ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአፋር ክልል ካቢኔ ውስጥ የተነሳው ውዝግብ አይሎ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ፣ የብአዴፓን የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊን ከሀላፊነት አንስተዋል። ሌሎች የካቢኔ አባላት በበኩላቸው ” ፕሬዚዳንቱ ” ላለፉት 18 አመታት በስልጣን ላይ ቆይተው፣ ለክልሉ ህዝብ ያመጡት ነገር ባለመኖሩ ስልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው” እያሉ ነው። አብዛኞቹ የካቢኔ አባላት ፕሬዚዳንቱ የሀወሀት ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን የአፋርን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ ለግራዚያኒ የሚሰራውን ሀውልት አለም እንዲያወግዘው ጠየቁ
ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያውያው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የአለማቀፉ ማህበረሰብና የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እና በሊቢያ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ ላደረሰው ግራዚያኒ ሀውልት ለማቆም የሚደረገውን ጥረት እንዲያወግዝ ጠይቀዋል። ሚ/ሩ ይህን የተናገሩት በሩዋንዳ የደረሰውን ዘር ማጥፋት 19ኛ አመት ለማስታወስ በተጠራ ዝግጅት ላይ ነው። የኢትዮጵያን እና የሊቢያን ዜጎች በግፍ የጨፈጨፈው ግራዚያኒ ሀውልት አይገባውም ብለዋል ሚስትሩ። የሚኒሰትሩ ንግግር ...
Read More »አማርኛ ተናጋሪዎች ከደቡብ ክልል በድጋሜ እንዲለቁ ተደረገ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ እንደገለጠው፣ ቀደም ሲል በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ከ20 ሺ ያላነሱ አርሶደሮች የገቡበት ሳይታወቅ፣ አሁን ደግሞ በዚሁ ዞን በሚኒት ወልድያ ወረዳ በተለይም ዘንባብና አርፋጅ ቀበሌ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከ350 በላይ የአማርኛ ተናጋሪዎች ተፈናቅለው በወረዳው አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ። ተፈናቃዮቹ ከመኖሪያ አካባቢያቸው 61 ከብቶችና ግምቱ ያልታወቀ እህል ...
Read More »ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አርሶአደሮች የደረሰባቸውን ግፍ ለሚዲያዎች እያቀረቡ ነው
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲስ አድማስ ጋዜጣ በቅዳሜ እትሙ ወደ ፍኖተሰላም በማቅናት አንድ ዘገባ አቅርቧል። በዘገባውም ተፈናቃዮች የደረሰባቸውን ግፍ በዝርዝሮ አትቷል። “ከእነ ቤተሠቤ እዚህ ለመድረስ ያየሁትን ፈተና ፈጣሪ ያውቀዋል፡፡ ቤተሰቤ ከቁጥር ሳይጐድል ለአገሬ መሬት በቅቻለሁና ከእንግዲህ የፈለገው ይሁን” አሉኝ፤ ከቤኒሻንጉል ክልል ያሶ ወረዳ ተፈናቅለው በፍኖተ ሰላም ድንጋያማ መጠለያ ውስጥ ያገኘኋቸው አዛውንት፣ ትላለች የአዲስ አድማሱዋ ናፍቆት ዮሴፍ ። ...
Read More »ማርጋሪት ታቸር አረፉ
መጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚ/ር በመሆን እኤአ ከ1979 እስከ 1990 የቆዩት ታቸር በ87 ዓመታቸው በድንገት አርፈዋል። ታቸር በእንግሊዝ ታሪክ የመጀመሪያዋ የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሴት ጠ/ሚኒስትር ነበሩ። በእንግሊዝኛ ( ዘ አይረን ሌዲ) እየተባሉ የሚጠሩት ታቸር በዘመናቸው በተከተሉት የኢኮኖሚ ፍልስፍና አወዛጋቢ ሰው እንደነበሩ ይታወቃል። በመላው አለም የሚገኙ መሪዎች ታቸር በጊዜያቸው ላሳዩት ጽናት አድናቆታቸውን እየገለጡላቸው ነው።
Read More »ተፈናቃይ አርሶአደሮች የደረሰባቸውን ጉዳት በመዘርዝር ለመንግስት ባለስልጣናት አቀረቡ
መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ፍኖተሰላም ከተማ ላይ ሰፍረው የሚገኙትን ተፈናቃዮች ያነጋገሩ ሲሆን፣ ተፈናቃዮችም ልዩ ሀይል እየተባለc በሚጠራው ታታቂ ቡድን የደረሰባቸውን ግፍ ያለምንም ፍርሀት ማቅረባቸውን በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አንድ ተፈናቃይ ገልጠዋል። በስብሰባው ላይ ከአማራ ክልል መገናኛ ብዙሀን የተውጣ ጡ ጋዜጠኞች ቢገኙም፣ ስብሰባውን እንዳይቀርጹ መደረጉን አንድ በስፍራው አለው ...
Read More »ለ3ኛ ጊዜ ህትመቱ የተቋረጠበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ” ከእንግዲህ ከጫካ መለስ ባሉ መታገያ መንገዶች በመጠቀም መብታችን እናስከብራለን” አለ
መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እውቁ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይህን የተናገረው ልእልና ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዳድታተም ከታገደች በሁዋላ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ” የንግድ ሚኒስቴር በልእልና ጋዜጣ የቀድሞ ባለቤትና በአዲሱ ባለቤት መካከል ህገወጥ የሆነ የስም ዝውውር ተደርጓል በማለት የንግድ ፈቃዱ ” እንዲሰረዝ መደረጉን ተነግሯል። ፍትህ ጋዜጣ በህገወጥ መንገድ እንዳይታተም ከተደረገ በሁዋላ፣ ጋዜጠኛው አዲስ ታይምስ መጽሄትን ከሌላ አሳታሚ ላይ ...
Read More »በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ የደረሰውን መፈናቀል በመቃወም ፊርማ እያሳበሰቡ ነው
መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በጀመሩት የፊርማ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ በርካታ የጀርመን ዜጎች ፊርማቸውን አኑረዋል፡ ዝግጅቱን እያስተባበረ የሚገኘው የኢትዮጵያ የሲቪክና ፖለቲካ ድርጅቶች ጥምረት የተባለው ገለልተኛ ድርጅት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በላይ ወንድአፍራሽ ለኢሳት እንደገለጡት፣ ዝግጅቱ ለሚቀጥለው አንድ ወር ይቀጥላል። የተሰባሰበውን ፊርማም ለጀርመን ፓርላማ፣ ለጀርመን የተለያዩ መሰሪያ ቤቶች፣ ለአውሮፓ ህብረትና፣ ለተለያዩ የአውሮፓ አገራት፣ ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ለሂውማን ...
Read More »በፌስ ቡክ “ስም አጉድፈሀል” የተባለው ተማሪ በ5 ሺ ብር ዋስ ተፈታ
መጋቢት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የመጀመሪያ አመት ተማሪ የሆነው ማንያዘዋል እሸቱ ለኢሳት እንደገለጠው ከአንድ ሳምንት እስር በሁዋላ፣ የአርባ ምንጭ ፍርድ ቤት “ስትፈለግ ትመጣለህ” በማለት በ5 ሺ ብር ዋስ ለቆታል። ወደ ፈተና ለመግባት ሲዘጋጅ ሶስት ፖሊሶች መጥተው የፍርድ ቤት ማዘዣ በማሳየት እንደወሰዱትና በአርባ ምንጭ እስር ቤት አንድ ሳምንት ማሳለፉን ተማሪ ማንያዘዋል ገልጿል። ተማሪ ማንያዘዋል፣ ...
Read More »ሙስና እና ፖለቲካ ብአዴንን እየፈተኑት ነው
መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-“ማንኛውም ሰው” ይላሉ አንድ የብአዴን ከፍተኛ አመራር ” ስለ እነ አቶ በረከት ክፉ ቢያወራ በደቂቃዎች ውስጥ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያገኘዋል፣ ባበህርዳር።” በ9ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ በተለመደው ቋንቋ ሙስና ወይም ጉቦኝነት የድርጅቱ ዋነኛው የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ነበር። የብአዴን ነባር ታጋይ አቶ ህላዊ ዮሴፍ፣ እውን ከፍተኛውን አመራር የምንጠይቅበት ስርአት አለን?” ሲሉ ያቀረቡት ...
Read More »