ታህሳስ ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታህሳስ 29 ቀን 2005 ዓም በእራት ሰአት ላይ በድሬዳዊ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተን ረብሻ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥራቸው የበዛ ተማሪዎችን ደብድበዋል፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎችን ደግሞ ይዘው አስረዋል። እስከ ምሽት የዘለቀውን ይህንኑ የፖሊሶች ድብደባ መቋቋም ያቃታቸው ተማሪዎች በምሽት ግቢያቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ያመለከተው ዘጋቢያችን፤ የሚያድሩበት ቦታ በማጣታቸው በቤተክርስቲያኖች እና ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ወደ መስጊድ ሄደው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
‹‹ከእስረኞች ሁሉ ህገ-መንግስታዊ መብቴ ተጥሶ ዘመድ አዝማድ እና ጓደኛ እንዳይጠይቀኝ የተደረኩት እኔ ብቻ ነኝ››ሲል የአንድነት ፓርቲ አመራሩ አንዷለም አራጌ ገለጸ
ታህሳስ ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንዷለም ይህን ያለው፤የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ እንዲጠይቁት የተፈቀደላቸው የ አንድነት አመራሮች በቃሊቲ ተገኝተው በጎበኙት ጊዜ ነው። ወጣቱ ፖለቲከኛ በዚሁ ጊዜ ቃሊቲ ለተገኙት የአንድነት አመራሮች ፦”በፍቅርና በመተሳሰብ የምንኖርባት ኢትዮጵያ ትናፍቀኛለች”በማለት ህያው ራዕዩንና ውስጣዊ ምኞቱን ገልጾላቸዋል። ከአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ አቶ ተመስጌን ዘውዴ፣ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን፣ ...
Read More »የጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ ይግባኝ ውድቅ ተደረገ
ታህሳስ ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ርእዮት ዛሬ ሰበር ሰሚ ችሎት ባትቀርብም ጠበቃዋ፣ አባቷ እና ሌሎች የስራ ባልደረቦቿና ጓደኞቿ በችሎቱ ተገኝተው ውሳኔውን ሰምተዋል። ሰበር ሰሚ ችሎቱ በርእዮት የቀረበው አቤቱታ የህግ ክፍተት የለበትም ሲል ውሳኔ አሳልፎአል። ጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት ጥር 17 ቀን 2004 ዓም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት የ14 አመት ጽኑ እስራትና የ33 ሺ ብር ቅጣት እንደተወሰነባት ይታወሳል። ...
Read More »የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ዘንድ እየተከበረ ነው
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየአመቱ ታህሳስ 29 የሚከበረው የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል በመላው የኢትዮጵያ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ሲሆን በአገሪቱ የሚታየው የኑሮ ውድነት የበአሉን ድምቀት እንደቀነሰው ምእመናን ተናግረዋል። ዘጋቢያችን ያነጋገራት አንድ የኦሮቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተክርስቲያኑዋ ከሁለት በመከፈሉዋና የቤተክርስቲያን አባቶች ችግሩን ለመፍታት ባለመቻላቸው ማዘኑዋን ገልጻለች። በበአሉ ዋዜማ በተደረገው የጸሎት ስነስርአት ላይ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያኑዋን እንዲጎበኝ ስትጸልይ ማደሯንም ተናግራለች። ...
Read More »ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታስረዋል ተባለ
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተከስቶ የነበረውን የብሄር ግጭት ተከትሎ ከ100 በላይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መታሰራቸውን የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ታስረዋል ያላቸውን የ99 ተማሪዎች ስም ዝርዝር ይፋ ያደረገው የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አብዛኞቹ ከቀላል እስከ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን ጠቁሟል። ከታሰሩት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የኦሮሞ ተወላጆች ቢሆንም፣ የአማራና የትግራይ ተማሪዎችም ይገኙበታል። ...
Read More »ባለሀብቶች ለኢህአዴግ ጽ/ቤት ግንባታ ቃል የገቡትን ገንዘብ ሊሰጡ አልቻሉም ተባለ
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህም ምክንያት የግንባሩ ጽህፈት ቤት ግንባታ መስተጓጎሉን ሪፖርተር ዘግቧል። ጋዜጣው እንዳለው ከአራት ዓመት በፊት ኢሕአዴግ ሰባት ፎቅ ከፍታ ያለው ሕንፃና ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሰንዳፋ ከተማ የካድሬዎች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ለመገንባት ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡ አራት ኪሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አካባቢ ይገነባል የተባለው የኢሕአዴግ ፖለቲካ ...
Read More »ግንቦት7 በሀረር ሙስሊሞች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ
ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ህወሀት መራሹ መንግስት በሀረር በታዳጊው ላይ የወሰደውን ኢሰብአዊ ድርጊት በጽኑ አውግዟል። ዜጎች መብታቸውን በጠየቁ በጥይቅ የቆላሉ ያለው መግለጫው፣ ከእንዲህ አይነት አስከፊ ስርአት ለመላቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ኢትዮጵያውያን የትግል ጽናት በመማር ለእውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል። ህወሀት መራሹ መንግስት ቅንጣት ያህል ለዜጎች መብት ...
Read More »የቻይና ጋዜጠኞች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ኢህአዴግ በሙስሊሙ ተቃውሞ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባቱ ታወቀ
ታህሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከኢህአዴግ ምንጮች ለመረዳት እንደቻለው ግንባሩ በየጊዜው እያየለ የመጣውን የሙስሊሞችን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የመ-= ፍትሄ ሀሳብ በማጣቱ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደወደቀ ታውቋል። የመጅሊስ አመራሮች ከተመረጡ እና መሪዎቹ ወደ እስር ቤት ከተጓዙ በሁዋላ እንቅሰቃሴው ይዳከማል የሚል እምነት ይዞ የነበረው ኢህአዴግ፣ እንቅስቃሴው በተቃራኒው እየጨመረ እና የአብዛኛውን ሙስሊም ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋት ላይ ጥሎታል። በግንባሩ ውስጥ ...
Read More »የባለራእይ ወጣቶች ማህበር በደህንነት ሰዎች እየተዋከብን ነው ይላሉ
ታህሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማህበሩ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆነው ወጣት አለማየሁ አበበ እና የህዝብ ግንኙነት ሀላፊው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ እንደገለጹት ባለፈው ሳምንት ለኢሳት ቃለምልልስ ከሰጡ በሁዋላ፣ ከአሸባሪዎች ጋር ተገናኝታችሁዋል በሚል በደህንነት ሀይሎች እየተዋከቡ ነው። ከእነርሱ አልፎ ቤተሰቦቻቸውንም ማስፈራራትና ማሸበር መጀመራቸውን ገልጸዋል። ወጣት ብርሀኑ እንደሚለው በህጋዊነት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰውን ማህበር የተለያዩ ስሞች እየሰጡ መወንጀልና አመራሮችንም ማዋከብ የሰላማዊ ትግል አስፈላጊነትን ...
Read More »