በኢትዮጵያ የተጀመረውን ለውጥ ስኬታማ እንዲሆን ጠቅላይ ሚንስትሩ ሊታገዙ ይገባቸዋል። ወንጀል የፈጸሙ በህግ ይጠየቁ፣ ጉዳተኞች ካሳ እንዲያገኙና አፋኝ ሕጎች እንዲነሱ ሲሉ የህግ ባለሙያዎች ገለጹ (ኢሳት ዜና ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) በመላው ኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመታት ህግን ተገን በማድረግ ለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት በሕግ ሊጠየቁ እንደሚገባ፤ ወንጀሎቹ በገለልተኛ አካል ተጣርተው ለህግ መጠየቅ አለባቸው። ጉዳተኞቹ ለደረሰባቸው ጉዳቶች ተገቢውን የሞራል ...
Read More »የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን የለውጥ ጅምር ለማወደስ የሀረር ሕዝብ ለነገ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በመስተዳድሩ ሳይፈቀድ ቢቀርም ሕዝቡ የፊታችን ቅዳሜ በራሱ ኃላፊነት ሰልፍ ለመውጣት መዘጋጀቱ ተገለጸ።
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን የለውጥ ጅምር ለማወደስ የሀረር ሕዝብ ለነገ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ያቀረበው ጥያቄ በመስተዳድሩ ሳይፈቀድ ቢቀርም ሕዝቡ የፊታችን ቅዳሜ በራሱ ኃላፊነት ሰልፍ ለመውጣት መዘጋጀቱ ተገለጸ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) የሀረር ነዋሪዎች በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት የሀረር ከተማን ጨምሮ በወረዳው ከተሞችና ገጠሮች በሙሉ ጅምር ለውጡን የሚያወድስ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ሕዝቡ ቢጠይቅም፣ የክልሉ መስተዳድር “ በሰልፎቹ የጸጥታ ችግር ...
Read More »የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጠላት ስለሆኑ ልንታገላቸው ይገባል ሲሉ ኮነኑ
የቀድሞው የኢንሳ ዳሬክተር ዶ/ር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን ጠላት ስለሆኑ ልንታገላቸው ይገባል ሲሉ ኮነኑ (ኢሳት ዜና ሰኔ 25 ቀን 2010 ዓ/ም) የቀድሞው የመረጃና ደህንነት ኤጄንሲ (ኢንሳ) ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ተክለብርሃን ወልደአረጋይ በትግረኛ ቋንቋ ከሚተላለፈው ድምጸ ወያኔ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን የለውጥ ጅምር አውግዘዋል። ‘“በዶክተር አብይ የሚመራው የለውጥ ኃይል ሳይሆን ጠላት ነው። በግልጽ ...
Read More »የአዲስ አበባውን የድጋፍ ሰልፍ ያስተላለፉ መገናኛ ብዙሃን ሊጠየቁ ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 25/2010) የአዲስ አበባውን የድጋፍ ሰልፍ ያስተላለፉ መገናኛ ብዙሃን ሊጠየቁ ይገባል ሲል የትግራይ ክልል ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ገለጸ። ድርጅቱ ከብሮድካስት ባለስልጣን የዕለቱን ትዕይንት ሽፋን ያልሰጠበትን ምክንያት እንዲያብራራ በደብዳቤ ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ ላይ እንደገለጸው በህግ የተከለከለ ሰንደቅ ዓላማን ጨምሮ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ የተባሉ ድርጅቶች አርማዎች የሚታይበትን ሰልፍ ያስተላለፉ የመገናኛ ብዙሃን መጠየቅ እንደሚገባቸው ጠቅሷል። የትግራይ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የትላንቱን ...
Read More »በኢትዮጵያ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እንደጠላት ማየት አለብን ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 25/2010) በኢትዮጵያ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እንደጠላት ማየት አለብን ሲሉ የቀድሞ የኢንሳ ዳይሬክተር ጄነራል ገለጹ። በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከስልጣናቸው የተነሱት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት መረብ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ ድምጸ ወያኔ ለተሰኘው የህወሀት ልሳን ሬዲዮ ጣቢያ በሰጡት ቃለመጠይቅ ላይ እንደገለጹት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር የኢህአዴግ ሽታ እንኳን የሌለው ነው። ህገመንግስታዊ ስርዓቱን እየበላ ያለ መንግስትም ...
Read More »የድጋፍ ሰልፉ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 25/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጀመሯቸውን የለውጥ ርምጃዎች የሚደግፉ ሰላማዊ ሰልፎች በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ውጭም ባሉ ኢትዮጵያውያን ዘንድ መቀጠላቸው ታወቀ። በተለይም በባህርዳር ከተማ የተካሄደው እጅግ ደማቅ ትዕይንተ ሕዝብ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ መሆኑም ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድም ሕዝቡ ለሰጣቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከመቶ ሺህ ሕዝብ በላይ የታደመበት የባህርዳሩ ትዕይንተ ሕዝብ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ሰብአዊ ...
Read More »በናይጄሪያ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ ተቃጥሎ 9 ያህል ሰዎች ሞቱ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) በናይጄሪያ አንድ ነዳጅ የጫነ ተሽከርካሪ በእሳት ከመያያዙ ጋር በተያያዘ 9 ያህል ሰዎች መሞታቸው ተሰማ። የተሽከርካሪውን ፍሬን መቆጣጠር ባለመቻሉ ተከሰተ በተባለው በዚህ አደጋ ሶስት የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ጨምሮ ከ50 በላይ ተሽከርካሪዎች በእሳት መጋየታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። የሃገሪቱ የመንገድ ደህንነት ተወካይ ለቢቢስ እንዳሉት ተሽከርካሪው ፍሬኑን መቆጣጠር ያቃተው በአካባቢው በሚገኝ ትልቅ ድልድይ አቅራቢያ ነው። ትራፊክ በሚበዛበት አካባቢ መፈጠሩና ከተሽከርካሪው የፈሰሰው ነዳጅ ...
Read More »ኦብነግ የጦር አዛዥ ከወህኒ ተለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር/ኦብነግ/የጦር ኮማንደር ትላንት ከወህኒ ተለቀቁ። የኦብነግ የጦር አዛዥ የነበሩት አብዱከሪም ሼክ ሙሳ አምና በነሐሴ ወር በሶማሊያ ጋልካዩ ታፍነው ወደ ሞቃዲሾ ከተወሰዱ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው መሰጠታቸው ይታወሳል። አምና በነሐሴ 2009 ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር የጦር አዛዥ ኮማንደር አብዱከሪም ሙሳ ላለፉት 11 ወራት በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ቆይተዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነሐሴ ...
Read More »በኦሮሚያ 4 የፖሊስ አባላት ቆሰሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) በኦሮሚያ ክልል ነቀምቴ ከተማ ያልታወቁ ሃይሎች 4 የፖሊስ አባላትን አቁስለው መሰወራቸው ተሰማ። የገዳዮቹን ማንነት ለማወቅና ለፍርድ ለማቅረብ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን የኦሮሚያ መንግስት አስታውቋል። የኦሮሚያ የገጠርና የፖለቲካ አደረጃጀት ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በአካባቢው ያለው ሕዝብ እራሱን ከአጥቂዎች እንዲጠብቅ አሳስበዋል። በኦሮሚያ ክልል የነበረው ግጭት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጋብ ቢልም በአንዳንድ አካባቢዎች ግን መጠነኛ ግጭት ይታያል። ግጭቱ ተባብሶ ...
Read More »ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የተፈናቀለባት ሃገር ናት ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 22/2010) ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ሆናለች ሲል የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ገለጸ። ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስከበር ህዝብ ተስፋ የጣለበት አጋጣሚ እንዳይባክን በሚል ርዕስ ሰመጉ ባወጣው መግለጫ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የዚህ ክልል ተወላጆች አይደላችሁም በሚል ከሚኖሩባቸው አከባቢዎች እየተፈናቀሉ ናቸው ብሏል። እነዚህ በሐገር ውስጥ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉም ሲል ...
Read More »