(ኢሳት ዜና–ሕዳር 1/2010)የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አመራሮች ለራሳቸው አካባቢ የማድላትና ሁሉንም ሕዝብ እኩል ያለማየት ችግር አለባቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ይህንኑ ችግር ለማስወገድ በኦሮሚያና አማራ ክልል መካከል የተካሄደው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ በሌሎች ክልሎችም በቅርቡ ተግባራዊ ይደረጋል። የኢህአዴግ ማዕከላዊ አሰራር ተዳክሞ አባል ድርጅቶች መርህ እየጣሱ ነው መባሉም ትክክል አይደለም ሲሉ ገልጸዋል። ...
Read More »የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ይፈታል የተባለ አዲስ እቅድ አወጣ
(ኢሳት ዜና–ህዳር 1/2010)በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተካተቱበት የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሀገሪቱ ያሉትን ችግሮች ይፈታል የተባለ አዲስ እቅድ አወጣ። የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ያወጣውን አዲስ እቅድ በተመለከተ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የጸጥታ ሃይሎች ከእንግዲህ የሚካሄዱ ህገ ወጥ ሰልፎችን ለማስቆም እንዲችሉ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። እስካሁን ለጠፋ ህይወትና ንብረት የሚጠየቁና ለሕግ የሚቀርቡ አካላት እንደሚኖሩም አቶ ሲራጅ ...
Read More »ፍልሰተኞችን ለመርዳት የሚመደበው በጀት በሕወሃት ደህንነት መስሪያ ቤት እየተመዘበረ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 30/2010)በኢትዮጵያ ያሉና አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ፍልሰተኞችን ለመርዳት የተባበሩት መንግስታት የሚመድበው በጀት በሕወሃት ደህንነት መስሪያ ቤት እየተመዘበረ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ይህው በጀት ግን በደህንነት መስሪያ ቤቱ እየተመዘበረ በየአመቱ ያልተወራረደ በሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር እየባከነ መሆኑን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ኮሚሽን በርካታ ተሽከርካሪዎች በደህንነት መስሪያ ቤቱ ለግድያና ለአፈና እንዲሁም ለእስር ከመዋላቸው ሌላ ለባለስልጣናት የግል ...
Read More »በሳውዲ አረቢያ ካላግባብ የባከነው ገንዘብ 100 ቢሊየን ዶላር መሆኑን ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 30/2010) በሳውዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለው ጸረ ሙስና ዘመቻ ምርመራ ካለአግባብ የባከነው ገንዘብ 100 ቢሊየን ዶላር መሆኑን አጋለጠ። በሌብነት ተጠርጥረው የተያዙት ሰዎች ቁጥርም 199 መድረሱን የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል። ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የተጀመረው ተጠርጣሪ ልኡላንን፣ሚኒስትሮችንና ነጋዴዎችን ኢላማ ያደረገው የጸረ ሙስናው ዘመቻው በ32 አመቱ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን የተመራ ነው። በዘመቻው ተጠርጥረው ከተያዙት ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑት ሼህ ...
Read More »በአቶ በረከት ስምኦን ንብረቶች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 30/2010)በቅርቡ ስልጣን በለቀቁት በአቶ በረከት ስምኦን ንብረቶች ላይ የተጀመረው የሙስና ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ከተገነባው ደብል ትሪ ሆቴል ጋር በተያያዘ የተጀመረው ምርመራ ሙሉ በሙሉ የሆቴሉ ግንባታ የገንዘቡ ምንጭ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን አረጋግጧል። ይህም የተፈጸመው በአቶ በረከት ስምኦን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርነት ግዜ እንደሆነ መረጋገጡን ምንጮቹ ጨምረው ገልጸዋል። በአቶ በረከት ስምኦን ...
Read More »በምስራቅ ሸዋ ጨፌ ዶንሶ ተቃውሞው ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 30/2010)በምስራቅ ሸዋ ጨፌ ዶንሶ ተቃውሞው ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። በርካታ የመንግስት ተቋማት በእሳት ቃጠሎ ወድመዋል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ህዝቡን ለማረጋጋት በመሞከር ላይ ናቸው። ሁኔዎች ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆኑ የሰጉ የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶችን እያነጋገሩ መሆኑ ተገልጿል። በምንጃር ሸንኮራ ዛሬ መንግስት የጠራው ስብሰባ በህዝብ ተቃውሞ መቋረጡን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በሌላ በኩል በመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ ማድረጋቸው ታውቋል። በዛሬው የጨፌ ዶንሳ ...
Read More »የዲቪ ቪዛ ሎተሪ መርሃ ግብር የሚሰረዝ ከሆነ ኢትዮጵያ፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ግብጽ ዋነኛ ተጎጂዎች ይሆናሉ ተባለ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዲቪ ቪዛ ሎተሪ መርሃ ግብር እንዲሰረዝ በጠየቁት መሰረት ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ በአፍሪካ ኢትዮጵያ፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ግብጽ ዋነኛ ተጎጂዎች ይሆናሉ ተባለ። እነዚህ ሀገራት በመርሃ ግብሩ መሰረት ብዙ ኮታ ከሚያገኙት ግንባር ቀደሞቹ መካከል መሆናቸውም ታውቋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጥያቄውን ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት አንድ የኡዝቤክስታን ተወላጅ ኒዮርክ ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 8 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ...
Read More »በምንጃር ሾንኮራ ህዝባዊ አመጽ ተቀሰቀሰ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010)በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሾንኮራ ህዝባዊ አመጽ ተቀሰቀሰ።–በጨፌ ዶንሳ ትላንት የጀመረው ተቃውሞም ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል። የምንጃር ሸንኮራ ህዝብም የቻይና ቺፑድ ፋብሪካን በማቃጠል ማውደሙ ተገልጿል። የአማራ ወጣቶችና የኦሮሞ ቄሮዎች በጋራ እየሰሩ መሆኑን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር ወገራ አንድ የሚሊሺያ ሃላፊ በነጻነት ሃይሎች ታፎኖ መወሰዱ ተሰምቷል። ምንጃር ሸንኮራ ህዝባዊ አመጹ የተጀመረው ዛሬ ነው። ለ15 ቀናት መብራት ያላገኘው ...
Read More »ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ የሌሎች ታሳሪዎች የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ ታገደ
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010)የሳውዲ አረቢያ መንግስት ባለፈው ቅዳሜ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ የሌሎች ታሳሪዎችን የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ አገደ። ከእስሩ ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ ለአደጋ የተጋለጠው የባለሀብቶቹ ንብረት 33 ቢሊየን ዶላር እንደሚገመትም ከብሉምበርግ ዘገባ መረዳት ተችሏል። የሼህ መሀመድ አላሙዲን ቃል አቀባይ ከብሉምበርግ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ርምጃው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ የተገደበና በሌሎች ሀገራት ያላቸውን ንብረት የማይመለከት መሆኑን ገልጸዋል። ...
Read More »ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር እንዲፈቱ አለምአቀፍ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በመካሄድ ላይ ነው
(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010)ኢትዮጵያዊው አለምአቀፍ የልብ ህክምና ባለሙያ ያላቸው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ ከእስር እንዲፈቱ አለምአቀፍ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ በመካሄድ ላይ መሆኑ ታወቀ። እስካሁንም በፊርማ ማሰባሰቡ ዘመቻ ከ112 ሺ በላይ ፊርማዎችን ማሰባሰብ መቻሉ ታውቋል። ለ40 አመታት በልብ ህክምናው ዘርፍ ከፍተኛ ልምድና እውቀት ያላቸው ኢትዮጵያዊው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በኢትዮጵያውያኑ 2000 ወደ ሀገራቸው በመግባት የልብ ህክምና መስጫ ተቋም አቋቁመው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ይታወሳል። ዶክተር ...
Read More »