Amsterdam

የወልቃይት የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባል ታሰሩ

ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዳንሻ ይኖሩ የነበሩት የወልቃይት የአማራ ማንነት የኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ግዛው በሬ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያና ዛቻ ሲፈጸምባቸው ከቆዩ በሁዋላ ትናንት ማክሰኞ ሶረቃ ከተማ በስራ ላይ እያሉ  በትግራይ ክልል የደህንነት አባላት ታፍነው ተወስደዋል። አቶ ግዛው በዳንሻ መኖር ስላልቻሉ ወደ ሰሮቃ ሄደው በግል ስራ ላይ ይተዳደሩ ነበር። ግለሰቡ እስካሁን ድረስ የት ቦታ እንደታሰሩ የታወቀ ...

Read More »

የሙስና ኮሚሽኑ ሙሰኞችን እየደበቀ ነው የሚል ትችት ቀረበበት

ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የጸረሙስና አውደጥናት ላይ እንደተገለጸው የአማራ ክልል ጸረሙስና ኮሚሽን ስራውን በአግባቡ ከመስራት ይልቅ በርካታ ሙሰኞችን ስራ በመደባበቅ ላይ መሆኑን ተሳታፊዎች አጋልጠዋል፡፡ “ለልማት፣ ለሰላምና ለደህንነት በሙስና ላይ የተባበረ ክንድን ማንሳት!!” በሚል መሪ ቃል ለ12ኛ ጊዜ በሚከበረው የጸረሙስና ቀን ጥናት አቅራቢው እንደተናገሩት በአማራ ክልል ከሚገኙ መንግስታዊ መስሪያቤቶች ውስጥ በፌደራል ደረጃ ...

Read More »

የሃዋሳ ፔፕሲ ኮላ እና የድሬደዋ ኮካ ኮላ ፋብሪካዎች  እንዲዘጉ ተደረገ

ታኅሣሥ ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃዋሳው ፔፕሲ ኮላ እና የድሬደዋ ኮካ ኮላ ፋብሪካዎች ተዘግተው ለሽያጭ የተስራጩት ምርቶቻቸው እንዲሰበሰቡ ሲል ንግድ ሚንስቴር የእገዳ ትእዛዝ መመሪያ አውጥቷል። የሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ንብረት የሆነው የሃዋሳ ፔፕሲ ፋብሪካ እና የምስራቅ አፍሪካ ቦትሊንግ ንብረት የሆነው የድሬዳዋው ኮካ ኮላ ምርቶቻቸው የጥራት ደረጃቸውን ሳይጠብቁ  ለተጠቃሚው ለገበያ መቅረባቸውን ሚኒስቴሩ ጠቅሷል። የሃዋሳ ሚሊኒየም ፔፕሲ ፋብሪካ ...

Read More »

በአፋር የሎጊያ ከተማ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ማክሰኞ በአፋር ክልል በሌጊያ ከተማ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከመማር ማስተማር ሂደት ችግና ከመልካም አስተዳዳር እጦትና ጋር በተያያዘ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ሰልፉን ተከትሎ ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽመዋል። ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ። አካባቢው በወታደሮችና በልዩ ሃይል አባላት እየተጠበቀ መሆኑን የደረሰን መረጃ ...

Read More »

ኢህአዴግ “ገምግሞ ከስልጣን ያወረዳቸውን ባለስልጣናት” ወደ ትምህርት ሊልክ ነው

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ በጥልቅ ትሃድሶ ስም  በሙስና የተዘፈቁ ያላቸውን 479 የአማራ እና የኦሮምያ ክልሎች የወረዳ እና የቀበሌ ባለስልጣናት ወደ ትምህርት ሊላከቸው መሆኑን ምንጮች ገለጹ። “ኢህአዴግ ህዝብን ያስቸገሩ እና ያመረሩ ፣ የመልካም አሰተዳደር ችግር ያለባቸው እና ስርአቱን አደጋ ውስጥ የጣሉ ናቸው” በሚል ከአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች የተለዩትን ባለስልጣናት ማባረሩ “አመራሮቹ ወደ ተቃዋሚዎች ገብተው ለስርዓቱ ...

Read More »

በለገዳዴና ለገጣፎ አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታሰሩ

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ትናንት ሰኞ ከምሽት ጀምሮ ወታደሮች በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ለገጣፎ፣ ለገዳዲ እና ሌሎችም አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። በእሬቻ በአል ወቅት ወረቀት ሲበትኑ የነበሩትን አጋልጡ እየተባሉ የአካባቢው ሰዎች ስቃይ ሲደርስባቸው ቆይቷል። በእስር ላይ የነበሩ 10 ሺ ወጣቶች መለቀቃቸው እንደተነገረ የተጀመረው የእስር ዘመቻ፣ ትናንት ምሽት ተጠናክሮ ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ በጽኑ ታሞ ባቱ ሆስፒታል ገባ

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታህሳስ18 ቀን 2009 ዓ.ም በፀና ታሞ በአንፑላንስ ተጭኖ ዝዋይ በሚገኘው ባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል። በተደጋጋሚ ጊዜያት ከቤተሰቦቹ እና ሕጋዊ ጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ሲደረግ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት በሚገቡበት ወቅት በአቅራቢያው የሚገኙትን ...

Read More »

በጎንደር በህዝብ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ አደጋ 10 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 15 ሰዎችን ጭኖ ከጎንደር  ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽካርካሪ ጠዳ ከተማ አካባቢ ሲደርስ በመገልበጡ 10 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 4 ሰዎች ደግሞ በጽኑ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል። የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ሲኖ ትራክ እየተባለ በሚጠራ የጭነት ተሽከርካሪ ተመትቶ ሳይገለበጥ እንዳልቀረ ወኪላችን ገልጿል። አብዛኞቹ ሟቾች ነገ የሚከበረውን ወንቅሸት ገብርኤል ለማክበር በመጓዝ ...

Read More »

በባህርዳር እና በዙሪያዋ ወረዳዎች ተይዘው ከታሰሩት መካከል በሺዎች የሚቆጠሩት ፍድር ቤት ሳይቀርቡ ለወራት መታሰራቸው ታወቀ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከነሃሴ ፣ 2008 ዓም ጀምሮ በባህርዳር ዙሪያ በሚገኙ ወረዳዎች ማለትም በባህርዳር ዙሪያ፣ ጎንጂ ቆለላ፣ ይልማና ዴንሳ፣ ሜጫ፣ አቸፈር፣ ባህርዳርና ደራ ወረዳዎች ተይዘው ከታሰሩ ከ4 ሺ በላይ ወጣቶች መካከል 1 ሺ 500 የሚሆኑት እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በባህርዳር ወህኒ ቤት ታስረው ለስቃይ እየተዳረጉ ነው። እስረኞቹ በከፍተኛ የውሃ እና ህክምና ችግር እየተሰቃዩ ...

Read More »

በአፋር ክልል የተተከለው ራዳር መነሳቱ ታወቀ

ታኅሣሥ ፲፯ (አሥራ ሠባት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጥቶባቸው ከተተከሉት ራዳሮች መካከል በአፋር ክልል ዱብቲ አካባቢ የተተከለው ራዳር ሳምንት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ እንዲነቀል ተደርጓል። እርምጃው ለምን እንደተወሰደ ባይታወቅም፣ ዘገባው በኢሳት ከተላለፈ በሁዋላ እንዲነሳ መደረጉ ምናልባትም ከመረጃው ከመውጣት ጋር የተያያዘ ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ በማድረግ ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የርቀት መቆጣጠሪያ ...

Read More »