በሲዳማ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የዞኑ አስተዳደሪና ከንቲባው ስልጣን ለቀቁ

በሲዳማ ዞን የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የዞኑ አስተዳደሪና ከንቲባው ስልጣን ለቀቁ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) በቅርቡ የሲዳማ አመታዊ በአል ጨምበለላ በተከበረበት ወቅት በተቀሰቀው ግጭት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ወደ ሃዋሳ ያቀኑት ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ በግጭቱ እጃቸው ያለበት ባለስልጣናት ስልጣን እንዲለቁ በጠየቁት መሰረት የዞኑ አስተዳደሪ አቶ አክሊሉ አዱላ እና የሃዋሳ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ ስልጣናቸውን ለቀዋል።
ግለሰቦቹ ለፍርድ ይቅረቡ አይቅረቡ የታወቀ ነገር ነገር የለም።