ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር አሁንም እንዳልተረጋጋ እየተነገረ ሲሆን፤ የድርጅቱ አመራር አባላት በመስከረም አጋማሽ ተጀምሮ ያልተቋጨውን ስበስባ ለመቀጠል አዳማ መክተታቸው ታውቋል። ከኢትዮጵያ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ ከወረዳ ጀምሮ የሚገኙት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አባላትም በዚህ ስበሰባ እንደተካከቱ ለማወቅ ተችሏል። ቀደም ሲል በአቶ አባዱላ ገመዳ፤ ኩማ ደመቅሳና ጁነዲን ሳዶ ይመሩ የነበሩት ሶስት አንጃዎች ወደአራት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሰመጉና የሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር ገንዘብ እንዲወረስ የተወሰነው ውሳኔ ጸና
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፤ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ) እና የኢትዮጵያ ሴቶች የህግ ባለሙያዎች ማህበር ገንዘብ እንዲታገድና እንዲወረስ በበታች ፍ/ቤቶች የተወሰነውን ውሳኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አጸና። የአገሪቱ ከፍተኛው የፍትህ አካል የሆነው ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችሎት፤ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ባለስልጣን 20 ሚሊዮን ብር የሚደርሰውን የሁለቱን ድርጅቶች ገንዘብ እንዲታገድና እንዲወረስ የወሰነውና ቦርዱና ...
Read More »ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡ ልጃገረዶች መጠን 30 ከመቶ ብቻ ነው
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ውስጥ ወደሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚገቡ ሴት ተማሪዎች ቁጥር ከአፍሪካ አማካይ እንኩዋን ያነሰ መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ፤ ፕላን ኢንተርናሽናል የተሰኘው አለማቀፍ ድርጅት ገለጸ። ድርጅቱ በዚህ ወር ባወጣው የዓለም የልጃገረዶች ሁኔታ የተመለከተ ዘገባ፤ በአንደኛ ደረጃ የተመዘገቡ ሴቶች ቁጥር ከ30 በመቶ ወደ75 በመቶ ቢያድግም፤ ከአንደኛ ደረጃ ወደሁለተኛ ደረጃ የሚሸጋገሩ ልጃገረዶች ቁጥር ግን 20 ከመቶ ብቻ ነው ...
Read More »ኢትዮጵያ በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ አገሮች 33ኛ ወጣች
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ሀገራት የመልካም አስተዳደር ይዘትን የሚያጠናውና ደረጃ የሚያወጣው የ ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ባወጣው የ2012 ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ ከመቶ 47 ነጥብ በማግኘት 33ኛ ደረጃ መውጣቷን ይፋ አደረገ። በትውልድ ሱዳናዊ፤ በዜግነት እንግሊዘዊ በሆኑት ቢሊዮኔር ዶ/ር ሞሀመድ ኢብራሂም የተቋቋመው ይህ ተቋም፤ የአፍሪካ ሀገራትን በተለያዩ ዘርፎች በመመርመርና በማወዳደር በሰጠው ደረጃ፤ ሞሪሸስ በ83 ነጥብ የአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተመዝግባለች። ኬፕ ቬርድና ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም በአንዋርና በበኒ መስጊዶች ተቃውሞአቸውን አሰሙ
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ በኢህአዴግ መንግሥት ደረሰብን ላሉት የሕገ-መንግሥትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዛሬ ከጁምዓ የጸሎት ፕሮግራም በኋላ ፒያሳ በሚገኘው የበኒ መስኪድ እና መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስኪድ ተቃውሟቸውን ገለጹ፡፡ በከፍተኛ ቁጥር ፒያሳ በሚገኘው በኒ መስኪድ እና መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስኪድ የተሰባሰበው የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ከጸሎተ ሥግደት በኋላ ለ30 ደቂቃ ያህል እጅ ለእጅ በመያያዝ አንድነታቸውን ያሳዩ ...
Read More »በአማራ ክልል ነጋዴዎች በዘፈቀደ በሚጣለው ግብር እየተማረሩ ነው
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ነጋዴዎቹ በበቂ ጥናት ባልተደገፈ መልኩ በሚጣልባቸው ግብር በመማረር የንግድ ድርጅቶቻቸውን እየዘጉ፣ ወደ አዲስ አበባ ወይም ወደ ጎረቤት አገሮች በተለይም ወደ ደቡብ ሱዳን በመጓዝ ላይ ናቸው ። መንግስት የአምስት አመቱን የልማት ግቦች አሳካለሁ በማለት የጀመረው እቅድ በገንዘብ እጥረት ምክንያት ፈተና ውስጥ እየወደቀ መምጣቱን በመመልከቱ ፣በነጋዴው ላይ ግብር ለመቆለል መገደዱን ባለሙያዎች ...
Read More »በኢትዮጵያ ለውጭ አገር ባለሀብቶች የሚሰጡት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ዋጋ ተገቢ ነው ሲሉ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ተናገሩ
ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኦል አፍሪካ ዶት ኮም እንደዘገበው በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ወ/ሮ ገነት በኢትዮጵያ የጠረፍ አካባቢዎች በቂ የሆኑ የመሰረተ ልማቶች ያልተዘረጉ በመሆኑና ሰው ሀይልም በበቂ ሁኔታ አለመገኘቱ፣ እንዲሁም አንዳንድ አገሮች ባለሀብቶችን ለመሳብ መሬት በነጻ የሚሰጡ በመሆኑ በኢትዮጵያ የእርሻ መሬቶችን ለውጭ ባለሀብቶች በርካሽ ዋጋ መሸጡ ተገቢ ነው ሰሉ የመንግስታቸውን አቋም አጠናክረዋል። ወ/ሮ ገነት ይህን ይበሉ እንጅ ...
Read More »ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞች፡ “የኢትዮጵያ ፍርድ ሂደት ቀልድ ነበር” አሉ
ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ በእስር ላይ ቆይተው የተለቀቁት የስዊዲን ጋዜጠኞች የታሰሩበት እስር ቤት በእስረኛ ብዛት ከ200 በመቶ በላይ የተጨናነቀና በሽታ የበዛበት መሆኑን ጋዜጠኞቹ አስታወቁ:: በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች የታሰሩበት እስር ቤት ከ200 በመቶ በላይ መያዝ ከሚችለው በላይ የተጨናነቀና ፍጽም ቆሻሳ መሆኑ ተገለጸ:: በእስር ቤቶቹ አይጦችና ዝንቦች ለታሳሪዎች መከራ መሆናቸውንም ቢቢሲ ጋዜጠኞቹን ጠቅሶ ዘግቧል:: በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ...
Read More »ኢትዮጵያ ከመሀይምነት ባልተላቀቁ ሰዎች ብዛት ከዓለማችን ሶስተኛ ናት ተባለ
ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም (ዩ ኤን ዲ ፒ)፤ ከመሀይምነት የተላቀቁ ሰዎች ብዛትን በተመለከተ ይፋ ባደረገው መረጃ፤ ኢትዮጵያ ከዓለማችን በርካታ አገራት ከመጨረሻ ሶስተኛ መሆኗን ይፋ አደረገ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሮግራም ከሶስተኛ አለም አገራት ውስጥ አጥንቶ ይፋ ባደረገው በዚህ ጥናት፤ በኢትዮጵያ ከአጠቃላይ ህዝብ ውስጥ፤ 28 በመቶው ብቻ ፊደል የቆጠሩና መጻፍና ማንበብ የሚችሉ ናቸው ...
Read More »በመንግስት አና በ ኦብነግ መካከል የተጀመረው ድርድር ሳይሳካ ቀረ
ጥቅምት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለድርድሩ መደናቀፍ አንድኛቸው ሌለኛቸውን ተጠያቂ እያደረጉ ነው። በኢትዮጵያ መንግስትና በኦጋዴ ብሔራዊ ነፃነት ግንባር መካከል የተጀመረው ድርድር አለመሳካቱን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ። ናይሮቢ ሚገኘው የ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ድርድሩ የከሸፈው ኦብነግ የ ኢትዮጵያን ህገ-መንግስት ባለመቀበሉ ነው ሲል፤ኦብነግ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ፤ አላስፈላጊ ቅደመ-ሁኔታዎችን በማስቀመጥ በድርድሩ ላይ እንቅፋት የፈጠረው የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን ገልጿል። በጀነራል መሀመድ ኡስማን ...
Read More »