ከ100 ሺ በላይ የሚቆጠሩ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ ገቡ

ከ100 ሺ በላይ የሚቆጠሩ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ ገቡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሳምንታት በፊት በጉጂ ብሄረሰብ አባላትና በጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት መካከል ተነስቶ የነበረው ግጭት ተከትሎ ከ200 ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱን በሽምግልና ለመፍታት በተደረገው ሙከራ ብዙዎቹ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ ተመልሰው ነበር። ይሁን እንጅ ግጭቱ ካለፈው እሁድ ጀምሮ እንደገና በማገርሸቱ ከ 100 ...

Read More »

የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን መስመር ዘግተው አመሹ

የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን መስመር ዘግተው አመሹ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ወጣቶቹ እርምጃውን የወሰዱት ከህዳር 26 ጀምሮ በደህንነት አባላት ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ እስከዛሬ ድረስ ያለበት ያልታወቀው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊ አቶ ሳሊህ ረሺድ እንዲፈታ ለመጠየቅ ነው። ወጣቶቹ በሌሊት የጅቡቲን መንገድ በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስተጓጎል ያደረጉ ሲሆን፣ የክለልዩ ልዩ ሃይል ወደ ስፋረው በመጓዝ መንገዱን አስከፍቷል። ወጣቶች መንገዱን ...

Read More »

የመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አድማ በማድረግ ላይ ናቸው

የመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አድማ በማድረግ ላይ ናቸው (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ተማሪዎቹ አድማውን የጀመሩት ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተፈናቅለው በመቱ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተደረጉት ተማሪዎች ወደ ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ተመልሰው ትምህርታቸውን እንዲጨርሱ መወሰኑን ተከትሎ ነው። ተማሪዎቹ አስተማማኝ ሰላም በሌለበትና ለህይወታችን ዋስትና በማናገኝበት ሁኔታ ወደ ጅግጅጋ ለመመለስ አንችልም በማለት በማለት ለዩኒቨርስቲው ባለስልጣናት ቢያሳውቁም፣ ባለስልጣናቱ ግን የተማሪዎችን ጥያቄ የሚቀበሉት አልሆነም። በዚህም ተነሳ ...

Read More »

አለማቀፍ የኡንዲስትሪያል ህብረት የኢትዮጵያ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ዘመቻ ጀመረ

አለማቀፍ የኡንዲስትሪያል ህብረት የኢትዮጵያ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ዘመቻ ጀመረ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ውስጥ በጨርቃጨርቅና አልባሳት እንዱስትሪዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የተሻለ ክፍያ እንዲያገኙ ለማድረግ ኢንዳስትራያል ግሎባል ዩኒየን የተባለው የሰራተኞች ማህበር ዘመቻ ጀምሯል። በእነዚህ እንዱስትሪዎች ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን በወር 20 ዶላር አካባቢ የሚከፈላቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ያለውን የኑሮ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ሰራተኞቹ የመጨረሻ ክፍያቸው በወር 121 ...

Read More »

ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ልታደርግ የነበረውን ውይይት ሰረዘች

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010)ሰሜን ኮሪያ ከጎረቤቷ ደቡብ ኮሪያ ልታደርግ የነበረውን ውይይት ሰረዘች። ሰሜን ኮሪያ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ጋር ለመገናኘት የያዝኩትንም እቅድ ልሰርዝ እችላለሁ ማለቷም ተሰምቷል። ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ በኒዩክለር መሳሪያዬ ላይ ያላት አቋም አስገዳጅ ይመስላል ይህ ተከትሎም ከፕሬዝዳንት ትራምፕ ጋር ላልገናኝ እችላለሁ ብላለች። ከወር በፊት ነበር የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆን ኡን ከ 63 አመታት በኋላ የመጀመሪያ ነው የተባለና ታሪካዊ ...

Read More »

አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል ተፈቱ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010)በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአገር ውስጥ ደኅንነት ኃላፊና አማካሪ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ወልደ ሚካኤል  ከእስር ተፈቱ፡፡ ከ2006 ጀምሮ በእስር ላይ የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ በማረሚያ ቤት የነበራቸው ባህሪና ሌሎች መሥፈርቶች ታይተው በአመክሮ መፈታታቸው ተነግሯል፡፡ በሙስና ሰበብ የተከሰሱት የብአዲኑ አቶ መላኩ ፋንታ ግን እስካሁን አለተፈቱም። በሙስና ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩት አቶ ወልደ ሥላሴ ከእስር የተፈቱት ከሁለት ሳምንት በፊት ነው፡፡ ...

Read More »

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች የሚሰጡትን ድጋፍ ሊያጠናክሩ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010) ኢትዮጵያ እና ሱዳን ለኤርትራ መንግስት ተቃዋሚዎች የሚሰጡትን ድጋፍ ለማጠናከር ካርቱም ላይ ስምምነት መፈጸማቸውን ኤርትራ ገለጸች። ኳታርም ሂደቱን በመደገፍ ተባባሪ መሆኗ ተመልክቷል ። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው ስምምነቱ የተደረሰው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ  በቅርቡ ካርቱምን በጎበኙበት ወቅት  ነው። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ከትላንት በስቲያ ባወጣው እና በድረገጹ ላይ በለጠፈው መግለጫ  እንዳመለከተው አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ...

Read More »

በሃና ማሪያም አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው ፈረሰ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/ 2010) በአዲስ አበባ በተለምዶ ሃና ማሪያም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ቤታቸው ፈርሶ ሜዳ ላይ መጣላቸውን ገለጹ። ምትክ ቦታ ሳይሰጣቸው ድንገት በአፍራሽ ግብረሃይል ቤታቸው የፈረሰባቸው ነዋሪዎች በከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃችውን አመልክተዋል። በሌላ በኩል የስራ ማቆም አድማ ከመቱ አራተኛ ቀናቸውን ያስቆጠሩት የቦሌ ለሚ የኢንንዱስትሪ ዞን ሰራተኞች በፌደራል ፖሊስ ሲዋከቡ መዋላቸው ተገልጿል ። አዲስ አበባ ሃና ማርያም በዳግም ...

Read More »

በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/ 2010) በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት መቀጠሉ ተገለጸ። በመተከል ሁለት የአማራ ተወላጆች በጫካ ተገድለው መገኘታቸውን የኢሳት ወኪል ከስፍራው ካደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ክልል መንግስት ከጥቃት ሸሽተው በቅርቡ ወደ ባህርዳር የተሰደዱ የአማራ ተወላጆችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ ጥረት እያደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት ግድያው መቀጠሉ ተነግሯል። ባለፈው ህዳር ወር የጀመረው ጥቃት አሁንም ቀጥሏል። ከቀዬ መንደራቸው በማንነታቸው ...

Read More »

በሶማሌ ክልል 11 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 8/2010) በሶማሌ ክልል በቀጠለው ተቃውሞ በፊቅ ዞን በሁለት ከተሞች 11 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። ኢሳት የተገደሉት ሰዎች ስም ዝርዝር ደርሶታል። ቡሳ እና ለጋሂዳ በተባሉ ከተሞች ግድያውን የፈጸሙት የክልሉ ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ ታጣቂዎች መሆናቸው ታውቋል። ልዩ ሃይሉ ከየከተሞቹ እንዲወጣ ከፌደራል መንግስት ትዕዛዝ መሰጠቱን የሚጠቅሱት የኢሳት ምንጮች በህወሃት ጄነራሎች የሚደገፈው የክልሉ ፕሬዝዳንት ትዕዛዙን ተግባራዊ ለማድረግ እንዳልፈለገ ገልጸዋል። አንደኛ ወሩን እየደፈነ ያለው ...

Read More »