በለገዳዴና ለገጣፎ አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታሰሩ

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጡት ትናንት ሰኞ ከምሽት ጀምሮ ወታደሮች በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ ለገጣፎ፣ ለገዳዲ እና ሌሎችም አካባቢዎች በርካታ ወጣቶች ታፍሰው ወደ እስር ቤት ተወስደዋል።

በእሬቻ በአል ወቅት ወረቀት ሲበትኑ የነበሩትን አጋልጡ እየተባሉ የአካባቢው ሰዎች ስቃይ ሲደርስባቸው ቆይቷል። በእስር ላይ የነበሩ 10 ሺ ወጣቶች መለቀቃቸው እንደተነገረ የተጀመረው የእስር ዘመቻ፣ ትናንት ምሽት ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ የአካባቢው ወጣቶች ወደ ሌሎች አካባቢዎች ለመሰደድ ተገደዋል።

በኢትዮጵያ እስር ቤቶች የሚገኙ ወጣቶች ቁጥር በውል አይታወቅም። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከ50 ሺ በላይ ወጣቶች በመላው አገሪቱ ታስረው ይገኛሉ።