.የኢሳት አማርኛ ዜና

አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጡ

ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጩ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ አዲስ ነገር አለመጠበቃቸውን ሲናገሩ፣ እውቁ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ደግሞ፣ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር “ከእነስታይላቸው ” አቶ መለስን መስለዋል ብለዋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከፓርላማ አባላቱ ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች መልሶችን የሰጡት፣ የቀድሞው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር  ፎቶ ግራፍ ፊት ለፊታቸው ተሰቅሎ በሚታይበት ሁኔታ ነው። አዲሱ ጠቅላይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ኢቲቪን ፦”የቆሻሻ ፕሮፓጋንዳ ፋብሪካ” ሲል ገለጸው

ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት  ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ሰሎሞን መንግስት  በውሸት ፕሮፓጋንዳ በመማረሩ ሥራውን በፈቃዱ መልቀቁን አስታወቀ። ጋዜጠኛ ሰሎሞን  መንግስት ባለፉት ዓመታት  በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የእንግሊዝኛው ፕሮግራም ክፍል ባልደረባ በመሆን የተለያዩ ዘገባዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል። በእንግሊዝኛው ፕሮግራም  የተሻለ አቅም ካላቸው ጋዜጠኞች መካከል አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት  ጋዜጠኛ ሰሎሞን ፤በድርጅቱ የ ኢዲቶሪያል ነፃነት አለመኖሩና ጋዜጠኞች ዘወትር ፕሮፓጋንዳ እንዲሠሩ ...

Read More »

በድሬዳዋ፣ ሀርርና ጅጅጋ የተፈጠረው የኤሌክትሪክ መቋረጥ በምሰሶዎች ላይ በተፈጠረ ስርቆት ነው ተባለ

ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት እንዳስታወቀው ወለንጨቲ አካባቢ በኤሌትሪክ ምሶሶ ላይ በተፈጸመው ዝርፊያ  5 ምሶሶዎች ወድቀዋል። በዚህም የተነሳ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በ ድሬዳዋ፣ ሀረርና ጅጅጋና በሌሎችም ትልልቅ ከተሞችና የገጠር መንደሮች ኤሌትሪክ ተቋርጦባቸዋል። በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ስራዎች እንዲቋረጡም ከማስገደዱ በተጨማሪ በኤሌትሪክ የሚሰሩ የውሀ ፓንፖች ስራቸውን በማቋረጣቸው  የአካባቢው ነዋሪዎች መቸገራቸውን መንግስት አምኗል። በወለንጨቲ የተፈፀመው የኤሌትሪክ ምሰሶ ስርቆት ከ35 ሚሊዮን ብር ...

Read More »

አቦይ ስብሀት የፊታችን ኦክቶበር 20 ጀርመን ይመጣሉ

ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት)መስራች አባል የሆኑትን በአቶ መለስ ጊዜ ከከፍተኛ የድርጅቱ ቦታዎች ተገፍተው የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በመጪው መስከረም 20 በጀርመን-ቡንደስታግ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ተመለከተ። በነባሮቹ የድርጅቱ አባላት ዘንድ <አቦይ>ተብለው የሚጠሩት አዛውንቱ አቶ ስብሀት ነጋ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ  በድርጅቱ ውስጥ ወደ ቀድሞ ተሰሚነታቸውና አድራጊ ፈጣሪነታቸው እየተመለሱ እንደሆነ ...

Read More »

የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ጉባኤ በቨርጂኒያ ተካሄደ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የመጀመሪያው የኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች ጉባኤ በአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ ተካሄደ። ትናንት እሁድ፤ መስከረም 4 ቀን በተካሄደው ጉባኤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከተለያዩ የአሜሪካን ከተሞች የመጡ ኢትዮጵያዊያን የተገኙ ሲሆን፤ ለኮንግረስና ለሲቲ ካውንስል የሚወዳደሩ እጩዎች ቀርበው ንግግር አድርገዋል። ኮንግረስማን ሞራን ግሪፊዝ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ችግር እንደሚረዱ ገልጸው፤ ከኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን ጎን እንደሚቆሙ ገልጸዋል። የአሌክሳንድሪያው ከንቲባ ዊሊያም ዲ ኢዩልም ...

Read More »

ጅጅጋ፤ ሀረርና ድሬዳዋ ካለፉት ስድስተ ቀናት ወዲህ ጨለማ ውስጥ ናቸው

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ምስራቅ ከተማዎች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው የታወቀ ሲሆን፤ የደብረዘይት ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት 7 ቀናት የውሀ አገልግሎት እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ከድሬዳዋ ጅጅጋና ሀረር ከተሞች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሀረር፤ ድሬዳዋና ጅጅጋ ከተሞች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት አልነበራቸውም። የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አመት ለጅቡቲ 20 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ መሸጥ መጀመሩን መናገሩ የሚታወስ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ውስት የሸሪአ ሕግ መጫን ጨርሶ የማይታሰብ ነው ተባለ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሸሪያ ሕግ እንዲታወጅ የኢትትዮጲያ ሙስሊሞች አለመጠየቃቸውን፤ በኢትዮጲያ ያለው ነባራዊ ሁኔታም ይህንን ጨርሶ እንደማይፈቅድ፤ አንድ የእስልምና ሐይማኖት ምሁር ገለጹ። በሸሪያ ሕግ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን የሰሩትና የፈርስት ሒጅራ ፋውንዴሽን ኢማም የሆኑት ሼህ ካሊድ መሐመድ ኡመራ ለኢሳት እንደተናገሩት ሸሪያ ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሙስሊሙ ላይ ብቻ እንደሆነም አመልክተዋል። እስልምና መቻቻልን እንደሚሰብክ አጥብቀው የተናገሩት ሼህ ካሊድ መሐመድ ኡመር፤ ...

Read More »

ቤታቸው የፈረሰባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 በተለምዶ አሮጌው ቄራ በሚባለው  አካባቢ ላለፉት 20 እና 30 አመታት የቀበሌ እና የወረዳ ህጋዊ እውቅና ኖሮአቸው በመጠለያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 51 አባዎራዎች እና እመዎራዎች ባለፈው ቅዳሜ ያለምንም ምትክ  ቤታቸውን አፍርሰው የቤት ቁሳቁሳችንን ሁሉ ወረሱብን በማለት በአራዳ ክፍለከተማ አስተዳዳሪ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ፖሊስ ሰልፉን በትኖ ...

Read More »

ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሥነምግባር ችግር ከተባረሩ በኋላ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትዕዛዝ ያለጨረታ የደቡብ ክልል መገኛኛ ብዙሃን የቴክኒክ ሥራን ተረክበው በአቋራጭ ከባለሃብት ጎራ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ፣ ዛሚ በተሰኘው ራዲዮ ጣቢያቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአጃቢ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ሲሟገቱ ውለዋል፡፡ ሰሞኑን የወጡ ጋዜጦች ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን ለአቶ ኃይለማርያም አላስረከቡም በሚል ያወጡትን ተከታታይ ዘገባዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ከ 31 ዓመት በሁዋላ ለአፍሪካ ዋኝጫ ውድድር አለፈ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት የብሔራዊ ቡድኑን ውጤት የፖለቲካ መነገጃ ለማድረግ መሞከሩ ብዙዎችን ቅር አሰኝቷል። በቅጽል ስሙ<ዋሊያ>ተብሎ የሚጠራው የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ትናንት በ አዲስ አበባ ስታዲየም ባደረገው የመልስ ጨዋታ ሁለት ለባዶ በማሸነፍ ነው ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማለፉን ያረጋገጠው። ከወራት በፊት ሁለቱ ቡድኖች ለመጨረሻው የማጣሪያ ጨዋታ አንድ ላይ ሲመደቡ፤ በሁለቱም አገሮች ዘንድ የደስታ ስሜት ...

Read More »