በአፋር የሎጊያ ከተማ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ታኅሣሥ ፲፰ (አሥራ ስምንት)ቀን ፳፻ / ኢሳት ዜና :- ዛሬ ማክሰኞ በአፋር ክልል በሌጊያ ከተማ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከመማር ማስተማር ሂደት ችግና ከመልካም አስተዳዳር እጦትና ጋር በተያያዘ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን፣ ሰልፉን ተከትሎ ፖሊሶች ወደ አካባቢው በመድረስ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽመዋል።

ተማሪዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውን ይገልጻሉ። አካባቢው በወታደሮችና በልዩ ሃይል አባላት እየተጠበቀ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በክልሉም ሆነ በሎጊያ ከተማ ስራ የሚገኘው በቤተሰብ ትስስር መሆኑ፣ በአካባቢያቸው በሚገነባው የስኳር ፕሮጀክት አፋሮች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ቢባልም፣ በተግባር የሚታየው ሌላ መሆኑ፣ በአነስተኛ ስራ ላይ ተቀጥረው የነበሩት የአፋር ተወላጆች ከስራ መባረራቸው እንዲሁም በአፋር ህዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነቸው አርቲስት መፋራ ሙሃመድ ለሶስት ወራት ያለፍርድ መታሰሩዋ በአካባቢው ህዝብ ዘንድ ቅሬታ ሲፈጥር ቆይቷል።

የአካባቢው ሹሞች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ሰልፍ በማድረጋችሁ ተጨማሪ እርምጃ ይወሰድባችሁዋላ እያሉ በማስፈራራት ላይ መሆናቸውም የደረሰን ዜና ያመለክታል።