(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 25/2009)የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግንባር ኦብነግ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጠላት የሆነውን የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አገዛዝን ለማስወገድ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ። የህወሀት መንግስት ከዚህ በላይ በስልጣን ላይ ከቆየ ኢትዮጵያን እንደሶሪያና የመን የብጥብጥ ሀገር ሊያደርጋት ይችላል ሲል ኦብነግ አስጠንቅቋል። አንድ ሀገር አንድ ህዝብ ነን ልዩነታችንን ወደ ጎን በማድረግ የህወሃትን መንግስት ለማስወገድ በጋራ እንነሳ ብሏል ግንባሩ። አንድ ከፍተኛ አመራሩ ለህወሀት ...
Read More »አማራና ቅማንትን በጎጥ ለመከፋፈል የተጠነሰሰው ሴራ በአስቸኳይ እንዲቆም የጎንደር ህብረት አስጠነቀቀ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 25/2009)አማራና ቅማንትን በጎጥ ለመከፋፈል በትግራይ ሕወሃት ነጻ አውጭዎች የተጠነሰሰው ሴራ በአስቸኳይ እንዲቆም የጎንደር ህብረት አስጠነቀቀ። ሕብረቱ ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የጎንደር ሕዝብ አማራና ቅማንትን ለመከፋፈል መስከረም 7/2010 የታቀደውን ሕዝበ ውሳኔ በማክሸፍ መሬቱ ለትግራይ ከመተላለፉ በፊት አካባቢውን እንዲያድን ጥሪ አቅርቧል። ሕወሃት በራሱ ክልል የሚገኙትን የኩናማ፣የኢሮብና የአገው እንዲሁም የአፋር ጎሳዎችን ሳይከፋፍልና የሕዝበ ውሳኔ መብት ይሰጣቸው ሳይል የአማራና ቅማንትን ሕዝብ በመብት ...
Read More »በቁጥር 30 የሚሆኑ የወልቃይት ተወላጆች 24 ሰአታት በካቴና ታስረው በደል እንደሚፈጸምባቸው ተገለጸ
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 25/2009) ከሁመራና አካባቢዋ ተይዘው ወደ መቀሌ ወህኒ ቤት የተጋዙ በቁጥር 30 የሚሆኑ የወልቃይት ተወላጆች 24 ሰአታት በካቴና ታስረው በደል እንደሚፈጸምባቸው ተገለጸ። የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ እንዳስታወቁት ከመካከላቸው 6ቱ የደረሱበት አልታወቀም። ሰዎቹ ይረሸኑ አልያም ወደሌላ እስር ቤት ይወሰዱ የታወቀ ነገር አለመኖሩን አመልክተዋል። ከሁመራና አካባቢዋ የተያዙትና ወደ መቀሌ የተጋዙት የወልቃይት ተወላጆች ከሰኔ 17 2009 ጀምሮ 24 ሰአታት ...
Read More »ሶስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ከአርብ ጀምሮ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 25/2009)በኢትዮጵያ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ ያለውን የምግብ እህል እጥረት በተመለከተ ሶስት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ከአርብ ጀምሮ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው። ባለስልጣናቱ የአለም የምግብና የእርሻ ድርጅት/ፋኦ/ዳይሬክተር፣የአለም አቀፍ የግብርና ምርት ፈንድ ተጠሪና የአለም የምግብ ፕሮግራም ዋና ሃላፊ ናቸው። የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በሐገሪቱ ያለውን አሳሳቢ ድርቅ በተመለከተ ከኢትዮጵያው አገዛዝ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ለማወቅ ተችሏል። የአሜሪካ የእርዳታ ድርጅት ዩ ኤስ አይዲ ...
Read More »የአሜካዋ ሒዩስተን ከተማ በመልሶ ግንባታው ሒደት የኮንስትራክሽን ሰራተኞች እጥረት ሊገጥት ይችላል ተባለ
(ኢሳት ዜና–ነሀሴ 24/2009)ለ5 ቀናት ዶፍ ዝናብ የወረደባትና በ20 ትሪሊዮን ጋሎን ያህል ውሃ የተጥለቀለቀችው የአሜካዋ ሒዩስተን ከተማ በመልሶ ግንባታው ሒደት የኮንስትራክሽን ሰራተኞች እጥረት ሊገጥማት ይችላል ተባለ። ዝናቡም ከሂውስተን ወደ ሉዚያና መሻገሩም ተመልክቷል። በዚህ እጅግ ከፍተኛ በሆነው አደጋ በጎርፍ የተወሰዱ 6 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ 20 ሰዎች መሞታቸው ይፋ ሆኗል። እድሜያቸው ከ6 እስከ 16 አመት የሆነ 4 ልጆች በ80ዎቹ የእድሜ ክልል ከሚገኙት ...
Read More »የኢትዮጵያ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ መታገል ይኖርበታል ተባለ
(ኢሳት ዜና –ነሀሴ 24/2009) ኢትዮጵያ አደገኛ በሆነ አቅጣጫ እየተወሰደች በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ በስልጣን ላይ ያለውን ስርዓት ለማስወገድ መታገል ይኖርበታል ሲል የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ገለጸ። የኢትዮጵያ ለም መሬቶችን ለሱዳን ለ10ዓመታት በውሰት ለመስጠት በድብቅ ከስምምነት መደረሱን በመጥቀስ ጥሪ ያደረገው የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ፡ የህወሀት መንግስት የጥፋት ግስጋሴ በአስቸኳይ ካልተገታ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው ብሏል። የታላቋን ትግራይ ...
Read More »የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አንድ ከፍተኛ አመራር ለኢትዮጵያ ተላልፈው ተሰጡ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 24/2009) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር አንድ ከፍተኛ አመራር በሶማሊያ መንግስት አማካኝነት ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸው ታወቀ። የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር እንዳስታወቀው ሶማሊያ ውስጥ ተይዘው ለህወሃት መንግስት ተላልፈው የተሰጡት የግንባሩ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አብዱልከሪም ሼክ ሙሴ ናቸው። ላለፉት ሶስት አመታት ነዋሪነታቸውን በሞቃዲሾ አድርገው የቆዩት አብዱከሪም ሼህ ሙሴ ባለፈው ሳምንት ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ ችግር ወደ ሶማሊያ ማእከላዊ ግዛት ጋልሙዲግ መሔዳቸውንና ...
Read More »ህወሃት አዲሱን አመት በተለየ መልኩ አከብራለሁ አለ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 24/2009) ለ25 አመታት ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ አካባቢያዊ ስሜትን ሲያቀነቅን የነበረው ስልጣን ላይ ያለው ቡድን ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ መጪውን የኢትዮጵያ አዲስ አመት ከወትሮው በተለየ አከብራለሁ ማለቱ ተሰማ። ከነሐሴ 24 እስከ ጳጉሜ 5/2009 በተዘረጋለት መርሃ ግብር መሰረት የሚከበረው በአል የመንግስት ሰራተኞች የባህል ልብስ እንዲለብሱም ያስገድዳል። ለ10 ቀናት የሚከበረው ይሄ በአል በየቀኑ የሚቀያየሩ መሪ ቃሎችንም አስቀምጧል። ምክንያቱ ግልጽ ባልሆነ መንገድ መጪውን ...
Read More »በጣሊያን መዲና በኢትዮጵያውያንና በጣሊያን ፖሊስ መካከል በተፈጠረው ግጭት የተጎዳ ኢትዮጵያዊ የለም መባሉ በርካቶችን ማስቆጣቱ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 23/2009) በጣሊያን መዲና በኢትዮጵያውያንና በጣሊያን ፖሊስ መካከል በተፈጠረው ግጭት የተጎዳ ኢትዮጵያዊ የለም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ በርካቶችን ማስቆጣቱ ታወቀ። በሮም የሚገኘው ኤምባሲው በቦታው ተገኝቼ ባደረኩት ማጣራት አራት ኢትዮጵያውያን ከህንፃው በሰላማዊ መንገድ ሲወጡ አይቻለሁ በማለት የሰጠው ምስክርነትም በርካቶችን አስገርሟል። ከዚህ ውጭ የሌሎች አፍሪካውያን አገራት እንጂ የጉዞ ሰነድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቦታው አልነበሩም ሲል የሰጠውን ምስክርነትም ከእውነት የራቀ ሲሉ ...
Read More »በአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ታሪፍ ላይ ጭማሪ ሊደረግ ነው
(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 23/2009) በአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ታሪፍ እንዲጨምር የአዲስ አበባ ምክር ቤት ወሰነ። በምግብ እህሎችና በተለያዩ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየተመዘገበ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት በውሃ ላይ የታሪፍ ጭማሪ መደረጉ በከተማዋ ነዋሪ ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረውም እየተገለጸ ይገኛል። የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ውሃውን ከማመርትበት የምሸጥበት ዋጋ ያነሰ በመሆኑ ለመጨመር ተገድጃለሁ ማለቱም ተመልክቷል። አንድ ሜትር ኪዩብ ውሃ ወይንም አንድ ...
Read More »