ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፖሊስ አባላት ጋር ተጋጩ በርካታ ሰዎች ተጎድተዋል በዛሬው የኢድ አል ፈጥር በአል ላይ በጊዮን ሆቴል በኩል የተቃውሞ መፈክሮችን እያሰሙ ሲሄዱ የነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፣ ከብረት ለበስ የፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ተጋጭተዋል። በርካታ ሙስሊሞች ተረጋግጠዋል፣ በቆመጥና በዱላ ተደብድበዋል፤ የተፈነከቱ፣ እጅና እግራቸው የተሰባበሩ ሰዎች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተወስደዋል። አንዲት እርጉዝ ሴት መረገጧንም ዘጋቢያችን ገልጧል። ብዙዎችም በፖሊስ ካሚዮን ተጭነው ወደ ...
Read More »ወቅታዊ ዜና:-በኢድ አል ፈጥር በአል ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ
በኢድ አል ፈጥር በአል ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ የተወሰኑ ሰዎች ታሰሩ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢድ አል ፈጥርን በአል ለማክበር የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል። የክብር እንግዳው የነበሩት የአዲስ አበባ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ እና የእስልምና ምክር ቤት ሃላፊዎች ንግግር እንዳይደመጥ እና እንዲቋረጥ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተቃውሞው እንደተጀመረ የቀጥታ ስርጭቱን አቋርጧል። በተመሳሳይም በደሴ ፣ አዳማ ( ናዝሬት) , ጅማ ...
Read More »የደህንነት ሹሙ አቶ አቶ ጌታቸው አሰፋ “የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ተከትሎ ጎንበስ ቀና ማለቱ ያስተዛዝባል” አሉ
ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የብሄራዊ የመረጃ እና የደህንነት ምንጭ እንደገለጠው የደህንነት ዋና ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሰሞኑን ዋና ዋና የሚባሉ የኢሚግሬሽንና የውጭ መረጃ ሰራተኞችን እና በተለያዩ ተቋማት የተመደቡ የደህንነት አባላትን ሰብስበው በአቶ መለስ ዜናዊ የደህንነት ሁኔታ ላይ ገለጻ ሰጥተዋል። ከስብሰባው በፊት በከፍተኛ የስልጣን እርከን ላይ ለሚገኙት የደህንነት አባላትና የመንግስት ባለስልጣናት ” የጠቅላይ ሚኒስትሩን ህመም ተከትሎ ...
Read More »ብአዴን እየታመሰ ነው
ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የብአዴን አባል የሆኑ ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሰሞኑን የብአዴን የኮር አባላት ለሁለተኛ ጊዜ በአቶ በረከት መሪነት በባህርዳር ከተማ ስብሰባ አድርገዋል። የአማራ ክልል የወጣቶች ፕሬዚዳንት የሆነው ወጣት ዘመነ ካሴ ከአገር መውጣቱና ለኢሳት ቃለምልልስ መስጠቱ፣ በክልሉ የተነሳው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከአቶ መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ ጋር ተደማምሮ በብአዴን የኮር አባላት ላይ ከፍተኛ ፍርሀት እና አለመረጋጋት ...
Read More »ልዑል ሙሉጌታ አስራተ ካሳ ተባረሩ
ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከውጭ ጉዳይ ሰራተኞች በደረሰው መረጃ ልኡሉ በትናንትናው እለት በ2 የደህንነት ሰዎች ታጅበው ምርር ብለው እያለቀሱ ከለንደን ኢምባሴ ወጥተዋል። የኢህአዴግ ካድሬ በመሆናቸው ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የአማካሪነት ቦታ አግኝተው የነበሩት አስራቴ ካሳ ፣ ከስራ የተባረሩት ያለ ኢምባሲው ፈቃድ ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ ዝግጅት ጳጳሱን በተመለከተ ቃለምልልስ ሰጥተዋል ተብሎ ነው። እርሳቸው ግን ቃለምልልሱን ...
Read More »በነገው የኢድ በአል ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል
ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ እና አካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ በቅርቡ በፌደራል ፖሊስ እና በደህንነት ሀይሎች በማእከላዊ እስር ቤት በቁጥጥር ስር የዋሉ የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ለማስፈታት የነገውን የኢድ አል ፈጥር በአል የአዲስ አበባ ስታዲዮምን ስግደት ሊጠቀሙበት መዘጋጀታቸውን ምንጮቻችን ገልጠዋል። የታሰሩ ወገኖቻችንን ሳናስፈታ ወደ ቤታችን አንገባም የሚል መሪ ቃል መዘጋጀቱም ታውቋል። በትናንትናው የጁመአ ...
Read More »የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትን ለመምረጥ ፍትጊያው ቀጥሎአል
ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከምግብ መመረዝ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሕመም ምክንያት ከኃላፊነታቸው ለመነሳት ከአንድ ዓመት በፊት የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ያቀረቡት የኦህዴድ እና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አለማየሁ አቶምሳ እስካሁን ጥያቄያቸው ምላሸ ባለማግኘቱ ፣ እርሳቸውን ማን ይተካ የሚለው ጥያቄ በኦህዴድ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ መፍጠሩ ታውቋል። በጳጉሜ ወር 2002 ዓ.ም በአዳማ ...
Read More »በሲያትል እና አካባቢዋ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የህወሀትን የዘረኝነት አሠራርን አጥብቀው ተቃወሙ
ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሲያትል እና አካባቢዋ የሚኖሩት የትግራይ ተወላጆች ህወሀትን አጥብቀው የተቃወሙት፤ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ነገ እሁድ ኦገስት 19 ቀን በ3515 ሳውዝ አላስካ በሚገኝ የስብሰባ አዳራሽ በሚካሄድ እና ከ2 ሰ ዓት እስከ 6 ሰዓት በሚቆይ የመንግስት ስብሰባ ላይ የትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲገኙ ተለይቶ ጥሪ በመደረጉ ነው። በበርሀ ስማቸው ተወልደ አጋመ ተብለው በሚጠሩት በአምባሳደር ተወልደ ገብሩ ...
Read More »የብጹፅ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዜና ረፍት የመላው ኢትዮጵያውያን መነጋገሪያ ሆኗል
ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢዎቻችን እንደገለጡት የአቡነ ጳውሎስን ድንገተኛ ዜና እረፍት ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው ። አንዳንድ ሰዎች አቡኑ በዋልድባ እና በሌሎች ገዳማት ላይ ለፈጸሙት በደል እግዚአብሄርን አሳዝነዋል የሚል አስተያየት ሲሰጡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ የሞታቸው መንስኤ ከአቶ መለስ ዜናዊ ደህንነትጋር የተያያዘ ነው ይላሉ። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አባት አቡነ ጳውሎስ ለሞት የሚያበቃ በሽታ እንዳልነበረባቸው መስክረው፣ ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መረጋጋት የሚያስፈልጋት ጊዜ ላይ ናት ሲል ታዋቂው ጸሀፊ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ገለጠ
ነሀሴ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀይማኖታዊ ጽሁፎቹ የሚታወቀው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ የአቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ እረፍት እንዳስደነገጠው ገልጧል:: በአቡነ ጳውሎስ የ20 አመታት አስተዳዳር የተሰሩ መልካም ስራዎች የመኖራቸውን ያክል ባይሰሩ ይሻል ነበር የሚያስብሉ ጉዳዮች እንደነበሩም ዲያቆን ዳንኤል ይናገራል:: ወቅቱ የመረጋጋት ፣ እርስ በርስ የምንተጋገዝበት እና ለወደፊቱ መልካም የሆኑ ስራዎችን ስርተን ለማለፍ የምንችልበት መሆኑን ሁለም ሰው ...
Read More »