(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2010) ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በጠላትነት የሚተያዩት ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በአንድ ባንዲራ በአለም አቀፍ የኦሎምፒክ ውድድር ለመሳተፍ መስማማታቸው ተዘገበ። በአንዲት ኮሪያ ስም ሁለቱ ሀገራት ለመወዳደር መስማማታቸውን በሰበር ዜና የዘገበው የብሪታኒያው የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ በቀጣዩ ወር በሚካሄደው የክረምት ኦሎምፒክ ስምምነታቸው ተግባራዊ እንደሚሆንም አመልክቷል። ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ በክረምቱ ኦሎምፒክ በአንድ ኮሪያ ስም በጋራ ባንዲራ ለመወዳደር ከመስማማታቸው ባሻገር በአንዳንድ ውድድሮች የጋራ ...
Read More »የተበላሸ ብድር ያላቸው ድርጅቶች ታወቁ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2010) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብዛት የተበላሸ ብድር ያላቸው ድርጅቶች ሰፋፊ የእርሻ ፕሮጀክቶችና የቱርክ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የሆነው አይካ አዲስ መሆኑን አስታወቀ። በባንኩ ከፍተኛ የተበላሸ ብድር እንዳለበት የሚታወቀውና የህወሃት ንብረት የሆነው ኤፈርት ግን በዚህ ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም። የህወሃት ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና የባንኩን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ሃይለየሱስን ጠቅሶ እንደዘገበው የልማት ባንክ በተለያዩ ዘርፎች ብድር ሰጥቶ አደጋ ውስጥ ያለውን ...
Read More »የትግራይ ህዝብ መካስ አለበት ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2010) የትግራይ ህዝብ ከማንም በላይ ውድ ዋጋ የከፈለ በመሆኑ መካስ አለበት ሲሉ የህወሃት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ቃል አቀባይ ገለጹ። ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ የህወሀትን 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት የትግራይን ህዝብ ለመካስ አዲሱ አመራር ቆርጦ ተነስቷል። በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል ሰፊ የልማትና የእድገት ልዩነት ፖለቲካዊ ቀውስ በፈጠረበት በዚህን ወቅት የአቶ ጌታቸው ረዳ መግለጫ ...
Read More »የስርአቱ ሰዎች ድሆች የእነሱን ሐጥያት እንዲሸከሙ እያደረጉ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2010) በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ 31ኛ ተከሳሽ አቶ ጌታቸር እሸቴ የስርአቱ ሰዎች እየገደሉና እየረሸኑ ድሆች የእነሱን ሐጥያት እንዲሸከሙ እየተደረጉ ነው ሲሉ በጻፉት ድብዳቤ አስታወቁ። አቶ ጌታቸር እሸቴ በ30 ደቂቃ ውስጥም 9 ሰዎችን ግድለሀል ተብዬ በሀሰት ውንጀላ መከሰሴን ዓለም ይወቅልኝ በማለት ተናግረዋል። ነሐሴ 28/2008 የቂሊንጦ እስር ቤት በእሳት በጋየበት ወቅት በተደረገ ተኩስ 23 እስረኞች መገደላቸውን የህወሃት መንግስት ...
Read More »ዶክተር መረራ ጉዲና ከወህኒ ወጡ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2010) የኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ ከወህኒ ወጡ። ከሳቸው ሌላ በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ግን አልተፈቱም። ዶክተር መረራ እንዲፈቱ ተወስኖ ክሱ ከተቋረጠ በኋላ የመንግስት ቃል አቀባዩ ዶክተር ነገሬ ሌንጮ ትላንት በሰጡት መግልጫ የዶክተር መረራ ጉዲና ጉዳይ ውሳኔ የሚያገኘው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ነው ማለታቸው ይታወሳል። የህወሃት ንብረት የሆነው ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልም በተመሳሳይ አይፈቱም የሚል ዘገባ ...
Read More »ግብጽ ከሱዳንም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አልፈልግም አለች
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) የግብጹ ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብዱልፈታህ አልሲሲ ከሱዳንም ሆነ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት አንፈግም አሉ። በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረት እንዲረግብ ፍላጎታችን ነው ያሉት ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ሀገራቸው በማንም ሀገር ጉዳይ ጣልቃ የመግባት ፍላጎት እንደሌላትም በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። የሱዳን መንግስት በበኩሉ በግብጽና በኤርትራ መንግስት ላይ ያቀረበውን ክስ በመሳብ ጉዳዩን ከሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ጋር አያይዞታል። የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከሀገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ትላንት ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገደደ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ሰኞ ረፋድ ላይ ከዋሽንግተን ዲሲ ወደ ኢትዮጵያ ይበር የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በተፈጠረበት የቴክኒክ ችግር በዳላስ አይሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ መገደዱ ተሰማ። በተሳፋሪውም ሆነ በአውሮፕላኑ ሰራተኞች ላይ ምንም ጉዳት ሳይደርስ አውሮፕላኑ በሰላም ማረፉም ታውቋል። ተሳፋሪዎቹን ሆቴል ያሳደረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬ የአውሮፕላን ጥገናውን ጨርሶ ጉዞውን ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል። የበረራ ቁጥር 501 ቦይንግ 777-300 የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2018 ተሸላሚ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ታዋቂው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ሁለት አለም አቀፍ ተቋማት በጋራ የ2018 ተሸላሚ አድርገው መረጡት። የሽልማት ስነስርአቱ ከነገ በስትያ በኔዘርላንድ ዘሄግ በከፍተኛ ስነስርአት የሚካሄድ መሆኑ ታውቋል። በስነስርአቱ ላይ የከተማዋ ከንቲባ እንደሚገኙም ከወጣው መርሃ ግብር መረዳት ተችሏል። በአለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ አክብሮት እየተቸረውና ሽልማት እየተጎናጸፈ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በአሁኑ ወቅት በቃሊቲ ወህኒ ቤት የ18 አመታት እስር ተፈርዶበት ይገኛል። ኦክስፋም ...
Read More »ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ድርጅት ራስ ምታት ሆነዋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ድርጅት ራስ ምታት ሆነው መቀጠላቸውን ዘገባዎች አመለከቱ። የቀድሞውን የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን የአለም ጤና ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር በሚል በመሾማቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውሳኔውን መሰረዛቸው ይታወሳል። አሁን ደግሞ ምንም እውቅናና ችሎታ የሌላቸውን ሩሲያዊ ባለስልጣን የአለም ጤና ድርጅት የሳምባ በሽታ ፕሮግራምን እንዲመሩ በመወሰናቸው ከቀድሞው በባሰ እየተብጠለጠሉ መሆኑ ታውቋል። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ለአለም ጤና ...
Read More »ህወሃት በክልሉና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያየ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2010) ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ህወሃት በክልሉና በሀገራዊ ጉዳዮች እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ። ሀገሪቱን ስጋት ላይ የጣሉ አመራሮች ላይም ርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቋል። የህወሀት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የትግራይ ህዝብ በአመራሮቹ ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርበት ተደርጓል ሲሉም በስም ያልጠቀሷቸውን አመራሮች ተጠያቂ አድርገዋል። የህወሀት 7ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ከተጀመረ አንድ ሳምንቱን አጠናቋል። ከመላው ዓለም የህወሃት ደጋፊዎችና ...
Read More »