ባለፈው ዓመት በስዊድን ስቶኮሆልም በከባድ መኪና ሕዝብ ላይ በመንዳት አምስት ሰዎችን የገደለው የኡዝቤክ ተወላጅ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የ40 ዓመቱ ራክማት አኪሎቭ የስቶኮሆልሙን ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ራሱን ኢስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ተመልክቷል።. ይሁንና አይ ኤስ ግን ከጥቃቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት ምንም ያለው ነገር የለም። የስደተኝነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ...
Read More »Amsterdam
የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈጸመ ነው ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ
የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈጸመ ነው ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በ4ኛው ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ነው። “ ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር መምጣት በሁዋላ የሚታዩ የኢኮኖሚ “ሳቦታጆች”፣ የሚፈጸሙ ቅጥፈቶች ህብረተሰቡ በንቃት ካልታገለው ትንሽ ተብሎ የሚናቅ እንዳልሆነ ግምት ሊሰጠው ይገባል።” ሲሉ ተናግረዋል። ዶ/ር አብይ ከእርሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ...
Read More »የብአዴን አባላት የህውሃትን አገዛዝ አወገዙ፡፡
የብአዴን አባላት የህውሃትን አገዛዝ አወገዙ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሁለት የተለያዩ ቀናት በተደረገው የባህር ዳር ከተማ አጠቃላይ የብአዴን አባላት ስብሰባ፣ “የህውሃት አገዛዝ በአማራው ላይ ማለቂያ የለሽ ስቃይና ሰቆቃ ለዓመታት ሲያደርስ ቢቆይም፣ክልሉን በሚያስተዳድሩ አድር ባዮች ምክንያት እንዳንናገር ታፍነን ነበር” በማለት አባላቱ የህውሃትን አገዛዝ በድፍረት ሲቃወሙ ተሰምተዋል፡፡ በባህር ዳር ሙሉዓለም አዳራሽ በተደረገው ስብሰባ የክልሉ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ስብሰባውን ...
Read More »በገንዳ ውሃ ከተማ በተከሰተ የአሳት አደጋ 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፡፡
በገንዳ ውሃ ከተማ በተከሰተ የአሳት አደጋ 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በመተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ ከተማ ከሚገኙ ፋብሪካዎች መካከል የህወሃት ሰዎች ንብረት እንደሆነ በሚነገርለት” ካልሚ የሰሊጥ ፋብሪካ” ላይ ሰሞኑን በተከሰተው ከፍተኛ የአሳት አደጋ በሚሊዮን የሚገመት ንብረት ወድሟል፡፡ ፋብሪካውን በበላይነት የሚመሩት አቶ ፍስሃ ጽዬን መሐሪ እንደተናገሩት ከ30 ሽህ ኩንታል በላይ ጥጥና ከ10 ሽህ ...
Read More »በኮማንደ ፖስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ባንተወስን አበበ አሁንም አልተፈታም
በኮማንደ ፖስት ቁጥጥር ስር የሚገኘው ባንተወስን አበበ አሁንም አልተፈታም (ኢሳት ዜና ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ የሆነው ባንተ ወሰን አበበ ቀደም ብሎ በሽብር ወንጀል ተከሶ ኢህአዴግ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ከእስር ቤት የወጣ ቢሆንም፣ በሳምንታት ውስጥ እንደገና ተይዞ ታስሯል። ላለፉት 57 ቀናት በእስር ቤት የሚገኘው ባንተወሰን ፍርድ ቤት አለመቅረቡንና በከፍተኛ ችግር ላይ መሆኑን ወንድሙ ፈቃዱ አበበ ተናግሯል። ባንተ ...
Read More »በጉጂ እና በጌዲዮ ማህበረሰቦች መካከል የሚካሄደውን ግጭት ተከትሎ የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው
በጉጂ እና በጌዲዮ ማህበረሰቦች መካከል የሚካሄደውን ግጭት ተከትሎ የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ባለፈው እሁድ ያገረሸውን ግጭት ተከትሎ ዛሬም የዜጎች ህይወት እያለፈ ነው። በርካታ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ድርጅቶችም ወድመዋል። በኦሮምያና ደቡብ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተለይም በባንቆ ጎትቲ፣ በባንቆ ላሌሳ፣ በባንቆ ጣጣጡ፣ በደገብ ኤደራ፣ በከቾሬ ወረዳ በስቄ፣ በቶሬ እና ሽፎ አከባቢዎች ግጭሬ ...
Read More »መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ወደ ተግባር ለመለወጥ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ
መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ወደ ተግባር ለመለወጥ ዝግጁ መሆኑን ገለጸ (ኢሳት ዜና ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለአለፉት 20 አመታት ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ በመቀየር ከኤርትራ መንግስት ጋር ወዳጅነት ለመመስረት ሲባል፣ “ መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን “ ዛሬ በዋወጣው መግለጫ አስታውቋል። ...
Read More »በኢትዮ-ሶማሊ ክልል ከ100 በላይ ወጣቶች ታሰሩ
በኢትዮ-ሶማሊ ክልል ከ100 በላይ ወጣቶች ታሰሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተነሳ ማግስት፣ የአብዲ አሌ አገዛዝ ከ100 በላይ የሚሆኑ በጅጅጋ ዞን የሚኖሩ ወጣቶችን ይዞ አስሯል። ወጣቶቹ በእስር ቤት ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በክልሉ የሚታዬውን የለውጥ እንቅስቃሴ በመስጋት የህወሃቶችን ድጋፍ ለማግኘት ታች ላይ በማለት የሚገኘው አብዲ ኢሌ፣ በህወሃት በኩል አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግለት ...
Read More »መርጌታ እንደስራቸው አግማሴ እንዲፈቱ ተጠየቀ
መርጌታ እንደስራቸው አግማሴ እንዲፈቱ ተጠየቀ (ኢሳት ዜና ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ በቤትክርስቲያኗ የተክሌ አቋቋም ምስክር ፣ የቤተልሄም ምስክርና ቅኔ መምህር የነበሩት ሊቁ መሪጌታ እንደስራቸው አግማሴ በሃገረ ሰስከታችን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት አግልገሎት ሲሰጡ የቀዩ፣ በጎንደር ከተማም ሃዋርያ ጳውሎስ እየተባለ በሚጠራው የካህናት ማሰልጠኛ በሃገረ ...
Read More »የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ የማኔጅመን አባላት የሙስና ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ የማኔጅመን አባላት የሙስና ወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። (ኢሳት ዜና ግንቦት 28 ቀን 2010 ዓ/ም) እንደ ፎርቹን ዘገባ፣ በፌዴራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ጉዳይ ክፍል፣ ተጠርጣሪዎቹ በስማቸው ያስቀመጡት ገንዘብ ካለ መጠኑ እንዲገለጽለት ለሁሉም የንግድ ባንኮች ደብዳቤ ጽፏል። ፖሊስ-ለንግድ ባንኮቹ በጻፈው በዚህ ደብዳቤ ላይ ስድስት የቀድሞ የልማት ባንክ አመራሮችን ጨምሮ የ30 ሰዎች ሰፍሯል። ቀደም ሲል ባንኩን በፕሬዚዳንትነት ለረዥም ...
Read More »