የፈደራል ፖሊስ አባላት ሁለት የአፋር ተወላጆችን ከክልሉ ፖሊስ እጅ ነጥቀው ገደሉ

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፈደራል ፖሊስ አባላት  ሁለት የአፋር ተወላጆችን ከክልሉ ፖሊስ እጅ ነጥቀው  ገደሉ የዱብቲ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ፤ የፌዴራሎቹን ድርጊት ተቃውመዋል። የኢሳት  ወኪል ከስፍራው እንደዘገበው፤ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የተወከሉ ፖሊሶች በዱብቲ ወረዳ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ይገኙ የነበሩ አፋሮችን በጉልበት በመውሰድ አንዱን መኪና ውስጥ ወዲያውኑ ሲረሽኑት፤ ሌላኛውን ደግሞ ቁስለኛ አድርገውታል። ፌደራል ፖሊሶቹ  የሟቹን አስከሬን እና ቁስለኛውን ...

Read More »

የማስተርስና የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው ዜጐች አዲስ አበባ ውስጥ የጐዳና ተዳዳሪ ሆነዋል

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህ የተገለፀው፤የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ትናንትና በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ካህሳይ ገብረመድህን እንዳሉት፤ በከተማው ያሉትን የጐዳና ላይ ተዳዳሪዎች ወደ መልካም ሕይወት ለመመለስ፣ አስተዳደሩ በማድረግ ላይ ባለው እንቅስቃሴ፤ መምህር፣ ነርሶችና በተለያዩ ሙያዎች የተመረቁ ዜጐች የጐዳና ላይ ተዳዳሪ ሆነው መገኘታቸውን አረጋግጧል፡፡ እነዚህን የተማሩ ዜጐች ለጐዳና ...

Read More »

የአለም ደቻሳ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈጸመ

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቤይሩት ውስጥ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ በአሰቃቂ ሁኔታ ስትደበደብ ከታየች ከቀናት በኋላ፤ ለሕክምና የገባችበት ሆስፒታል ውስጥ ሕይወቷን አጠፋች የተባለችው የአለም ደቻሳ የቀብር ስነ-ስርዓት  ተፈጸመ። የ ዓለም የቀብር ሥነ-ስርዓት የተፈጸመው፤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 27 ቀን በትውልድ ቦታዋ ቡ በግንደ-በረት  ቤተሰቦቿን ጨምሮ የአካባቢው ማሕበረሰብ በተገኙበት ነው። ለአራት ወራት ያህል እዚያው ቤይሩት የሚገኝ ሆስፒታል ...

Read More »

የስዊድን መንግሥት አትሌት አበባ “ስዊድናዊ ነት ይላል

ሰኔ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጣሊያን ሮም በተደረገው ዳይመንድ ሊግ ኢትዮጵያን ወክላ በ1 500 ሜትር ውድድር ያሸነፈችው የአትሌት አበባ አረጋዊ የዜግነት ጉዳይ ውዝግብ አስነሳ። አበባ ከሳምንታት በፊት ሮም ላይ በተደረገው ዳይመንድ ሊግ ውድድር፤ ገንዘቤ ዲባባንና ሌሎች የዓለማችንን ታላላቅ አትሌቶች አስከትላ በመግባት አንጸባራቂ ድል መቀዳጀቷ ይታወሳል። አበባ፤በሮሙ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ  አገሯን ወክላ ከመሮጧ አኳያ፤ ኢትዮጵያ ለለንደኑ ኦሊምፒክ ...

Read More »

በዋልድባ ገዳም መነኮሳት እየታደኑ ነው

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የገዳሙ መነኩሴ ለኢሳት እንደተናገሩት መንግስት የህዝብን ተቃውሞ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት የገዳሙን አካባቢ ማረስ መጀመሩን የተቃወሙ 5 መነኮሳት በፌደራል ፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። 3ቱ መነኮሳት ማይጸብሪ ወይም አድርቃይ አካባቢ ተወስደው መታሰራቸውን የተናገሩት አባት፣ ሁለቱ ግን አድርቃይ ተወስደው መታሰራቸውን እንደሚያውቁ ተናግረዋል። ጨመው በር እና አጠላ የሚባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች የመነኮሳቱን ...

Read More »

ለሀገር ጥፋት ከመኖር፤ ከሀገር መጥፋት ይሻላል” የአዲስ ዘመን አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገንን አስፈራሩ

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍትህ ጋዜጣንና  ዋና አዘጋጁን ተመስገን ደሳለኝን -ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ለማስመሰል በአልሸባብ ስም ኢሜይል በመፃፍ የተደረገው የክፋትና የተንኮል ሙከራ ፤በራሱ በጋዜጠኛ ተመስገን መጋለጡ ይታወቃል። “ሀገር በምን ይፈርሳል?” በሚል ርዕስ ተመስገን በዚህ ሳምንት ባሰፈረው ቀጣይ ጽሁፉ ፤የዚያ እኩይ ምግባር ፊታውራሪ አዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደሆነ ፦ የዘመንን ህትመቶች መጥቀሱን አውስቷል። ይህንን ተከትሎ በማግስቱ ቅዳሜ  ...

Read More »

የቡና ገቢ አሸቆለቆለ

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዓለም አቀፍ ደረጃ በተፈጥሮ ቡና ምርትዋ የምትታወቀው ኢትዮጵያ በ2004 በጀት ዓመት ባለፉት 11 ወራት ለውጪ ገበያ ያቀረበችው ቡና ለመላክ ከታሰበው ገቢ ጋር ሲነጻጸር መቀነሱ ታወቀ፡፡ ከንግድ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ እንደሚያሳየው የአገሪቱ የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚነገርለት ቡና በ11 ወራት ውስጥ ያስገኛል ተብሎ ከተጠበቀው ጋር ሲነጻጸር ያስገኘው 67 በመቶ ያህል ብቻ ነው፡፡በተጠቀሱት ጊዜያት 261 ...

Read More »

በአዋሳ ከተማ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፉት 2 ሰማንታት በአዋሳ የነበረው ውጥረት እየተባባሰ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ትናንት ማታ በፌደራል ፖሊስና በህዝቡ መካከል በተነሳ ግጭት 1 ሰው ሲገደል ሁለት ደግሞ ቆስለዋል። ግጭቱ የተነሳው በአዋሳ ከተማ ወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ አካባቢ የተካሄደውን የሰርግ ስነስርአት ተከትሎ ነው። የሲዳማ ወጣቶች በሲዳምኛ እየጨፈሩ ሙሽሮችን ለመቀበል ሲሄዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ተኩስ ከፍተውባቸዋል። በፖሊሶች ድርጊት የተበሳጩት ...

Read More »

የዋልድባ መነኮሳት በፌዴራል ፖሊስ እየታደኑ ነው

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዋልድባ ሰቋር ኪዳነ ምሕረት ገዳም አራት መነኮሳት ባለፈው ቅዳሜ በመንግስት ታጣቂዎች ተይዘው መወሰዳቸውንና ገዳሙም ከሰሜን ጎንደር ዞን በተላኩ በርካታ የፌዴራል ፖሊሶች ተከቦ እንደሚገኝ “ደጀ ሰላም” የተሰኘው ድረገጽ በዝርዝር ዘገበ። እንደ ዜናው ዘገባ በሱባኤ ላይ የነበሩ በርካታ መነኮሳትም በፖሊሶች ዱላ ተደብድበው እንዲበተኑ መደረጋቸው ታውቋል። ከገዳሙ ከተወሰዱት አራት መነኰሳት መካከልም ሶስቱ አባ ኀይለ ኢየሱስ፣ ...

Read More »

ቃሊቲ እስር ቤት የሚገኙት የስዊድን ጋዜጠኞች ብሶታቸውን ገለፁ

ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የ11 ዓመታት እስራት ተፈርዶባቸው፣ አንድ ዓመት በእስር ቤት ያሳለፉት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች “ይህ ዓመት በሕይወታችን እጅግ በጣም ረጅሙ ነው፣ እየደረሰብን ያለው ስነልቦናዊ ጉዳትም የማሰብ ችሎታችንን እያሳጣን ነው” ሲሉ አማረሩ። ሁለቱ  ጋዜጠኞች ባለፈው ሃሙስ እስር ቤቱ ድረስ ሊጠይቋቸው ለሄዱት የስዊድን ዲፕሎማቶች እንደገለፁት “እያሰብን ያለነው ስለምንበላው ምግብ፣ የምንተኛበት የሲሚንቶ ወለል እንዴት ሊሞቅ እንደሚችል፣  እና ...

Read More »