ኦነግ በምዕራብና ምስራቅ ወለጋ የሚካሄደውን ጦርነት ህዝቡ እንዲያከሽፈው ጠየቀ ድርጅቱ አቶ ለማንና ዶ/ር አብይንም አውግዟል (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ባወጣው መግለጫ በቄለም ወለጋ ውስጥ “ ለምን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንቅስቃሴን ትደግፋላችሁ?” በማለት የጦር ሃይሉ ግዳጅ ወስዶ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጿል። ዘመቻው በኦሮምያ ክልል መስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ትእዛዝና እውቅና እንዲሁም በጄኔራል ገብሬ ...
Read More »Amsterdam
የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች 700 ሜትር ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን ገለጹ
የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች 700 ሜትር ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን ገለጹ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች በባህርዳር ከተማ ተይዞ የተወጣውን ባንዲራ የሚበልጥ ረጅም ባንዲራ በመያዝ ዶ/ር አብይ አህመድ እያደረጉ ላሉት የለውጥ እንቅስቃሴ ድጋፉን ገልጿል። የመተከል ከተማ ነዋሪዎች ፣ በአውራጃቸው የሚፈናቀሉና የሚገደሉ ወገኖች ሰቆቃ ይቁም፣ አገር በጭንቅላት እንጅ በአፈሙዝ አይገዛም የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በመያዝ ወደ ...
Read More »በሲዳማ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የዞኑ አስተዳደሪና ከንቲባው ስልጣን ለቀቁ
በሲዳማ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የዞኑ አስተዳደሪና ከንቲባው ስልጣን ለቀቁ (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ የሲዳማ አመታዊ በአል ጨምበለላ በተከበረበት ወቅት በተቀሰቀው ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ወደ ሃዋሳ ያቀኑት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ በግጭቱ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ በጠየቁት መሰረት የዞኑ አስተዳደሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሃዋሳ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ስልጣናቸውን ለቀዋል። ግለሰቦቹ ለፍርድ ...
Read More »አሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው
አሜሪካና ቻይና የንግድ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የትራምፕ አስተዳደር ቻይና ወደ አሜሪካ በምትልካቸው እቃዎች ላይ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ የቀረጥ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ ፣ ቻይናና ሩስያ ተመሳሳይ እርምጃዎችን ወስደዋል። ቻይና በአለማችን የተከሰተ ታላቁ የኢኮኖሚ ጦርነት ስትል የአሜሪካንን ውሳኔ አደገኝነት ገልጻለች። አሜሪካ 34 ቢሊዮን ዶላር በሚደርስ የቻይና ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ ጭማሪ ስታደርግ፣ ...
Read More »ዶ/ር አብይ አህመድ በሶማሌው ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አብዲ ኢሌ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ይሰጡ ዘንድ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ
ዶ/ር አብይ አህመድ በሶማሌው ርዕሰ መስተዳድር በአቶ አብዲ ኢሌ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ ይሰጡ ዘንድ ሂውማን ራይትስ ዎች ጠየቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ባወጣው መግለጫ በክልሉ በሚገኘው የኦጋዴን እስር ቤት ውስጥ በተፈጸሙት አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ምርምራ ማካሄዱን በመጥቀስ፣ የደህንነት ሰራተኞችና ባለስልጣናት ተጠያቂ እንዲሆኑ ያደርጉ ዘንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጠይቋል። “የሞቱትን እንመስላለን” በሚል ርዕስ ...
Read More »ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7ን በሽብርተኝነት የፈረጀው ፓርላማ ፍረጃውን አነሳ
ኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7ን በሽብርተኝነት የፈረጀው ፓርላማ ፍረጃውን አነሳ (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ሟቹ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በፓርላማው በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ ያስደረጓቸው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች የሆኑት፣ የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻ አውጭ ግንባርና አርበኞች ግንቦት7፣ ዛሬ በዚያው ፓርላማ ፍረጃው እንዲነሳላቸው ተደርጓል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ቃል በገቡት መሰረት የተላለፈው ይህ ውሳኔ ፣ የሃይል ...
Read More »በመልካ ጀብዱ በተነሳ ብሄር ተኮር ግጭት ሰዎች ተጎዱ
በመልካ ጀብዱ በተነሳ ብሄር ተኮር ግጭት ሰዎች ተጎዱ (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) በድሬዳዋ ከተማ ዙሪያ በምትገኘው መልካ ጀብዱ ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓም በኢሳ የሶማሊ ጎሳዎችና በጉርጉራ የኦሮሞ ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት አንድ ሰው ሲገደል ፣በርካታ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። ግጭቱን የድሬዳዋና የአካባቢውን ስልጣን ለመቆጣጠር ያለሙ የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስነሱት ነዋሪዎች ተናግረዋል። ግጭቱን ተከትሎ በተነሳው አመጽ አህመድ አብዱልሀኪም ...
Read More »ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት መልዕክት መላካቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ።
ሰሞኑን በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት መልዕክት መላካቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘገበ። (ኢሳት ዜና ሰኔ 28 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑባቸው የድንበር አካባቢዎች ግጭት ተቀስቅሶ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች መሞታቸውና በርካቶች መጎዳታቸው ይታወቃል። የሱዳን ታጣቂዎች ድንበር አሳብረው በመግባት ” የእርሻ መሬት ይገባኛል” በሚል በፈጸሙት ጥቃት የተቀሰቀሰው ግጭት በሚቆምበት እና በሀገራቱ ድንበሮች አካባቢ ዘላቂ ...
Read More »በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከግድያ ሙከራ ጀምሮ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያሴሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው
በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ከግድያ ሙከራ ጀምሮ የተለያዩ ሴራዎችን ሲያሴሩ የነበሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚካሄዱ ግጭቶችን በማስተባበር እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ በዶ/ር አብይ አህመድና ሌሎችም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ላይ የግድያ ሙከራ ለማድረግ ሲያቀናብሩ ከነበሩት ሰዎች መካከል የተወሰኑት መያዝ መጀመራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በአሁኑ ሰዓት መቀሌ ከሚገኘው ከቀድሞው የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ...
Read More »በአማሮ ወረዳና በጉጂ መሃል ያለው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ታሰማ
በአማሮ ወረዳና በጉጂ መሃል ያለው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ታሰማ (ኢሳት ዜና ሰኔ 27 ቀን 2010 ዓ/ም) አንድ አመት ያስቆጠረዉ ግጭት ሰሞኑን ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በዳኖ፤ ደርባ እና ቲፋቴ ግጭቱ ተባብሶ የሰዎች ህይወት አልፏል። ዳኖ በሚባል ቀበሌ ከብቱን በመጠበቅ ላይ የነበረ ደመቀ ደባሱ የሚባል የ44 ዓመት ጎልማሳ አርሶአደር ወዲያውኑ ሲገደል፣ በቲፋቴና ደርባ ቀበሌዎች ደግሞ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት እኩለ ቀን ጊዜ ...
Read More »