Amsterdam

በጅግጅጋ ወጣቶች በአብዲ ኢሌ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ አደረጉ

በጅግጅጋ ወጣቶች በአብዲ ኢሌ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ አደረጉ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) ወጣቶቹ ተቃውሞዋቸውን ያሰሙት የአብዲ ኢሌን ፍጹማዊ አገዛዝ በመቃወም እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ተጠርጥረው የተሳሩ ዜጎች እንዲፈቱ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ እስር ቤቶች እንዲዘጉ ለመጠየቅ ነው። ወጣቶቹ ተቃውሞአቸውን በሚያሰሙበት ወቅት አብዲ አሌ ወታደሮቹን ልኮ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ማድረጉን አቶ አሊ አብዲ ሃሰን ከጅግጅጋ ገልጸዋል። በጥቃቱ እስካሁን የደረሰውን ...

Read More »

በባሌ ጎባ አንጻራዊ መረጋጋት ቢታይም አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ነዋሪዎች ገለጹ

በባሌ ጎባ አንጻራዊ መረጋጋት ቢታይም አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ነዋሪዎች ገለጹ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ ደም አፋሳሽ የነበረው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ አንጻራዊ መረጋጋት ታይቶበታል። ባለፈው ረቡዕ የዞኑ ባለስልጣናት የባሌ ገበሬዎች አመጽ መሪ የነበሩትን የሃጂ አደም ሳዶን ሃውልት ለማቆም በሚል ህዝቡን አወያይተው የነበረ ሲሆን፣ በእለቱ አብዛኛው ተሰብሳቢ ሃውልቱ ቢቆም ...

Read More »

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ባደረጉት ዉይይት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባረው የነበሩ መምህራን ወደሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ አስታወቁ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም )በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከመላው ኢትዮጵያ ከሃምሳ ዩኒቨርሲቲዎች ከተወጣጡ 3 ሽህ 175 የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር በአገሪቱ የከፍተኛ የትምህርት ጥራት፣ አገራዊ አንድነት፣ አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለ ብልሹ አሰራር እና ...

Read More »

በሳውላ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው

በሳውላ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጎፋ ሳውላ የተካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ ተከትሎ ፣ ሰልፉን አስተባብራችሁዋል የተባሉ ሰዎች እየተደበደቡ ታስረዋል። በሰልፉ ዋዜማ እለት አንድ እናት እስከ ልጃቸው የተደበደቡ ሲሆን፣ ከሰልፉ በሁዋላ ደግሞ በርካታ ወጣቶች በባለስልጣናት ድብደባ ደርሶባቸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት 5 ሰዎች ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ቤተሰብ እንዳይጠይቁዋቸው ...

Read More »

በሃረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት በተገኘው አጽም የተጠረጠሩ የፖሊስ አዛዦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔ ተላለፈ

በሃረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት በተገኘው አጽም የተጠረጠሩ የፖሊስ አዛዦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔ ተላለፈ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት የተገኙትን አጽሞች ተከትሎ ዛሬ አርብ ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓም የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አበበ መብራቱ ፣ ም/ል ፕሬዚዳንት ጋቢሳ ተስፋዬ፣ ሃብሊ ሊቀመንበር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ በኦህዴድ የሃረሪ ...

Read More »

በርካታ የጌዲዮ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረሩ

በርካታ የጌዲዮ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቅርቡ በጉጅና ጌዲዮ ማህበሰረቦች መካከል የነበረውን ግጭት ተከትሎ በተለያዩ ያሃላፊነት ደረጃ ላይ የነበሩ የጌዲዮ ማህበረሰብ የመንግስት ሰራተኞች በጉጂ ዞን ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተባረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት በሰዎች እና በንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ፣ የብሄረሰቡ ተወላጆች ከስራ መባረራቸው ተቀባይነት የለውም። ከተባረሩት መካከል ከ 30 በላይ ...

Read More »

በሽንሌ ዞን በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በሽንሌ ዞን በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) ላለፉት 5 ወራት በሺንሌ ዞን የተጀመረው ተቃውሞ እየቀጠለ ባለበት ሰዓት ፣ የአብዲ ኢሌ አስተዳደር የሚወስደውም እርምጃ በተመሳሳይ መልኩ እየጨመረ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሻለቃ አሊ ሳምሪ ሰገድ እንደተናገሩት ከ3 ቀናት በፊት አዲጋላ ላኢ አንዲት ሴት መገደሏንና ሌላ ሴት ደግሞ መቁሰሏን ተናግረዋል። ...

Read More »

ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ማስወጣት ጀመረች

ኤርትራ ጦሯን ከኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ማስወጣት ጀመረች ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )ሬውተርስ እንደዘገበው ኤርትራ ጦሯን ከድንበር ማስወጣት የጀመረችው የቀረበውን የእርቅ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ፍላጎት ለማሳየት ነው። ምክትል ኢታማዦር ሹሙ ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ መንገድ ጦሯን ከድንበር ለማስወጣት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን ውሳኔ እየጠበቁ መሆናቸውን የኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል። ኤርትራ ጦሯን ማስወጣቷ በአካባቢው ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቁልፍ እርምጃ ...

Read More »

የጎፋ ህዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ጠየቀ

የጎፋ ህዝብ ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ጠየቀ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )በሳውላ ዶ/ር አብይ አህመድን ለመደገፍ በተጠራው ሰልፍ ላይ ህዝቡ ያቀረባቸው የመብትና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች እንዲሟሉለት ጠይቋል። የአስተዳደር ወሰን ፣ የሹመት እንዲሁም መንገድን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ጥያቄያቸውን መንግስት እንዲፈታላቸው ነዋሪዎች ጥያቄ አቀርበዋል። ህዝቡ ለውጡን ለሚመሩት የኢህአዴግ መሪዎች እና ለተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ያለውን ድጋፍም የተለያዩ ፎቶዎችን በመያዝ ድጋፉን ገልጿል።

Read More »

የመንግስት ባለስልጣናትን ሃብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ_በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ።

የመንግስት ባለስልጣናትን ሃብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ_በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እዬልኝ ሙሉ ዓለም እንደገለጹት የኮሚሽኑ ተግባር ሀብትን መመዝገብ ብቻ ሳይሆን ፣ ሹመኛው ወይም ሠራተኛው ያስመዘገበው ሀብት ትክክል ነው? ወይስ አይደለም?የሚለው መረጋገጥ ጭምር እንደሆነ በመጥቀስ፤ መዝግቦ እና ማጣራት አድርጎ ያረጋጠውን ሀብት ለሕዝቡ ...

Read More »