ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትግራይን የኢንደስትሪ ማእከል ለማድረግ አቶ መለስ ያወጡትን ስትራቴጂ ለመተግበር ርብርብ በማድረግ ላይ መሆኑን ወ/ሮ አዜብ መስፍን ገለፁ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤትና የ ኤፈርት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ አዜብ መስፍን የ ኤፈርት ኩባንያዎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውንም ገልፀዋል ። ከኤፈርት ኩባንያዎች አንዱ ሉሆነው ዋልታኢንፎርሜሽን ማዕከል ወ/ሮ አዜብ መስፍን በሰጡት ቃለ ምልልስ ያቶ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአባይ ግድብ አሁን ባለው ሁኔታ በ20 አመታት አይጠናቀቅም ሲሉ ሰራተኞች ገለጡ ሰራተኞቹ ተገደው ወደ ስራቸው እንዲመለሱም ተደርጓል
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ትናንት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ሰራተኞቹ ተቃውሞውን ያነሱት ከስራው መጓተት፣ ከክፍያ ፣ ከስራ ከባቢ ከመጠለያና ተዛማች ችግሮች ጋር በተያያዘ ነው። ሳሊኒ ከግብጽ መንግስት ጋር የተመሳጠረ በሚመስል ሁኔታ ስራው እንዳይሰራ እያጓተተው ነው፣ ሰራተኛው አለስራ ጊዜውን እያባካነ ነው፣ የሚከፈለን ክፍያ ከስራው ጋር የተመጣጠጠነ አይደለም፣ የምግብ፣ የመጠለያና ሌሎችም ችግሮች አሉብን በማለት የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት ...
Read More »በደጋን ወረዳ የተያዙ ሙስሊም እስረኞች በሰለጠኑ ውሾች ሳይቀር እንዲነከሱ እየተደረገ መሆኑን የአይን እማኞች ተናገሩ
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅርቡ በደጋንና በገርባን የተነሳውን የሙስሊሞች ተቃውሞ ተከትሎ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸውን፣ ግጭቱን አስነስተዋል የተባሉ 2 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች እንዲረሸኑ፣ ሌሎች ሁለቱ ደግሞ በግጭቱ ላይ በፌደራል ፖሊሶች ጥይት እንዲገደሉ መደረጉን ፣ ይህን ተከትሎም የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው በስፋት በመስፈር አካባቢውን የጦር ቀጣና እንዳስመሰሉትና እስካሁን ድረስ ከ200 በላይ ወጣቶችን፣ አዛውንቶችንና ሴቶችን ሳይቀር ይዘው ማሰራቸውን ...
Read More »የፌደራል ገቢዎች ባለስልጣን የፍትህ ጋዜጣን አሳታሚ ንግድ ፍቃድ አላድስም አለ
ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ገቢዎች ባለስልጣን መስሪያ ቤት የንግድ ፈቃድ ፈቃድ ለማደስ የሄዱትን የማስተዋል የህትመት ማስታወቂያ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ እና ስራ አስፈጻሚ አባላት የንግድ ፈቃድ አላድስም በማለት እንደመለሳቸው ምንጮቻችን አስታውቀዋል። ላለፉት 4 አመታት በሀገሪቱ ላይ ያለውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተግዳሮቶች ተቃውሞ ፍትህ ጋዜጣን በማሳተም ለንባብ ሲያበቃ የነበረው ድርጅት ፍቃዱን እንዳያድስ ከበላይ ...
Read More »ለግራዚያኒ የተሰራው መታሰቢያ እንዲፈርስ ተጠየቀ
ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢጣሊያ ሮም አፍሌ ከተማ ለፋሽስቱ አዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን መካነ መቃብርና መናፈሻ የተቃወመና እንዲፈርስ የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ። ከትላንት በስቲያ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በሶስት ቀን የአውሮፖላን ድብደባና በመርዝ ጋዝ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያን ላስጨፈጨፈው ፋሽስቱ አዶልፍ ግራዚያኒ በታሰቢያ መሰራቱን በጽኑ አውግዞል። አለም አቀፈ ትብብር ለፍትህ (ገሎባል አሊያንስ ፎር ...
Read More »አንድ የሲቪል ሰርቪስ ባለስልጣን ሃገር ከዱ
ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስን ሕመምና ሕልፈት ተከትሎ ስርአቱን እየከዱ የሚሸሹ ባለስልጣናት በተለይም የሕውሐት አባላት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ከኢትዮጲያ ለኢሳት የሚደርሱ መረጃዎች እያመላከቱ መጥተዋል። በዚህ መሰረት የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ሕውሐት አባል አቶ አታክልቲ ሐጎስ ከነቤተሰባቸው ከሃገር መሰደዳቸው ታውቋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት አቶ አታክልቲ ሐጎስ ከነቤተሰባቸው ካናዳ መግባታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ...
Read More »የመከላከያ ሰራዊት አዲሱን መንግስት እንዲቀበሉ ለማሳመን የሚደረገው ግምገማ ቀጥሎአል
ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የመከላከያ ሰራዊት ምንጮች እንደገለጡት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ካረፉ እና አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ከተሾሙ በሁዋላ በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚካሄደው ግምገማ ተጠናክሮ ቀጥሎአል። ከፍተኛ የጦር አዛዦች ግምገማ መጠናቀቁን የጠቆሙት ምንጮች፣ ግምገማው ወደ መካከለኛና ተራ ወታደሮች እየወረደ ነው። በምስራቅ እዝ የሚገኙ እስከ ኮሎኔልነት ማእረግ ያላቸው መኮንኖች ሀረር ውስጥ ...
Read More »በቃሊቲ ግንቦት 7 እየተባሉ በሚጠሩ እስረኞች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑ ታወቀ
ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የቃሊቲ ምንጮቻችን እንደገለጡት በተለምዶ የአማራ ተወላጅ የሆኑትንና ከፖለቲካ ጋር በተያያዘ የታሰሩትን በሙሉ የማረሚያ ቤቱ ሀላፊዎች ግንቦት7 እያሉ እንደሚጠሩዋቸው ገልጸው፣ በእስረኞች ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶች እየተፈጸመ መሆኑንም ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በእነ ጀኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከሰው በእስር ላይ በሚገኙት ወታደራዊ መኮንኖች ላይ እጅግ ኢሰብዓዊ የሆነ አሰቃቂ ድብደባ ( ቶርች) የተፈጸመባቸው ...
Read More »በኢትዮጵያ የአደገኛ አደንዛዥ ዕፅ ምርት እየጨመረ ነው ተባለ
ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የህወሀት ንብረት የሆነው ፋና ራዲዮ ” ካናቢስ የተባለው የአደንዛዥ ዕፅ ምርት በአዲስ አበባ ፥ ለመልሶ ማልማት የታጠሩ አካባቢዎችን ጨምሮ በደቡብ ክልል ፣ በኦሮሚያ ፣ አርሲና ምስራቅ ሃረርጌ ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በአባይ በረሃ በስፋት እንደሚታይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መናገሩን” በመግለጽ ዘግቧል። ባለፈው ዓመት ብቻ መጠኑ ከ400 ኪሎ ግራም በላይ እንዲሁም ያልተመዘነ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለሁለተኛ ጊዜ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ
ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-”ይህች አገር ከማናቸውም የዓለማችን አገሮች በላይ ንብረት አላት። እኛን ሀብታም ያደረገን ግን ያ አይደለም። በታሪክ በጣም ግዙፍ የሆነ ወታደራዊ ሀይል አለን።ጠንካሮች ያደረገን ግን ያ አይደለም።ዩኒቨርሲቲያችን፣ባህላችን ሁሉ በዓለማችን ምርጦች የሚባሉ ናቸው።ዓለምን ወደኛ ዳርቻ ያመጡት ግን እነሱ አይደሉም። አሜሪካን የተለየ ያደረጋት ፤ የምድራችንን የተለያዩ ህዝቦች፤ በህብረት ያስተሳሰረችበት ሰንሰለት ነው” ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡት 44ኛው የአሜሪካ ...
Read More »