ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ካሚል ሸምሱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ኡላማዎችን ምክር ቤትን በደንቡ ያልተሾሙና መርጫ ለማስተባባር ስልጣን የሌላቸው ናቸው በማለት ምክር ቤቱ እንዲታገድና እንዲበተንና ምርጫ እንዳይደረግ ይወሰንልን በማለት መክሰሳቸው ይታወሳል። ዳኛ አምባቸው ታረቀኝ መስከረም 23 ቀን 2005 ዓም በሰጡት ትእዛዝ ፍርድ ቤቱ በሀይማኖት ጉዳይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያዊያን ሴቶች ላይ የሚፈፀመው ግፍ አስደንጋጭ ደረጃ ደርሷል
ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አራሷ ፤ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በሁዋላ ፍርድ ቤት ቀረበች። ዱባይ ውስጥ በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ሴት በወለደች በማግስቱ ከህፃኗ ጋር ወህኒ ቤት መውረዷን <ሰቨን ዴይስ ኢን አቡዳቢ>የተሰኘ ድረ-ገጽ ዘገበ። ኢትዮጵያዊቷ በወለደች በሰዓታት ውስጥ በዱባይ ፖሊስ የታሰረችው፤ ከጋብቻ ውጪ በመውለድ የ አገሩን ህግ ጥሳለች ተብላ ነው። ኢትዮጵያዊቷ ሴት ልጇን የወለደችው ከባንግላዴሸዻዊ ሾፌር ጓደኛዋ ...
Read More »በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ ባደረጉት ሰልፍ የኖርዌይ መንግስት በሰብአዊ መብት ረገጣ የሚታወቀውን የኢህአዴግ መንግስት መደገፉን እንዲያቆምና በኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ላይ ያለውን አቋም ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሀፊ የሆኑት አቶ ቢኒያም ካሳ ለኢሳት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ መንግስት በሰብአዊ መብቶች ጥሰቱ የሚታወቅ ቢሆንም የኖርዌይ መንግስት ግን አሁንም እርዳታውን ቀጥሎአል የኖርዌይ መንግስት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ለመመለስ ...
Read More »ከ200 ሺህ በላይ የኦሞ ሸለቆ ነዋሪዎች ለረሀብ ተጋልጠዋል
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል” የተሰኘ ዓለማቀፍ ድርጅት በታችኛው የኦሞ ሸለቆ በመንግስት ከመሬታቸው የተፈናቀሉ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች ለረሀብ ተጋልጠዋል አለ። በታችኛው የኦሞ ሸለቆ በመንግስት አስገዳጅነት ከመሬታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች አርሰውም አድነውም ለመብላት ባለመቻላቸው በረሀብ ላይ መሆናቸው ተገለጠ:: በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ሞታቸውን እየተጠባበቁ ነው ተብሎል:: ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ከትላንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ አለም ከረሀብ ...
Read More »አቶ ግርማ ሰይፉ ለኢትዮጵያ መንግስት የእንወያይ ጥሪ አቀረቡ
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብቸኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፤ መንግስት ከመድረክ ጋር እንዲወያይ ጥሪ አቀረቡ። በኢትዮጲያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ፤ መድረክ ከመንግስት ጋር በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለመወያየት ይችል ዘንድ ጥሪ አቀረቡ። የመድረክ ብቸኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ፤ መንግስት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ለመወያየት ፈቃደኛነቱን እያሳየ፤ ከሰላማዊ ...
Read More »የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀቱ መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በሀዲድ አምራችነት የሚሳተፍበት የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም ከአውሮፓ ኀብረት የ114 ኪሎሜትር የባቡር ሐዲድ በአዲስ መልክ ለመገንባት ለኢትዮጽያ መንግስት የተሰጠው ገንዘብ በትትክክል ሥራ ላይ አለመዋሉን ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅት የተገኘ መረጃ አመልክቷል፡፡ ገንዘቡ በዕርዳታ መልክ ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት መሰጠቱን ያስታወሱት ምንጮቹ ከ114 ኪሎሜትር ውስጥ ...
Read More »ከኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ጋር ተያይዞ በድሬዳዋ የዋጋ ግሸበት በአስደንጋጭ ፍጥነት እየጨመረ
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምሥራቁ የኢትዮጵያ ክፍል መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ከባድ ተሸካሚ መስመር መዘረፍ በኃላ መብራት ባጣችው በድሬዳዋ ከተማ የሸቀጦች ዋጋ በአስፈሪ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች አረጋገጡ፡፡ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከምሸቱ አንድ ሰዓት አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ያስታወሱት ነዋሪዎቹ ከዚያ በኃላ በከተማዋ የመጠጥ ውሃ መጥፋቱን ተናግረዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የአንድ ...
Read More »በቋራ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ስላልተከፈላቸው ስራ እያቆሙ ነው
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በቋራ ወረዳ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች የመስከረም ወር ደሞዝ በወቅቱ ስላልደረሰላቸው ትናንትና ዛሬ የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል። ተቃውሞአቸውንም ለመንግስት ባለስልጣናት አቅርበዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ መምህር ለኢሳት እንደገለጡት ፣ በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች መምህራን ከሀምሌ ወር ጀምሮ ደሞዝ ያልተከፈላቸው በመሆኑ፣ “ካልበላን አንሰራም” በሚል ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋትና ተማሪዎችን ለመበተን ተገደዋል። የመንግስት ባለስልጣናት መምህራን ስራ ...
Read More »አል-አሙዲ በጨረታ ላሸነፉባቸው ድርጅቶች ክፍያ አልፈጸሙም
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለአፍሪካ ዋንጫ ላለፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 5 ሚሊዮን ብር ለመሸለም ቃል የገቡት ሼክ አል አሙዲ ፤ከሸሪኮቻቸው ጋር በመሆን በጨረታ ላሸነፉዋቸው ድርጅቶች የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ክፍያ ሊፈጽሙ አለመቻላቸው ተዘገበ። ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ አራት የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ለመግዛት የጨረታ አሸናፊነታቸው የተገለጸላቸው የሼክ መሐመድ አል አሙዲና ሸሪኮቻቸው ኩባንያዎች የቅድሚያ ክፍያ ጊዜ ቢራዘምላቸውም፣ በተፈቀደላቸው ...
Read More »መንግስት በቀጣዩ ፓትሪያሪክ ምርጫ ዙሪያ ላይ እጁን እያስገባ ነው ተባለ
ጥቅምት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“የቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ጉዳይ ከእርቅ እና ከአንድነት በኋላ እንጂ በችኮላ መሆን እንደሌለበት አጽንዖት እየተሰጠው ባለው በአሁኑ ወቅት; የየራሳቸውን ወገን “ፓትርያርክ” አድርገው ለማስሾም ፍላጎት ያላቸው የተለያዩ ቡድኖች፣ በይፋ ብቅ ማለት መጀመራቸውን በዝርዝር የዘገበው ደጀ-ሰላም ነው። እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ፤ ቀጣዩን የፓትርያርክ ምርጫ አስመልክቶ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ውስጥ በስፋት እጁን ያስገባው መንግስት ነው። የሙስሊሙ ህብረተሰብ ...
Read More »