ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሆላንድ ጉዞው ቢስተጓጎልም በመጨረሻ በግብዛ ቦታው ላይ እንደሚገኝ ታወቀ (ኢሳት ዜና ሚያዝያ 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሆላንድ አምስተርዳም በሚከበረው የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50 ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል የክብር እንግዳ ሆኖ የተጋበዘው ጋዜጠኛና የነጻነት ታጋይ እስክንድር ነጋ ለበረራ እየተዘጋጀ ሳለ ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ፓስፖርቱን ተነጥቆ ከሀገር እንዳይወጣ መከልከሉ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ነገ ቅዳሜ ቀትር ላይ ...
Read More »ስዋዚላንድ ስሟ ተቀየረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 12/2010) የስዋዚላንዱ ንጉስ የሃገራቸውን ስያሜ መቀየራቸው ተሰማ። ንጉስ ምስዋቲ የሃገራቸውን ስያሜ መቀየራቸው በብዙዎች ዘንድ ያለተለመደ ነው ብሎታል ቢቢሲ በዘገባው። የስዋዚላንድ ዜጎችም ከስም ለውጥ ይልቅ በኮኖሚ ጉዳዮች ላይ ቢያተኩሩ ይሻላል ሲሉ ርምጃውን ተቃውመዋል።ስዋዚላንድ አዲሱ መጠሪያዋ ኢስዋትኒ መሆኑም ታውቋል። ሳልሳዊ ንጉስ ምስዋቲ ሃገራቸው ስሟ መቀየሩን ያወጁት የስዋዚላንድ 50ኛ አመት የነጻነት በአል በተከበረበት ስነስርዓት ላይ ነው።ስዋዚላንድ ከዚህ በኋላ የምትጠራበት ስያሜም ኢስዋትኒ ...
Read More »እስክንድር ነጋ ፓስፖርቱ ተመለሰለት
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 12/2010) ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ አመት በአል ተጋብዞ ወደ ሆላንድ አምስተርዳም ሊያመራ ሲል በቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ የታገደው እስክንድር ነጋ ፓስፖርቱ ተመለሰለት። እስክንድር ነጋ በደህንነት ሰራተኞች ፓስፖርቱን ከተቀማ በኋላ ትላንት ወደ አምስተርዳም እንዳይበር ተደርጎ ነበር። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ፓስፖርቱ ተመልሶለት ነገ በሚከበረው 50ኛ አመት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል በአል እንዲሄድ አገዛዙ መፍቀዱን ለማወቅ ተችሏል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በሰብአዊ መብት ተከራካሪነቱና በዲሞክራሲ ...
Read More »በባህርዳር ነዋሪዎችን የማዋከብና የእስር ርምጃ እየቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 12/2010) በባህርዳር ከተማ ነዋሪዎችን የማዋከብና የእስር ርምጃ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ። ካለፉት 2 ቀናት ጀምሮ በተከታታይ በየመንገዱ በቀን ጨምሮ እየታፈኑ የሚታሰሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሕመድ በጣና ፎረም ስብሰባ ላይ ይገኛሉ መባሉን ተከትሎ በከተማዋ ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ይገኙበታል የተባሉ የሰሞኑ ስብሰባዎች ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጎንደርን ጎበኙ
(ኢሳት ዲሲ– ሚያዚያ 12/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጎንደር ሕዝብ ዛሬም አዲስ ታሪክ ይሰራል ሲሉ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዶክተር አብይ አህመድ ይህንን የተናገሩት ዛሬ በጎንደር ስታዲየም ለጎንደር ሕዝብ ባደርጉት ንግግር ነው። በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር የአማራ ክልል ሕዝብ ከዶክተር አብይ ጎን የተሰለፈው ለውጥ ስለሚፈልግ ነው ብለዋል። “ ጎንደር የድንቅ ታሪክ ባለቤት- የዘመነዊቷ ...
Read More »በኩባ የፊደል ካስትሮ ቤተሰብ የአገዛዝ ዘመን ሊያከትም ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2010) በኩባ የፊደል ካስትሮ ቤተሰብ የአገዛዝ ዘመን ሊያከትም መሆኑ ተገለጸ። ይህ የተባለው የቀድሞው የኩባ ፕሬዝዳንት የፊደል ካስትሮ ወንድም ራውል ካስትሮ ስልጣን ሊለቁ መሆናቸው መሰማቱን ተከትሎ ነው። የሃገሪቱ ፓርላማም የራውል ካስትሮ ቀኝ እጅ ናቸው የተባሉትን ሜግዌል ዲያዝ ኬኔልን በምትካቸው መምረጡ ተሰምቷል። የፊደል ካስትሮ ወንድም ራውል ካስትሮ እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2006 ጀምሮ የኩባን የመሪነት ስልጣን ተቆጣጥረው ቆይተዋል። የሃገሪቱን ኮሚኒስት ፓርቲንም ላለፉት ...
Read More »የድምጻዊ ታምራት ደስታ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2010)የድምጻዊ ታምራት ደስታ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ። ትላንት በድንገት ህይወቱ ያለፈው ድምጻዊ ታምራት ወዳጅ ዘመዶቹ፣ የሙያ ጓደኞቹና አፍቃሪዎቹ በተገኙበት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የቀብር ስነስርዓቱ መፈጸሙ ታውቋል። በሌላ በኩል የድምጻዊ ታምራት ደስታ የአሟሟቱ ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል። ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የተሰጠው መርፌ ድንገተኛ ሞቱን ሳያስከትል እንደማይቀር እየተነገረ ነው። ትላንት ጠዋት በጉሮሮው ላይ መጠነኛ ህመም ይሰማውና የሌሊት ...
Read More »በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የገባው የኮማንድ ፖስት ሃይል ከግቢው ተባረረ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2010)በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የገባው የኮማንድ ፖስት ሃይል በተማሪዎች ተቃውሞ እንዲወጣ ተደረገ። ባለፈው ሳምንት በተማሪዎች የተጀመረውን የምግብ ማቆም አድማ ተከትሎ ወደ ግቢው የገባው የኮማንድ ፖስት ሃይል ዛሬ መውጣቱን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አድማውን ለማስቆም የገባው ሃይል ተማሪዎችን የደበደበ ሲሆን 5 ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጅማ ተልከዋል። በሌላ በኩል ከምስራቅ ጎጃም ወደ ትግራይ ክልል ተጭኖ ሊወሰድ የነበረው ብረት በነዋሪው በተወሰደ ...
Read More »የወልቃይትን ጉዳይ የጸረ ሰላም ሃይሎች አጀንዳ አድርጎ ለማቅረብ እቅድ መያዙ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከጎንደር ህዝብ ጋር በሚያደርጉት ውይይት ላይ የተደራጁ ግለሰቦችን በማስገባት የወልቃይትን ጉዳይ የጸረ ሰላም ሃይሎች አጀንዳ ተደርጎ እንዲቀርብ ሕወሃት በዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ። ለኢሳት በደረሰው መረጃ ላይ እንደተመለከተው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን ከህዝብ የሚያጋጭ ሌላ ፍጥጫ በጎንደር ለመፍጠር የተዘጋጁ ግለሰቦች ስልጠና መውሰዳቸውም ታውቋል። በቅማንት የመብት ጥያቄ ስም የተደራጁት እነዚህ ግለሰቦች የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ...
Read More »የሜቴክ ዋና ዳይሬክተርና የኢንሳ ዳይሬክተር በሌላ ተተኩ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 11/2010)የብሔራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና የኢንሳ ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ምትክ አዲስ ሰዎች መሾማቸው ተሰማ።የፖሊስ ኮሚሽነሩም በሌላ ሰው ተተክተዋል። የብሔራዊ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ የሐገሪቱን ሃብት በመመዝበርና በማባከን በከፍተኛ ደረጃ እየተወቀሰ ሲሆን፣ ሃላፊዎቹም በበርካታ ቢሊዮን ብር ብክነት ተጠያቂ መሆናቸው ሲገለጽ ቆይቷል። ሹምሽሩ ተጠያቂዎችን ለፍርድ ማቅረብ ይጨምራል ወይ የሚለውም ...
Read More »