ኢሕአዴግ የመበስበስ ችግር ገጥሞታል

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ለተፈጠረው ቀውስ  ዋናው መንስኤ የስልጣን አተያይ እና የድርጅት የመበስበስ ችግር መሆኑን አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ገለጹ። ኢሕአዴግ ከግንባርነት ወጥቶ ከብሄር ድርጅትነት ወደ ሃገራዊ ፓርቲነት ለመቀየር በቀጣዩ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚቀርብም ገልጸዋል። የኢሕአዴግ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እንዳሉት ግንባሩ ወደ ውህድ ፓርቲነት ከመቀየሩ ሌላ የአጋር ድርጅቶችም ጉዳይ የዚሁ አካል እንዲሆኑ ታሳቢ እየተደረገ ነው። ...

Read More »

የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በውጥረት መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010)የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ውጥረት በተመላበት ሁኔታ መቀጠሉ ተሰማ። አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የመምረጡ ሂደት በፈጠረው ውዝግብ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰየሙ ሒደት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ሃሳብ መቅረቡም ተመልክቷል። በሕወሃት ሰዎች እንዲሁም ከብአዴን አቶ በረከትና ተከታዮቻቸው ከህወሃት ጎን በመሰለፍ ኦሕዴድን በማጥቃት ላይ መሆናቸውም ተመልክቷል። እሁድ የተጀመረውና የድርጅቱን ሊቀመንበር መምረጥን በዋናነት አጀንዳ ያደረገው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ እንደተጠበቀው የድርጅቱን ሊቀመንበር ...

Read More »

በሞያሌ የተፈጸመው ጭፍጨፋ በስህተት አይደለም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010)በሞያሌ የተፈጸመውን ጭፍጭፋ በስህተት ነው በሚል በኮማንድ ፖስቱ የተሰጠውን መግለጫ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል የኦሮሚያ ክልል መንግስት አስታወቀ። በሞያሌ የጦር ወንጀል ተፈጽሟል ሲልም ጠንካራ አቋም ይዟል። በክልሉ ፍትህ ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ ለጀርመን ድምጽ ሬዲዮ እንደተናገሩት የተፈጸመው ግድያ በስህተት እንዳልሆነ መረጃ አለ። ድርጊቱን የፈጸሙት ብቻ ሳይሆኑ የመከላከያና የኮማንድ ፖስቱ አዛዦች ጭምር በህግ ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎሉ ዘመቻ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 4/2010) በቄሮዎች የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ። ለአንድ ሳምንት የተጠራው ይህ ዘመቻ ነዳጅ የጫኑ ቦቴ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ፣ በሀገር ውስጥም ከአንድ አካባቢ ወደሌላ እንዳያመላልሱ የሚያደርግ ነው። ዛሬ ዘመቻው ሲጀምር አዲስ አበባ ተጽዕኖው ጎልቶ ከታየባቸው አካባቢዎች የሚጠቀስ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በርካታ ማደያዎች ነዳጅ የላቸውም። በየቦታው ነዳጅ አመላላሽ ቦቴዎች ቆመው እንደሚታዩ የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሰሜን ኢትዮጵያ ...

Read More »

የባንግላዴሽ አይሮፕላን በካታማንዱ ተከሰከሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) ንብረትነቱ የባንግላዴሽ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን በኔፓል መዲና ካታማንዱ ተከሰከሰ። በትንሹ 40 ያህል መንገደኞችና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ሕይወታቸው አልፏል። አውሮፕላኑ የተከሰከሰው በማረፍ ላይ እያለ መሆኑም ታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ትላንት ምሽት በኒዮርክ ከተማ አንድ ሔሊኮፕተር ተከስክሶ 5 ሰዎች ሞተዋል። ንብረትነቱ የባንግላዴሽ አየር መንገድ የሆነ ቦባርዲየር ዳሽ ኤይት የበረራ ቁጥር ቢኤስ 211 የሆነው አውሮፕላን ከባንግላዴሽ ዋና ከተማ ዳካ መነሳቱንም ...

Read More »

18 የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2018) በአማራ ሕዝብ ስም የተደራጁ 18 የፖለቲካና የሲቪክ ተቋማት በጋራ ተደጋግፎ ለመስራትና በተቀናጀ መልኩ ለመታገል መስማማታቸውን ገለጹ። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግም የአማራ ድርጅቶች አመራር ሰጭ አካል እንዲቋቋም በሜሪላንድ ሲሊቨር ስፕሪንግ ከየካቲት 30 እስከ መጋቢት 2 /2010 ባካሄዱት ዝግ ስብሰባ መወሰናቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል። በመግለጫው እንደተመለከተው የአማራ ሕዝብ ለሃገሩ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ውለታ የከፈለ ቢሆንም በጨቋኝነት ተፈርጆ ከፍተኛ በደልና ግፍ ...

Read More »

በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት ሰዎች የፍርድ ውሳኔ ተላለፈ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱት የ38ቱ ሰዎች የፍርድ ውሳኔ ለሌላ ጊዜ ተላለፈ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ለሌላ ጊዜ ያስተላለፈው በስራ መብዛት እና ሰንዶችን መርምሬ ባለመጨረሴ ነው ብሏል። በእነ ማስረሻ ሰጤ መዝገብ ዶክተር ፍቅሩ ማሩን ጨምሮ 38 ተከሳሾች በፍርድቤቱ ቀነ ቀጠሮ መራዘም ያላቸውን ቅሬታ መግለጻቸው ተነግሯል። በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ የተከሰሱ ሰዎችን ...

Read More »

የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል የታቀደው ዘመቻ ነገ ይጀመራል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በቄሮ የተጠራውና የነዳጅ አቅርቦትን ለማስተጓጎል የታቀደው ዘመቻ ከነገ ጀምሮ እንደሚካሄድ ተገለጸ። ለአንድ ሳምንት በሚካሄደው በዚሁ ዘመቻ ቦቴዎች ከውጭ ሃገር ነዳጅ ጭነው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ይደረጋል። በሃገር ውስጥም ነዳጅ ጭነው ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ርምጃ ይወሰድባቸዋል ተብሏል። ዘመቻው የሚጀመረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ በርካታ ሰዎች በመገደላቸው ነው። በቄሮ የተጠራው የነዳጅ አቅርቦትን የማስተጓጎል ዘመቻ ከነገ ጀምሮ ...

Read More »

ወደ ኬንያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 50 ሺህ ደረሰ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 3/2010) በሞያሌ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በመሸሽ ኬኒያ የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 50 ሺህ መድረሱ ተገለጸ። የአጋዚ ወታደሮች የሚፈጽሙት ግድያም ቀጥሏል። ወደ ኬኒያ በሽሽት ላይ በነበሩ የሞያሌ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ትላንት ተኩስ የከፈተው የአጋዚ ሃይል 2 ሰዎች መግደሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በሌላ በኩል የሞያሌው ጭፍጨፋ በስህተት የተፈጸመ ነው የሚለው የአገዛዙ መግለጫ ቁጣን ቀስቅሷል። ቅዳሜ  ለሞያሌ ነዋሪዎች ጥሩ ቀን አልነበረም። በጠዋት ...

Read More »

በሞያሌ ከተማ ዛሬም ግድያ አለመቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በሞያሌ ከተማ ዛሬም ግድያ አለመቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 03 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ቅዳሜ በሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከ13 ሰዎች በላይ መግደላቸውን ተከትሎ ግድያውና ውጥረቱ አሁንም ድረስ ያለ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ትናንት ምሽት አንድ የኮንሶ ብሄረሰብ ተወላጅ ሌሊት ላይ በ10 ጥይቶች ተደብድቦ ተገድሎአል። አንድ የምዕራብ ጉጂ አካባቢ ተወላጅ የሆነ ወጣት ደግሞ በ 2 ጥይቶች ተመትቶ ቆስሏል። ...

Read More »