ከ14ሺ በላይ ሕጻናት ከቤተሰቦቻቸው ጋር መለያየታቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 27/2010)   በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል በተፈጠረው ግጭት ከ14ሺ በላይ ሕጻናት ከቤተሰቦቻቸው መለያየታቸውን ዩኒሴፍ አስታወቀ። በሁለቱ ክልሎች በተፈጠረ ግጭት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉት ደግሞ ከ84 ሺ በላይ ሕጻናት መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት ይፋ አድርጓል። በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው ግጭት ካለፈው ታህሳስ ወዲህ ለመገመት የሚያስቸግር ቀውስ መፍጠሩን የዩኒሴፍ ሪፖርት ያመለክታል። እንደ ዩኒሴፍ ገለጻ በግጭቱ በተለይ ሕጻናትና እናቶች ...

Read More »

በወለጋ ሻምቡ አፈሳ እየተካሄደ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 27/2010) በወለጋ ሻምቡ በቅርቡ ከተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ አፈሳ እየተካሄደ መሆኑን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አስታወቀ። ከትላንት ምሽት ጀምሮ በርካታ የሻምቡ ነዋሪዎች ታፍሰው ተወስደዋል። በተያያዘ ዜና በምዕራብ ሸዋ ሻሸመኔ አካባቢም ግጭት መፈጠሩ ታውቋል። በሀረሪ ክልል ኤረር ወረዳ የፌደራል ፖሊስ አንድ አርሶአደር መግደሉን ተከትሎ ውጥረት መንገሱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል። ባለፈው እሁድ በሻምቡ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ለኢሕአዴግ የቅዳሜው መግለጫ ...

Read More »

እየተወሰደ ያለው ርምጃ በውጭ ግንኙነቱ ላይ ትልቅ ፋይዳ አለው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 27/2010) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየወሰደ ያለው ርምጃ በውጭ ግንኙነቱ ላይ ትልቅ ፋይዳ አለው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ እንዳለው የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ይፈታሉ መባሉ ግን በውጭ መንግስታት ተጽእኖ አይደለም ሲል አስተባብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም እንዳሉት የሀገሪቱ የደህንነት ምንጭ ከውስጥ ጥንካሬ የሚመነጭ ነው። ሆኖም የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተወሰደ ...

Read More »

እስረኞቹን ለመልቀቅ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 27/2010) በኢትዮጵያ ወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ፖለቲከኞችን ለመፍታት በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ እስረኞቹን ለመልቀቅ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን ለስርአቱ ቅርበት ያላቸው መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። አንዳንድ የሕወሃት ደጋፊዎች እስረኞቹን ለመፍታት የተደረሰው ስምምነትን በመቃወም ላይ መሆናቸውን ሰምተናል። የሕወሃት መሪዎችም የተወሰኑ የፖለቲካ እስረኞች እንዳይፈቱ በመከላከል ላይ መሆናቸውን ምንጮች ገለጸዋል። የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ 18 ቀናት ያህል ባደረገው ስብሰባ እንደተወሰነ ...

Read More »

የሰላም ባስ አውቶብስ በህዝብ ተቃውሞ እንዳይንቀሳቀስ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በሰሜን ሸዋ አጣዬ የሰላም ባስ አውቶብስ በህዝብ ተቃውሞ እንዳይንቀሳቀስ ተደረገ። ከትላንት በስቲያ የሆነው ዛሬም ድረስ አልበረደም። የአጣዬን ከተማ መሃል ለመሃል የሚከፍለው ድልድይ ላይ የተጀመረው ተቃውሞ ሰፍቶ በፌደራል ፖሊስና በታጠቁ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እንደተካሄደ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። መነሻው ድልድዩን ሊያቋርጥ የተቃረበን የሰላም ባስ አውቶብስን ነዋሪው በማስቆሙ ነው። ምክንያቱ ደግሞ የህዝብ ሀብት ተዘርፎ የተመሰረተው የትግራይ መልሶ ማቋቋሚያ ...

Read More »

በትራምፕና በቤተሰቦቻቸው ዙሪያ የተፈጸሙ የተለያዩ ቅሌቶችን አንድ መጽሀፍ አጋለጠ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በአንድ ጋዜጠኛ ተጽፎ በቅርቡ ለገበያ የሚቀርበው መጽሀፍ በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና በቤተሰቦቻቸው ዙሪያ የተፈጸሙ የተለያዩ ቅሌቶችን አጋለጠ። መጽሀፉ የተለያዩ ሚስጥሮችን ማጋለጡ ቀድሞውንም በቀውስ የተሞላውን ኋይት ሀውስ የበለጠ ነዳጅ ቸልሶበታል። መጽሀፉ ዋና መነጋገሪያ ከሆነባቸው ጉዳዮች አንዱ የቀድሞው የኋይት ሀውስ ዋና ዕቅድ ነዳፊ ስቲቭ ባነን በሰኔ ወር 2016 በትራምፕ ልጅና በሩሲያ መንግስት ሰዎች መካከል በትራምፕ ህንጻ ውስጥ የተደረገው ውይይት ...

Read More »

ኢብራሂም ሻፊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ፣መምህርና የፖለቲካ ጉዳዮች ጸሐፊ ኢብራሂም ሻፊ በስደት በሚኖርባት ኬኒያ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። በሌላ በኩል አንጋፋው የህክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር ዕደማርያም ጸጋ ተሻለ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ኢብሮ በአጭሩ የሚጠራበት ስሙ ነው። መምህር ሆኖ አገልግሏል። የስፖርት ጋዜጠኝነቱ በሰፊው ይነሳለታል። የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ትንተናዎችም ይታወቃል። በሰብዓዊ መብቶች መከበር ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግም አስተዋጽኦው የጎላ ...

Read More »

አዲስ የጣራ ክዳን ፋብሪካ ሊገነባ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) የሕወሃት ንብረት የሆነው ኢፈርት ከሁለት ኩባንያዎች ጋር በፈጠረው የሶስትዮሽ ግንኙነት አዲስ የጣራ ክዳን ፋብሪካ 2 ቢሊየን በሚጠጋ ብር ሊገነባ ነው። የኢፈርት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አዜብ መስፍን ስምምነቱን ከሲንጋፖሩ ኩባንያ ኩስቶና ፈርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ከተባሉ ኩባንያዎች ጋር ተፈራርመዋል። ፋብሪካውን በመቀሌ ወይም አቤዲ በተባሉ የትግራይ አካባቢዎች ለመገንባት የቦታ መረጣ እየተካሄደ ይገኛል። በስምምነቱ መሰረት መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከሁለቱ ኩባንያዎች ጋር ...

Read More »

በመንግስት የተሰጠው መግለጫ ሲሰረዝና ሲደለዝ ዋለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት የሚገኙ ፖለቲከኞችና ሌሎች እስረኞች ለሀገራዊ መግባባት ሲባል እንዲፈቱ ተወስኗል በሚል በመንግስት የተሰጠው መግለጫ በመንግስት ሲሰረዝና ሲደለዝ መዋሉ ታወቀ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ማህበራዊ ገጽ ላይ ሰባት ጊዜ እየተሰረዘና እየታረመ መጻፉ ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም የመንግስት መግለጫን ተከትሎ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና ሌሎች ወገኖች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰቆቃው ...

Read More »

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 26/2010) በአዲስ አበባ በሳህሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዳግም ግጭት ተቀሰቀ። በቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ የድረሱልን የደወል ድምጽ በመሰማቱ በርካታ ምዕመናን በአካባቢው ተገኝተው የተቃውሞ ድምጽ ማሰማታቸው ታውቋል። ለተቃውሞው ምክንያት የሆነው የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪ ድብደባ ደርሶባቸው እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ተመልሰው ወደ መቅደስ እገባለሁ በማለታቸው ነው። ቤተክርስቲያኗ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት መከበቧም ተነግሯል። በሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ምዝበራ እየተፈጸመ ነው በመባሉ ...

Read More »