የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አጋር እንደሆኑ የሚነገርላቸውና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ እየተባለ በሚጠራው ተሳታፊ የሆኑ ወደ ዘጠኝ የሚጠጉ ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ፤ በምርጫ ቦርድ በኩል የፋይናንስ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ካለማግኘቱ ጋር ተያይዞ በአጃቢነት ከገቡበት ምርጫ ተገፍተው ሊወጡ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡ ቀደም ሲል በአቶ ልደቱ አያሌው ይመራ የነበረው ኢዴፓ፣ በአቶ አየለ ጫሚሶ ሊቀመንበርነት የሚመራው ቅንጅት፣መኢብን ፣ራዕይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአዲስ አበባ የሙስሊሞችን ቤት መፈተሽ ቀጥሎአል
የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዘጋቢያችን እንደገለጠው በትናንትናው እለት በፈረንሳይ አካባቢ የሚኖሩ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት በድንገት ቤታቸው እየተበረበረ ቁራን ፣ የተለያዩ ሲዲዎች እና ሀይማኖታዊ መጽሀፎች ወስደውባቸዋል ። የኢህአዴግ ካድሬዎች እና የደህንነት ሰዎች ናቸው የሙስሊሞችን ቤት እንዲፈተሽ የሚጠቁሙት ያሉን አንድ የአካካቢው ነዋሪ ፣ ፈታሽ ፖሊሶች ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትእዛዝ ወረቀት አለመያዛቸውንም ተናግረዋል። የፖሊሶቹ ዋና አላማ ሙስሊሞች በስነልቦና ...
Read More »አዲሱ የመብራት፣ የውሀና ስልክ ክፍያ ስርአት ችግር እየፈጠረ ነው
የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በ ዶ/ር ደብረጺዮን አመራር በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የመብራት፣ የውሀ እና የስልክ ክፍያዎችን በአንድነት የመክፍል ሂደት በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ መጉላላት እየፈጠረ ነው። ህብረተሰቡ ክፍያዎችን ለመክፈል ረጃጅም ሰልፎችን መሰለፍና በርካታ ሰአታትን መጠበቅ ግዴታው ሆኗል ስራውን እንዲተገብሩ የተመረጡት በሙሉ ኢህአዴግ ካድሬዎች ሲሆኑ ፣ የኢህአዴግ አባላት ያልሆኑ የየድርጅቶቹ የቀድሞ ሰራተኞች ተንሳፋፊዎች ሆነዋል። መንግስት የህብረተሰቡን እንግልት ይቀንሳል ...
Read More »በሳውዲ አረብያ የታሰሩት የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ሊመለሱ ይችላሉ ተባለ
የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረብያ በእስር ላይ የሚገኙት 53 የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን በስተቀር ሁሉም ወደ አገራቸው ሊመለሱ እንደሚችሉ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ መቼ እንደሚመለሱ እስካሁን ባይታወቅም በቅርቡ ከሳውዲ ሊባረሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል። ከእሰረኞቹ መካከል 46ቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ ፖሊሶች ሴቶችን እየደጋገሙ በማስወጣት ለስነልቦና ...
Read More »የውጭ ምንዛሬ እጥረት በእህልና በእቃዎች ዋጋ ላይ ጭማሪ እያስከተለ ነው
የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የተከሰተው አሳሳቢ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ነዳጅን ጨምሮ በተለያዩ ከውጭ ተገዝተው በሚመጡ እቃዎች እና በእህል ዋጋ ላይ ጭማሪ እያሳየ መምጣቱ ታወቀ ዘጋቢያችን እንደገለጠው ካለፉት 7 ወራት ጀምሮ የተከሰተው ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ከውጭ በሚገቡ በተለይም ከትራንስፖርት ጋራ ተያያዢነት ባላቸው እቃዎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ እያሳየ ነው። የፍጆታ እቃዎች ባልሆኑት ላይ የታየው ጭማሪ በእህል ...
Read More »በኦሮሚያ ለአባ ገዳ የተሰበሰበው ገንዘብ በባለስልጣናት ተመዘበረ
የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጉጂ ኦሮሞ ባህል አንድ አባገዳ ስልጣን በተረከበ በስድስተኛው አመት ጉማታ ወይም ስጦታ ከህዝቡ ይሰበስባል። ስልጣኑን የሚያስረክበው በስምንተኛው አመት ሲሆን፣ ለሁለት አመታት የሚሰራበትን ገንዘብ፣ እህል ወይም የቤት እንስሳ ከህዝቡ በስጦታ መልክ ይቀበላል። በዚህ አመት አባገዳው ጉማታውን ለመሰብሰብ ዝግጅት በሚጀምርበት ጊዜ የቦረና ዞን የመንግስት ባለስልጣናት ከአሁን በሁዋላ ጉማታው መሰብሰብ ያለበት በመንግስት ነው በሚል ምክንያት፣ ...
Read More »አቡነ ሳሙኤል ለፓትሪያርክነት ለመመረጥ ቅስቀሳ መጀመራቸው ተዘገበ
የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን አወዛጋቢውን ጳጳስ አቡነ ጳውሎስን የሚተካ ስድስተኛው ፓትሪያሪክ ለማስመረጥ በዝግጅት ላይ ባለችበት በዚህ ወቅት ከዚህ የፓትሪያሪክ ምርጫ ጋር በተያያዘ የቤተ ክርስትያኒቷ የተራድኦ ኮሚሽን ሊቀጳጳስና ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በነበሩበት ወቅት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው የነበሩት አቡነ ሳሙኤል በቀጣዩ ምርጫ ...
Read More »ሱዳን በአሜሪካ ላይ ያላትን ተቃውሞ ገለጸች
የካቲት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካ ደቡብ ሱዳንን ለመደገፍ በሚል ለጋሾችን በአንድ ጉባኤ ላይ ለማናገር የምታደርገውን ጥረት ሰሜን ሱዳን ታቀወመች። የሰሜን ሱዳን የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ አሊ ኦቤድ ማርዊ አሜሪካ በኢኮኖሚ ቀውስ የተነሳ ለመፈራረስ ጫፍ ላይ የደረሰችውን ደቡብ ሱዳንን ለመደገፍ የምታደርገው ጥረት ፣ ደቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ጋር የገባችውን ውል እንዳታከብር ያደፋፍራታል ሲሉ ተናግረዋል። የአሜሪካ የደቡብ ሱዳን ...
Read More »ጣሊያን ኢትዮጵያውያንን በግፍ የጨፈጨፈችበት 76ኛ አመት በመላው አለም ታስቦ ዋለ
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፋሽስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረች ማግስት፣ አገራቸውን ከወረራ ለመታደግ ሞገስ አስገዶምና አብረሀ ደቦጭ የተባሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን፣ የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙስሎኒ የኢትዮጵያ ልኡክ የነበረውን ሮዶልፎ ግራዚያኒን ለመግደል ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ፣ ወራሪው ሀይል ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን በአንድ ቀን በግፍ መጨፍጨፉ ይታወሳል። ኢትዮጵያውያን በእየአመቱ የካቲት 12 የሚያከብሩት ይህ የሰማእታት ቀን በመላው አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ...
Read More »ጄነራል ሳሞራ የኑስ በ80 ሚሊዮን ብር ህንጻ አሰርተው እያከራዩ ነው
የካቲት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢታማጆር ሹሙ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ በቄራ መብራት ሀይል አካባቢ በ80 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ህንጻ ማሰራታቸውን በፎቶ ግራፍ አስደግፈው ውስጥ አዋቂዎች ለኢሳት ላኩት መረጃ ያመለክታል። የጄኔራል ሳሞራ ህንጻ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቶችም መከራየታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ጄኔራል ሳሞራ መከላከያ ሚኒስቴር በወር 10 ሺ ዶላር የሚከፍልበት በልዩ የደህንነት መሳሪያዎች በየሚጠበቅ መኖሪያ ቤት ውስጥ ...
Read More »