ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ ዛሬ ባወጠው ዘገባ እንደገለጠው ኢትዮጵያዊው የ15 ዓመት ታዳጊ ወጣት ፣ ናትናኤል የማነ፣ የኦሎምፒክ ችቦ ከሚያዞሩ ወጣቶች መካከል በመሆን ወደ እንግሊዟ ኖቲንግሀም ከተማ ባለፈው ሀሙስ አቅንቷል። ይሁን እንጅ ታዳጊው ወጣት ዛሬ ረፋዱ ላይ ከሆቴሉ እንደወጣ አልተመለሰም። የታዳጊው እንግሊዝኛ ችሎታ ውስን መሆንና መንገዶችን የማያውቅ በመሆኑ ፣ ታዳጊው ችግር ሊፈጠርበት ይችላል በማለት ፖሊሶቹ ስጋታቸውን ...
Read More »በሱዳን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የተቃዋሚ ደጋፊዎች የአልበሽር መንግስት እንዲወገድ ጠየቁ
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሱዳን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የተቃዋሚ ደጋፊዎች አልበሽር መንግስት እንዲወገድ ጠየቁበካርቱም እና በኦምዱርማን ዛሬ ከፍተኛ የመንግስት ተቃውሞ ሰልፎች ተደርገዋል። ተቃዋሚዎቹ የአልበሸር መንግስት እንዲወገድ ጥያቄ አቅርበዋል። ፖሊሶች ተቃውሞውን ለማፈን የሀይል እርምጃ መውሰዳቸውም ታውቋል። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other ...
Read More »የጭኮ እና የይርጋለም ህንጻዎች መፈክሮች ተውበው ታዩ፣ መፈክሮችን ለማጥፋት ህንጻዎች እንዲፈርሱ ተደርጓል
ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጭኮና በይርጋለም ከተሞች ዛሬ ጠዋት የታየው ነገር በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ይላል ዘጋቢያችን። ሰላም የራቀውና በሀዘን ድባብ ላይ የሚገኘው የከተማው ህዝብ ከቤቱ በጧት ሲወጣ የጠበቀው እንደ ሰሞኑ ፍርሀትና ጭንቀት ሳይሆን ደስታና ተስፋ ነበር። በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች ሁሉም በሚባል ደረጃ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሌሊቱን በሙሉ በደማቅ ቀለማት ሲሸለሙ አድረዋል። ህዝቡም በግድግዳዎቹ ላይ ...
Read More »ኢህአዴግ ነባር ታጋዮቹን ልዩ ተጠቃሚ የሚያደርግ ህግ አወጣ
ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነፍጥ ትግል የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረውና በአሁኑ ሰዓት ግን ኢህአዴግ በታገለበት መስመር በመሄድ በትጥቅ እና በሁለገብ ትግል ለውጥ ለማካሄድ የተደራጁ የተቃውሞ ኃይሎችን በአሸባሪነት የሚፈርጀው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ ለቀድሞ ታጋዮቹ ላሳለፉት የትግል ዘመን ልዩ የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ ደንብ አወጣ፡፡ በዚሁ ደንብ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ ሌሎች ታጋይ የነበሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ...
Read More »ከሳሾቼ እንድጠጣው የሚፈልጉትን የግፍ ጽዋ በጸጋ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ ሲል አቶ አንዱአለም አራጌ ተናገረ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ፓርቲ ም/ል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው አቶ አንዱአለም አራጌ ይህን የተናገረው ፣ የጥፋተኝነት ውሳኔ ለማስተላለፍ ዛሬ በዋለው ችሎት ላይ ነው። የዛሬውን የፍርድ ቤት ውሎ የተከታተለው ዘጋቢያችን እንደገለጠው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት በሽብር ወንጀል የተከሰሱትን ሁሉንም ተከሳሾች ጥፋተኞች ብሎአቸዋል። ከ9 ነኛ እስከ 24ኛ ባሉት ላይ የጥፋተኝነቱ ውሳኔ የተላለፈው በሌሉበት እና ...
Read More »በአዋሳ ከተማ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የክልሉ መስተዳደር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን በአዋሳ ባህል አዳራሽ ውስጥ በሰበሰቡት ወቅት ነው ውዝግቡ የተፈጠረው። አቶ ሽፈራው ” ሲዳማ ክልል እንዲሆን የጠየቃችሁት መቼውንም አይሳካም ቁርጡን እወቁት ” በማለት ሲናገሩ ተሰብሳቢው ተቃውሞውን ገልጧል። በአዋሳ ተወልደው የኖሩ የሲዳማ ብሄረሰብ ተወላጅ ያልሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ” እኛን የሲዳማ ህዝብ አላጠቃንም፣ ሲዳማ ...
Read More »ከታንዛኒያ ወደ ማላዊ ሲጓዙ የነበሩ 42 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞተው ተገኙ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የታንዛኒያ ያገር ውስጥ ምክትል ሚኒስትርን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው፤ በከባድ መኪና እንደ ዕቃ ከሁዋላ ታሽገው ወደ ማላዊ ሲጓዙ ከነበሩት 120 ሰዎች መካከል 42 ቱ ሞተዋል። ሚኒስትሩ ፔሬሪያ ሲሊማ እንዳሉት ስደተኞቹ የመጡት ከኢትዮጵያ ሲሆን፤የሞቱትም ከትራኩ የሁዋላ ክፍል ተጨናንቀው በመታሸጋቸው ሳቢያ አየር አጥሯቸው ነው። ታንዛኒያ እና ማላዊ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራቸው የሚፈጠርን ግጭት እና ድርቅን በመሸሽ ...
Read More »ከ 1 ሺህ 500 በላይ የወለኔ ተወላጆች አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገቡ ተከለከሉ
ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የወለኔ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ወሕዴፓ) እሑድ ሰኔ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በመሀል አምባ የጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ በፖሊስ ኃይል ተበተነ፡፡ ስብሰባውን ለመሳተፍ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተሰባስበው የመጡ የፓርቲው ደጋፊና የብሔረሰቡ ተወላጆች ወደ ከተማው እንዳይገቡ በክልሉ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ታግደው ወደመጡበት እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ፓርቲው ፤ ከብሔረሰቡ ተወላጆች፣ ከአባላቱና ከደጋፊዎቹ ጋር ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ...
Read More »በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የወረዳው የመረጃ ምንጭ እንደገለጠው ተቃውሞው የተነሳው ዛሬ 4 ሰአት ላይ ነው። በትናንትናው እለት እንደዘገብነው የካናዳ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተነሳውን ተቃውሞ ያነሳሱት ባለሀብቶችና ተቃዋሚዎች ናቸው በማለት የተናገሩትን ለመቃወም ነበር ዛሬ ሰለማዊ ሰልፉ የተጠራው። አቶ ሽፈራው ያደረጉትን ንግግር ያስቆጣቸው የጭኮ ወረዳ ...
Read More »ኢህአዴግ በአዲስ አበባ መጪውን ምርጫ 99 በመቶ ለማሸነፍ የሚያስቸለውን እንቅስቃሴ ጀመረ
ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ መንግሥት በመጪው ዓመት የሚካሄደውን የአዲስ አበባ እና የክልሎች የአካባቢ ምርጫ በሞኖፖል ጠርንፎ ለመቆጣጠር የሚያስችለውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ኢህአዴግ ጽ/ቤት የዜና ምንጮቻችን አስታወቁ፡፡ በየክረምቱ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ዩኒቨርስቲዎች አዳሪ የክረምት ኮርስ ስልጠና የሚወስዱ መምህራን ዓመታዊ የትምህርት ክፈለ-ጊዜያቸው ዘንድሮ ሊታጠፍ እንደሚችል፣ በምትኩ ኢህአዴግ የሚያካሂደው ሀገራዊ ንቅናቄ በዩኒቨርስቲዎች፣ በትምህርት ቤት ተቋማትና ...
Read More »