በርካታ የጌዲዮ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረሩ

በርካታ የጌዲዮ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረሩ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቅርቡ በጉጅና ጌዲዮ ማህበሰረቦች መካከል የነበረውን ግጭት ተከትሎ በተለያዩ ያሃላፊነት ደረጃ ላይ የነበሩ የጌዲዮ ማህበረሰብ የመንግስት ሰራተኞች በጉጂ ዞን ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተባረዋል።
ነዋሪዎች እንደሚሉት በሰዎች እና በንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ፣ የብሄረሰቡ ተወላጆች ከስራ መባረራቸው ተቀባይነት የለውም። ከተባረሩት መካከል ከ 30 በላይ መምህራን፣ የግብርና ሰራተኞች፣ መሃንዲሶች፣ ጤና ረዳቶች፣ የደን ባለሙያዎች፣ የእንስሳት ሀኪሞች፣ አካውንታንቶችና የተለያዩ ድርጅቶች ስራ አስኪያጆች ይገኛሉ።
ግጭቱን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀላቸው፣ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መሞታቸው እና ለአካል ጉዳት መዳረጋቸው ይታወቃል።