እንደነበር የአዋጁን አፈጻጸም የሚከታተለው ኮማንድ ፖስት ይፋ አድርጓል። አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ለእስር ...

Read More »

በመገንባት ላይ ያሉና በቀጣይ የሚገነቡ የባቡር መስመሮች ከግንባታ እስከ ማስተዳደር ያለው ስራ ለውጭ ሃገር ኩባንያ እንዲሰጥ መንግስት ወሰነ

ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2009) የኢትዮጵያ መንግስት ያጋጠመውን የፋይናንስ የብድር አቅርቦት ችግር ተከትሎ በመገንባት ላይ ያሉና በቀጣይ የሚገነቡ የባቡር መስመሮች ከግንባታ እስከ ማስተዳደር ያለው ስራ ለውጭ ሃገር ኩባንያ እንዲሰጥ ወሰነ። በዚሁ አዲስ ስምምነት መሰረትም የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የሞጆ-ሃዋሳ-አርባ ምንጭ-ሞያሌ የባቡር መስመር ግንባታ እና አስተዳደርን ለውጭ ሃገር ኩባንያ ለመስጠት የሚያስችል የመግባባቢያ ሰነድ መፈረሙን ሰኞ ይፋ አድርጓል። ኮርፖሬሽኑ የባቡር መስመር ግንባታዎችን ...

Read More »

ህዝባዊ ተቃውሞው የበጀት እጥረት ፈጥሮብናል ዋጋም አስከፍሎናል ሲሉ አመራሮች ተናገሩ

መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ተነስቶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ ወረዳዎች ስራ መስራት አቁመው ትኩረታቸውን ሁሉ ተቃውሞውን ወደ መከላከል አድርገው እንደነበረና ይህንን ተቃውሞ ለመቆጣጠር ለወረዳዎች የተበጀተውን በጀት በማጥፋታቸው ከፍተኛ የበጀት እጥረት መከሰቱን የተለያዩ አመራሮች ተናግረዋል። የፐብሊክ ሚኒስቴር ሃላፊዎች ከክልል አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት እንደተገለጸው፣ የክልሎች ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮዎች እስከ ወረዳ የሚደርሱ 31 ...

Read More »