Amsterdam

ካለፉት 6 ወራት ወዲህ በደሴ ከተማ የተከሰተው የውሃ እጥረት ተባብሷል

ሰኔ ፮ (ስድስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደቡብ ወሎ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የደሴ ከተማ ካለፉት ስድስት ወራት ጀምሮ በከፍተኛ የመጠጥ ውሃ እጥረት መቸገሯን የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። ለውሃ ስርጭቱ መቋረጥ የመብራት እጥረት መፈጠሩን መስተዳድሩ በምክንያትነት ይጠቅሳል። ነዋሪዎች አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ አስር ብር ለመግዛት ተገደዋል። ለተጨማሪ ወጪዎች ከመዳረጋቸው በተጨማሪ የምንጭ ውሃ በአምራጭነት በመጠቀማቸው ለውሃ ወለድ በሽታዎች መጋለጣቸውን ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 በሳምንቱ መጨረሻ በርካታ ጥቃቶችን መፈጸሙን አስታወቀ

ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መረጃ በሰሜን ጎንደርና በአዲስ አበባ የተለያዩ ጥቃቶችን ፈጽሟል። በሰሜን ጎንደር አንድ የሱዳን ተሳቢ የፈሳሽ መጫኛ መኪና ከሱዳን ተነስቶ በመተማ መንገድ በማለፍ ጣራገዳም ተራራን ጨርሶ አዲስ ዘመን ከተማ ለመግባት 2 ኪሎ ሜትሮች ሲቀረው የንቅናቄው ታጋዮች በወሰዱት ጥቃት የመኪናው ሹፌር እና የመኪናው ጎማ እንደተመታ ተሳቢውንና መኪናው ለየብቻ መውደቃቸውን ...

Read More »

በቲሊሊ የፖሊስ አባላት እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው

ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በአዊ ዞን ቲሊሊ ከተማ የፖሊስ አዛዥ የሆነው ኮማንደር አወቀን ጨምሮ አንድ የፖሊስ መኮንንና ሌላ አንድ የወረዳ የካቢኔ አባል ታስረዋል። አንዳንድ ፖሊሶቹ የታሰሩት ባለፈው አርብ ከሰአት በሁዋላ ስብሰባ ጨርሰው ከወጡ በሁዋላ በቤታቸው ውስጥ ሲሆን፣ ኮማንደር አወቀ ደግሞ ስራ ቦታው ላይ መያዙን ታውቋል። የፖሊስ አባላት መስራት ያለባቸው ለአማራ ...

Read More »

መሬታችንን አንሰጥም ያሉ የደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደሮች በጅምላ እየታሰሩ ነው

ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን ካለምንም ምትክ ቦታና ካሳ የመኖሪያ ቤቶቻቸውን እና የግጦሽ ማሳዎችን በልማት ስም መነጠቃቸውን የተቃወሙት አርብቶ አደሮች በገፍ ወደ እስር ቤቶች እየተጋዙ መሆኑን ምንጮቻችን አስታወቀዋል። በኩራዝ ስኳር ፋብሪካ አካባቢ ነዋሪ የሆኑ የሃመር፣ ጸሚያ፣ ዳሰነች፣ ናያቶም፣ ሙርሲ፣ ኤርቦሬ፣ ማና ብሄረሰብ አባላት የግፍ እስራቱ ተጠቂዎች ሆነዋል። በዞኑ በሚገኙ የወረዳ እስርቤቶችና ...

Read More »

ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ለሦስተኛ ጊዜ ተቃጠለ ሰኔ ፭ ( አምስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኮልፈ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 በተለምዶ ካራቆሬ በሚባለው አካባቢ ዘይት ቤት በመባል በሚጠራው ግቢ የሚገኘው ‹‹ሮያል ስፖንጅ ፋብሪካ ›› ከጥቅምት 05/09 ጀምሮ እስከ ሰኔ 3 ቀን 20099 ዓ.ም ድረስ ባሉት 9 ወራት ለሦስተኛ ጊዜ መቃጠሉን ዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ከቀኑ 8 ሰዓት ...

Read More »

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ስራአስኪያጅ አባ ሃይለማርያም የመመረቂያ ጽሁፋቸውን ከሌላ ተማሪ ጽሁፍ ገልብጠው የዶክትሬት ዲግሪ እንዳገኙ ተጋለጠ

ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ስራ አስኪያጅ፣ የአለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ የስራ አስፈጻሚ አባልና በቅርቡ ደግሞ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት “ዕጩ ቆሞስ” ኾነው የተሾሙት አባ ሃይለማርያም መለሰ ፣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 ለደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ባቀረቡት የዶክትሬት የመመረቂያ ጽሀፍ ላይ ፣ ከዚህ ቀደም በአንድ ኢትዮጵያዊ ቄስ የተጻፈውን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ...

Read More »

ብ/ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የአጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆኑ

ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ የነበሩት ብ/ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና የአጋዚ ክፍለ ጦር አዛዥ ሆነው ሲሸሙ ጄል ገብረመድህን በቅጽል ስማቸው ወዲ ነጮ ደግሞ ምክትል ሆነዋል። ብ/ ጄኔራል ጌታቸው በኦሮምያ ከነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ግምገማ ቀርቦባቸው ነበር። በኢትዮጵያ ውስጥ በጭካኔውና በፈጸማቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚታወቀውን የአጋዚ ክፍለጦር እንዲመሩ መደረጉ በጄኔራሉ ላይ ቅሬታ ...

Read More »

በአማራ ክልል የኮሌራ ወረሽኝ እየተስፋፋ ነው

ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በንጹህ መጠጥ ውሃ እና የምግብ መበከል ምክንያቶች የሚከሰተው የኮሌራ ወረሽኝ በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ በምእራብ ጎጃም ውስጥ በሚገኙ 12 ወረዳዎች አድማሱን እያሰፋ ነው። እስካሁን ድረስም ከ252 በላይ ነዋሪዎች በአጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት መጠቃታቸውን የክልሉ የጤና ቢሮ አስታውቋል። አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት አተት በመባል በሚታወቀው የኮሌራ በሽታ ተጠቂ የሆኑ 47 ታካሚዎች ...

Read More »

ነዋሪነቱ በስዊትዘርላንድ ሲዮን ከተማ የነበረውና በበርካታ ሀገራዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ጉልህ ተሳትፎ በማድረግ የሚታወቀው ኢትዮጵያዊ አቶ መኳንንት መታፈሪያ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሰኔ ፪ ( ሁለት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መኳንንት መታፈሪያ የሀገሩንና የወገኑን ጉዳይ እንደግል ጉዳዩ በመወሰድ ለኢትዮጵያዊያን የመብት ትግል ያለመታከት የዜግነት ድርሻውን ሲወጣ የኖረ ጎልማሳ ነበር። አቶ መኳንንት ከሰብአዊና ማህበራዊ ትጋቶቹ በተጨማሪ በሚኖርበት ከተማ የኢሳትን ቻፕተር በመመስረት ድጋፍ በማስተባበርና እራሱም በመደገፍ ሊረሳ የማይችል ተግባር ሲፈጽም እንደነበረ የስዊትዘርላንድ ኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ለኢሳት በላከው የሀዘን መግለጫ ጠቅሷል። የአቶ ...

Read More »

በሲዳማና በወላይታ ድንበሮች መካከል ግጭት ለመቀስቀስ እየተሰራ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ

ሰኔ ፩ ( አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአመታት በፊት በወላይታና ሲዳማ ድንበሮች መካከል ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ ተነስቶ የነበረው ግጭት፣ የብዙ ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈ በሁዋላ፣ ግችቱ በድጋሜ ሊቀሰቀስ እንደሚችል ነዋሪዎች አስጠንቅቀዋል። ከአመታት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት 19 ሰዎች ሞተው፣ 65 ቤቶች ተቃጥለው የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ገብቶ እንዳስቆመውና አወዛጋቢ የተባሉ ቦታዎች በወላይታ ዞን ክልል እንዲቆይ ተደርጎ ግጭቱ ...

Read More »