ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለ ዘረፈ ብዙ እና በብዙ ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ኢንቭስትመንት ወጪ ተደርጎለት ኢትዮጵያን ፡ኬኒያን እና ደቡብ ሱዳንን ይጠቅማል ተብሎ ኬኒያ ውስጥ የግንባታ እቅድ የተያዘለት የላሙ ፕሮጅክት ፤ከማህበረሰብ እና ከአካባቤያዊ ተቆርቋሪዎች ከፍተኛ ነቀፌታ ገጠመው ፡፡ “ኒው አፍሪካ የተባለውን ወርሃዊ መጽሄት” ዋቤ በማድረግ ህብር ራዲዮ ከላስ ቬጋስ እንደዘገበው ፤ይህ ከሃያ አራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ባላይ ...
Read More »ወቅታዊ የመወያያ መድረክ ለኢሳት የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አደረገ
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያንን በወቅታዊ የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በማመወያየት ከፍተኛ ከበሬታ ያገኘው የኢትዮጵያ ወቅታዊ የመወያያ መድረክ ( ኢካድፍ) በጋዜጠኛ አበበ ገላው ስም ለኢሳት ባደረገው የገንዘብ ማሰባሰብ ዝግጅት ከ30 ሺ ዶላር ያላነሰ ገንዘብ ማሰባሰቡን አስተባባሪው በቅጽል ስሙ ቅንጅት ፋር ኢስት ገልጧል። ቅንጅት ፋርኢስት እንደገለጠው ገንዘቡን ያዋጡት በመላው አለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ___________________________________________________________________________________________________________________________________________________ ESAT is ...
Read More »ሰበር ዜና በአዋሳ በተነሳ ግጭት 1 ሰው ተገደለ 2 ሰው ቆሰለ
የሲዳማ ወጣቶች “ሲወን” የሚል አዲስ ድርጅት መሰረቱ
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ የግብርና ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የክልሉ ፖሊስ ተወካዮች፣ የምክር ቤት አባላትና እና ሌሎችም ከ 300 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ዛሬ በአዋሳ ከተማ በህቡእ ተሰባስበው የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ የሚል ድርጅት መስረተዋል። በጉባኤው ላይ ከ22 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተወከሉ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን፣ የትግል ስትራቴጂያቸውን እና አላማቸውን ለተሰብሳቢው ይፋ አድርገዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ጉባኤ ...
Read More »በሚኒሶታ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ክርስቲያኑን እና ሙስሊሙን በማጋጨት ስልጣንን ማራዘም አይቻልም”፣ “ቀበሌ የካድሬ መፈልፈያ እንጂ የሙስሊም መሪዎች መምረጫ አይደለም”፣ “መንግስት በሃይማኖቶች ላይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ያቁም”፣ “በአሸባሪ ሽፋን ትግላችንን ማክሸፍ አይቻልም” የሚሉ መፈክሮችን የያዙ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በሚኒሶታ ሴንት ፖል ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አደርገዋል። ወደ 900 የሚጠጉ በርከት ያሉ የ እስልምና ተከታዮች ባደርጉት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ክርስቲያኖችም ...
Read More »ጋዜጠኛ እስክንድር እና አቶ ናትናኤል ብርሀኑ ወደ ክፍላቸው ተመለሱ
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጥፋተኝነት ብይን በተላለፈባቸው ማግስት ከታሰሩበት ክፍል በሌሊት ተወስደው የነበሩት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና አቶ ናትናኤል ብርሀኑ፤ ወደ ቀደመ የእስር ክፍላቸው ተመለሱ። “ስህተቱ ስለታረመ እናመሰግናለን!” በሚል ርዕስ የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ በፌስ ቡክ ባሰራጨው ዜና፤ ከትላንት በስቲያ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን እና አቶ ናትናኤል ብርሃኑንን በውድቅት ሌሊት ከእስር ክፍላቸው አውጥተው የት እንደወሰዷቸው ...
Read More »የአውስትራሊያ መንግስት ኢትዮጵያውያን የማደጎ ልጆች ወደ አገሩ እንዳይገቡ ከለከለ
ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአውስትራሊያ መንግሥት በማደጎ (ጉዲፈቻ ) ሥም፣ ወደ አውስትራሊያ ይመጡ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ወደ አገሪቱ እንዲገቡ ይፈቅድ የነበረውን ሕገ ደንብ መሰረዙን የአገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታወቁ። ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኒኮላ ሮክሶን ባለፈው ሃሙስ ይህንኑ አስመልክቶ እንደተናገሩት፤- የአውስትራሊያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የተገደደው ከኢትዮጵያ በማደጎ ስም የሚመጡ ሕፃናት ጉዳይ ብዙ ችግሮች ያስከተለና፣ ውስብስብ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት ሲጠይቁ ዋሉ
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአንዋር መስጊድ ለጁማ ሶላት የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ጥያቄያቸውን በጽናት እና በቁጭት አቅርበዋል። ድምጻችን ይሰማ፣ መጅሊስ አይወከለንም፣ ምርጫው በመስጊዳችን ይሁን፣ ህገ መንግስቱ ይከበርና የመሳሰሉትን መፈክሮች አሰምተዋል። መንግስት መጪው የመጂሊስ ምርጫ በቀበሌ እና በመስተዳድር ቦታዎች እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምርጫው በቀበሌ መሆኑ፣ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና ተማኞችን መልሶ ወደ መጅሊስ አመራር የሚመጣ ነው በማለት ይቃወማሉ። በዛሬው ...
Read More »ስቴት ዲፓርትመንት እስረኞቹ እንዲፈቱ ጥሪ አቀረበ
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ የ አቶ መለስ መንግስት ከመላው ዓለም ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተነሱበት ነው። የኢትዮጵያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነ አንዷለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት በተከሰሱ 24 ሰዎች ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማሳለፉን ተከትሎ በ አቶ መለስ መንግስት ላይ ከ ዓለም ዙሪያ ጠንካራ ተቃውሞዎች እየተሰነዘሩ ነው። በፍርድ ቤቱ ብይን ላይ ተቃውሞ ...
Read More »ግንቦት7 የይስሙላውን ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳፋሪ ሲል አጣጣለው
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት7 ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ ” የመለስ ዜናዊ የይስሙላ ፍርድ ቤት በ24 ንጹሀን ዜጎች ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ የሚገርም ” አይደለም ብሎአል። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲህ አይነቱን የይስሙላና አንድን ወገን ለመጥቀም ተብሎ የተደረገውን የድፍረት አሳፋሪ ውሳኔ የለመደው ነው የሚለው ንቅናቄው፣ በጋዜጠኞች ላይ የተላለፈው ውሳኔም ሀሳብን የመግለጽን መብት ሙሉ በሙሉ የሚደመስስ ነው በማለት አለማቀፍ የመብት ተንከባካቢ ...
Read More »