ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየውን የነጋዴዎች አድማ ተከትሎ፣ ገዢው ፓርቲ “ችግሩን በውይይት እፈታለሁ” በማለት በየስብሰባዎች ቃል እየገባ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ለማግባባት ሲሞክር ከቆየ በሁዋላ ወደ በቀል እርምጃ መግባቱን ነጋዴዎች ይገልጻሉ። የሞጣ ከተማ ባለስልጣናት ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጉት ስብሰባዎች ለነጋዴዎች ጥያቄ አጥጋቢ መልስ እንደሚሰጡ ሲገልጹ ቢቆዩም፣ ዛሬ ለነጋዴዎች ያላቸውን ንቀትና ...
Read More »ደም አፋሳሽ ሆኖ የቀጠለውን የጉጂ ዞን ግጭት የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስነሱት ነዋሪዎች ተናገሩ
ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስከ 1 ሺ የሚጠጉ ቤቶች መቃጠላቸውን የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱን የጉጂ ዞን ባለስልጣናት እንዳስነሱት ይገልጻሉ። ኢሳት በተከታታይ ያቀረባቸው ዜናዎች የአንድን ወገን መረጃ ብቻ ማእከል ያደረገ ነው በማለት ቅሬታቸውንም አቅርበዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭቱ የጉጂ ዞን ባለስልጣናት በደቡብ ክልል ...
Read More »አቶ ዳንኤል ሺበሺ ነጻ ተባሉ ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከተፈቱ በሁዋላ ይግባኝ የተጠየቀባቸው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ም/ል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና የደቡብ ክልል ተወካይ በመሆን ሲያገልግሉ የነበሩት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ፍርድ ቤት ዛሬ ነጻ ያላቸው ሲሆን፣ ሌላው ይግባኝ የተጠየቀባቸው የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ “ ...
Read More »በግብር ጭማሪ የተነሳውን ተቃውሞና አድማ እንደቀጠለ ነው
በግብር ጭማሪ የተነሳውን ተቃውሞና አድማ እንደቀጠለ ነው (ኢሳት ዜና–ሐምሌ 20/2009)በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት በመላ ሀገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ለማስቆም የሃይል ርምጃን ብቸኛ አማራጭ ማድረጉ ይነገራል። በአዲስ አበባ በመርካቶ ባለፈው ሰኞ የተዘጉትን ሱቅና መደብሮች ለማስከፈት ከፖሊሶች በተጨማሪ የደህንነት ሃይሎች በየሱቆቹና መደብሮቹ በመዘዋወር ነጋዴውን ሲያስፈራሩ እንደነበር የኢሳት ዘጋቢ ከስፍራው ገልጿል። የነጋዴው ቅሬታ ሳይሰማ ጥያቄው ምላሽ ሳያገኝ በሃይል በማስፈራራት የተዘጉት ሱቆችና መደብሮች ...
Read More »ከእለታዊ ግብር ጋር በተያያዘ የተጀመረው የነጋዴዎች አድማ በምስራቅ ጎጃምና በምስራቅ ሃረርጌ ቀጥሎ ዋለ
ሐምሌ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገቢያችንንና ኑሮአችንን ያላገናዘበ የግምት ግብር ይቀየርልን በማለት ተቃውሞ ያሰሙ ነጋዴዎች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍል ላለፉት 2 ሳምንት ድርጅቶቻቸውን በመዝጋት ሲያደርጉ የነበረውን አድማ ዛሬም ቀጥለዋል። ለተከታታይ አምስት ቀናት አድማውን እያደረጉ ካሉት ከተሞች መካከል የምስራቅ ጎጃሟ ሞጣ አንዷ ስትሆን፣ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን እንዲከፍቱ ጉልበትን ጨምሮ የተለያዩ ማስፈፋሪያዎችን ተግባራዊ ቢያደርጉም ነጋዴዎች ...
Read More »በመከላከያ ላይ ሲደረግ የነበረው የሙስና ምርምራ መታፈኑ ታወቀ
ሐምሌ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት ውስጥ በመከላከያና በደህንነት ሃይሉ መካከል የተነሳውን የቆየ ልዩነት ተከትሎ የደህንነት ሃይሉ ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመተባበር በመከላከያ ውስጥ የተፈጸመውን ሙስና በማጣራት፣ የተወሰኑ ቡድኖችን ለመምታት የተደረገው ሙከራ ፣ ምርምራው እንዲታፈን መደረጉን ምንጮች ገለጹ። መረጃ የሰጡ የተለያዩ ሰዎች መታሰራቸውንም ለማወቅ ተችሎአል። በጄ/ል ሳሞራ የኑስ የሚመራው መከላከያና በጌታቸው አሰፋ የሚመራው የደህንነት መስሪያ ...
Read More »በአገር ሽማግሌ ስም መቀሌ ከሄዱት መካከል 4ቱ የተባረሩ የአርበኞች ግንቦት አባላት የነበሩ ናቸው
ሐምሌ ፳ ( ሃያ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የአማራ እና የትግራይን ህዝብ እናስታርቃለን በማለት ወደ መቀሌ ከተጓዙ፣ የአገር ሽማግሌ ስም ከተሰጣቸው ሰዎች መካከል አራቱ በአርበኞች ግንቦት7 ስር ተደራጅተው ሲሰሩ የነበሩና በሁዋላ ላይ ህወሃት በሰላይነት እንዲያገለግሉት እንደመለመላቸው ሲታወቅ የተባረሩ ናቸው። አቶ ታያቸው ጥሩነህ፣ አቶ ሞላ መኮንን፣ አሰማራው መኮንን እና ሻንቆ ሽባባው የተባሉትን በመድረክ ላይ ...
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ታሰሩ
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 20/2009)የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር መሆናቸውን ምርጫ ቦርድ ከወራት በፊት ያጸደቀላቸው አቶ የሺዋስ አሰፋ መታሰራቸው ታወቀ። አቶ የሺዋስ አሰፋ የታሰሩት በባህር ዳር ከተማ ሲሆን የአባላቶቻቸውን የፍርድ ሂደት ለመከታተል በሄዱበት መታሰራቸው ተመልክቷል። የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አበባ አካሉ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩት አቶ የሸዋስ የታሰሩት ትላንት ረቡእ ሲሆን የታሰሩበት ምክንያት ግን እስካሁን አልታወቀም። ነሐሴ 1 ቀን 2008 በባህርዳር ከተካሄደው ...
Read More »ለጣና ሃይቅ ህልውና ማጣት ምክንያት የሆኑ 8 አበይት ችግሮች መኖራቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 20/2009)ባለሙያው አቶ ማስተዋል እጅጉ እንደገለፁት የጣና ሐይቅ በውሃ አስተዳደር መርህ መሰረት አለመያዙ በህልውናው ላይ ትልቅ አደጋ ደቅኗል። በሀይቁ ላይም 8 ዋና ዋና የሚባሉ አብይ ችግሮች መኖራቸውንም ባለሙያው ይገልፃሉ። እነዚህም በደለል መሞላት፣ የባህር ሽሽ መሬት መጨመር፣ ውሃውን ማፍሰስ እና በተለያዩ ሰበቦች እንዲቀንስ ማድረግ፣ በተለይ በኬሚካሎች መበከል፣ እንዲሁም የባክቴሪያ መብዛት፣ እምቦጭን በመሳሰሉ አረሞች መወረር፣ ፍሳሽ ቆሻሻን መልቀቅ እና ...
Read More »በኢትዮጵያ ያለው መንግስት በሙስና የተዘፈቀ ጨካኝና የዘረፋ መጠኑም ድንበር የማይገታው ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና -ሐምሌ 20/2009) በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የካሊፎርኒያ ተወካይ የሆኑት ዳና ሮራባከር እንዳሉት እሳቸው በግል የሚያውቋቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን የመንግስት ደጋፊ ባለመሆናቸው ብቻ ንብረታቸው እንደተወረሰ አስታውሰው እንዲህ ያለ የሰብአዊ መብትን ቀርቶ የግል ንብረትን እንኳ የማያከብር አገዛዝ ከአሜሪካ መንግስት ጋር ወዳጅና ተባባሪ ለመሆን መሞከሩ በጣም ይገርመኛል ብለዋል። ባጭሩ አሉ የምክር ቤቱ አባል በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ፈላጭ ቆራጭና ለምንም ነገር ገደብ ...
Read More »