ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያን ሀርነት ትግራይ ነባር ታጋይ የሆኑት አቶ አስገደ ገብረስላሴ ለአቶ መለስ ዜናዊ ወታደራዊ ትምህርት እንደሰጡዋቸው ይናገራሉ:: የአቶ መለስ ዜናዊን የ21 አመታት አስተዳዳር እንዴት ይገመግሙታል ተብለው የተጠየቁት አቶ አስገደ ፣ በርካታ ችግሮች መታየታቸውን አልሸሸጉም:: አቶ መለስ ስልጣን ለቀው ያሳለፉትን አመራር ለመገምገም እድል አግኝተው ቢሆን ኖሮ ይመርጡ እንደነበር ተናግረው፣ ስልጣኑን የተረከበው አካልም የኢትዮጵያን ...
Read More »ስለ አቶ መለስን ሞት የተለያዩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አስተያየት
ነሀሴ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በኢትዮጵያ የመሪነት ሥልጣን የሚይዘው ሰው የሚመራበትን ሁኔታ ራሱ መምረጥ ይኖርበታል፡፡ የሚመራበትን ሁኔታ በፓርቲ ማዕቀፍ ውስጥ አስገብቶ መስጠት የሚመራውን ሰው መናቅ ነው ብዬ ነው የማስበው” ሲሉ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ተናገሩ። በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሞት ሀዘን እንደተሰማቸው በመግለፅ፦” ፤”ከእንግዲህ በሞተ ሰው ...
Read More »የአቶ መለስ አስከሬን ዛሬ አዲስ አበባ ገባ
ነሀሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን በተገኙበት ዛሬ አስከሬናቸው አዲስ አበባ የገባው አቶ መለስ፣ በዋሽንት የሀዘን እንጉርጉሮ የታጀበ ወታደራዊ አቀባበል አቀባበል ተደርጎላቸዋል። አብዛኞቹ ባለስልጣናት በተለይም የኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምኦንና የደህንነት አማካሪው አቶ ጸጋየ በርሄ ስሜታቸውን መቆጣጠር ተስኖአቸው አምርረው ሲያልቅሱ ታይተዋል። ወይዘሮ አዜብ መስፍንና የአቶ መለስ ልጆችም እንዲሁ በእንባ ሲራጩ ታይተዋል። ከቦሌ ...
Read More »ተቃዋሚዎች ያለፈው የግፍ ስርአት ተመልሶ የማይመጣ መሆኑን በትግላችን የምናሳይበት ውቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ገለጡ
ነሀሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግንቦት 7 ንቅናቄ መሪ የሆኑት ኢኮኖሚስቱ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የመለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በግላቸው ስለፈጠረባቸው ስሜት እና በአገሪቱ ላይ ሊያመጣ ስለሚችለው መጥፎ ወይም ጥሩ አጋጣሚ ተናግረዋል የተለያዩ ሀይሎች እጃቸው ላይ ያለውን ካርድ የሚጫወቱበት መንገድ የኢትዮጵያን እጣ ፋንታ እንደሚወስን ዶ/ር ብርሀኑ ተናግረዋል:: በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን የሚታየውን የስልጣን ክፍተት ተከትሎ ...
Read More »የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሞት መለየታቸውን ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተንጸባረቁ ነው
ነሀሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከሳምንታት በፊት ከዓለማቀፉ ግጭት ተንታኝ ቡድን ውስጥ ያሉ ምንጮቹን በመጥቀስ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን ይፋ ቢያደርግም፤ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩን አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናትና በአገር ቤት የሚታተሙ አንዳንድ ጋዜጦች አቶ መለስ በቅርቡ ሥራ ለመጀመር በሚያስላቸው ጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሲገልፁ ቆይተዋል። አቶ መለስ አርፈዋል፤አላረፉም የሚለው እሰጥ እገባ ...
Read More »አዲሱ የኢትዮጵያ መሪ የሰብአዊ መብቶች እንዲሻሻሉ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ሂውማን ራይትስ ወች አሳሳበ
ነሀሴ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሂውማን ራይትስ ወች ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ አለማቀፉ ማህበረሰብ አዲሱ መንግስት መሰረታዊ የሚባሉ መብቶችን እንዲያከብር ፣ ቀደም ብለው የወጡ ህጎች እንዲሰረዙ ግፊት ማድረግ እንዳለባቸው ገልጠዋል። የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ወኪል የሆኑት ሌስሊ ሌፍኮው “አዲሱ መንግስት መሰረታዊ የሆኑ የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብር፣ አቶ መለስ የሰሩዋቸውን መልካም ስራዎች በመጠበቅ፣ በእርሳቸው ጊዜ የወጡ አደገኛ ህጎችን በመቀልበስ ...
Read More »የአቶ መለስ ዜናዊን ዜና እረፍት ተከትሎ በመላው አገሪቱ ውጥረት ነግሷል
በአዲስ አበባ በርካታ ሰዎች ከእየ አካባቢያቸው ተሰባስበው የሚሆነውን በኢትዮጵያ ሬዲዮና እና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚከታተሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ህዝቡን የማረጋጋት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ገድል በማወጅና እና በመሳሪያ የተቀነባበረ ሙዚቃ በማቅረብ ላይ ናቸው። በመንግስታዊ ድርጅቶች እና ተቋማት ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ መውለብለብ ጀምሯል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በየቦታው ፣ በሰፈሮች ውስጥ ሳይቀር ተበታትነው ይታያሉ። በቀበሌዎችና ወረዳዎች ውስጥ የመደናገጥ ሁኔታ ይታያል፣ አግልግሎት ...
Read More »ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በይፋ ከተነገረ በኃላ የመጀመሪያ በሆነው የመንግስት መግለጫ የቀብር አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን፣ከዛሬ ጀምሮ እስከቀብር ቀን የሚዘልቅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን መታወጁን፣የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ብሔራዊ ኮሚቴው የቀብሩን ቀንና ሥነሥርዓት በተመለከተ በቀጣይ ...
Read More »የፌደራል እና የመከላከያ ፖሊስ አባላት በከተሞች ጥብቅ ቅኝት እያደረጉ ነው
ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያው ጠ/ሚ፤ አቶ መለስ ዜናዊ በተወለዱ በ57 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ይፋ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሁለት ወራት ከተሰወሩ በኋላ ነው ዛሬ፤ ማክሰኞ፤ ነሀሴ 15 ቀን መሞታቸው የተዘገበው። ኢሳት ሀምሌ 23 ቀን፤ የአለምአቀፉን የቀውስ አጥኚ ቡድን (አይ.ሲ.ጂ) ውስጣዊ ምንጮችን ጠቅሶ የአቶ መለስን ሞት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ መለስን ሞት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ...
Read More »