.የኢሳት አማርኛ ዜና

በወልድያ ከተማ በርካታ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመላው አገሪቱ ከሚካሄደው የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልድያ ከተማ 10 ሙስሊም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአለፈው አርብ ጀምሮ መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በዛሬው እለትም እንዲሁ አንድ የሁለተኛ ደረጃ እንግሊዝኛ መምህር የሆኑት አቶ አብደላ እና የመደርሳ ትምህርት ቤት የእቃ ግምጃ ቤት ሀላፊ የሆኑ ግለሰቦች ተይዘው ታስረዋል። መንግስት የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ለማፈን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ አባላት ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ጋር ግንኙነት አላቸው ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች ይዘው አሰሩ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ከአዲስ አበባ የተንቀሳቀሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከባህርዳር በ35 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ መርአዊ ከተማ በመሄድ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን አፍነው ወስደዋል። ፖሊሶቹ ትናንት ምሽት ወደ ከተማዋ በመግባት እና የአካባቢውን ሰዎች በማስፈራራት ልጆቹን አፍነው የወሰዱዋቸው ሲሆን፣ አንድ ወጣት ክፉኛ መደብደቡን ለማረጋጥ ተችሎአል። የታሰሩት ወጣቶች ወደ አዲስ አበባ መወሰዳቸውም ...

Read More »

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን የመከላከያ ምስክሮች ያዳምጣል ተብሎ ቢጠበቅም፣ አቃቢ ህጎች የጊዜ ቀጠሮ በጠየቁት መሰረት ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል። የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቆች ታዋቂውን የሰብአዊ መብቶች ተማጓች ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ጨምሮ ሁለት ባለሙያዎችን ለመከላከያ ምስክርነት ከማቅረብ በተጨማሪ ሌሎች የቪዲዮና የኦዲዮ ማስረጃዎችንም አዘጋጅተው ነበር። ይሁን ...

Read More »

ከቫት ጋር በተያያዘ በኮምቦልቻና በደሴ ከ15 በላይ ነጋዴዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደሴ ዘጋቢ እንደገለጸው በከተማዋ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ 11 ነጋዴዎች ከቫት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሲሆን፣ በኮምቦልቻም ሶስት ነጋዴዎች ከትናንት በስቲያ ተይዘው ታስረዋል። ነጋዴዎቹ ቫት አልከፈላችሁም ተብለው መያዛቸውን የወረዳው ባለስልጣን መግለጻቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን፣ ነጋዴዎቹ በአሁኑ ጊዜ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባለስልጣናቱ ከመናገር ተቆጥበዋል።

Read More »

በኢትዮጵያ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ ህዝቡን ማሳተፍ ግድ ይላል ሲሉ አንድ ታዋቂ ኢኮሚስት ተናገሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙረይ ስቴት ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሰኢድ ሀሰን ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የኑሮ ውድነት ለመግታትም ሆነ የአገሪቱን የኢኮኖሚ ችግር ለመቅረፍ መንግስት ህዝቡን ያሳተፈ ስርአት መመስረት አለበት ብለዋል።   መንግስት ኢኮኖሚውን በበላይነት መቆጣጠሩና ከመንግስት ጋር ተለጥፈው የሚገኙት የመንግስት እና የገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች ኢኮኖሚውን እስከ ተቆጣጠሩት ድረስ በኢትዮጵያ የሚታየውን የኢኮኖሚ ችግር መፍታት ...

Read More »

የወንዶ ገነት ኮሌጅ ዲን እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዋሳ ዩኒቨርስቲ ስር የሚገኘው የወንዶገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ጸጋየ በቀለ እና የኮሌጁ የፖሊስ ክፍል አዛዥ  ሻምበል አለማየሁ ወረታ የታሰሩት የመንግስት ባለስልጣናት የኮሌጁን መሬት በመቁረጥ ለአካባቢው ተወላጅ ባለሀብት ለመስጠት የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወማቸው ነው።   አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ዩኒቨርስቲው ባለስልጣን ለኢሳት እንደገለጹት ሁለቱም ግለሰቦች የታሰሩት የአካባቢው ባለስልጣናትየኮሌጁን መሬት በመውሰድ ...

Read More »

የዐረና ለትግራይን ልሳን ያደሉ ሰዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል ማይፀብሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ አረና ለትግራይ ፓርቲን ልሳን ያደሉ ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ። ለ ኢሳት የደረሰው መረጃ እንደ ያመለክተው  ተሾመ ገብረመድህን እና ሰለሞን አባይ የተባሉ ሰዎች   ሚያዝያ13, 2005 ዓመተ ምህረት  አረና    ፓርቲ በምርጫው ለምን እንዳልተሳተፈ የሚያብራራ ጽሁፍ  በማይፀብሪ አካባቢ ሲያድሉ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። የፓርቲውን ልሳን ለህዝብ በማደላቸው ሳቢያ ወንጀል እንደፈፀሙ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ከእስር ተፈተው አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ለማጣራት ወደ መተከል ዞን አቅንተው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ  ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳና የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በቃሉ አዳነ በቡለን ወረዳ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢሳት በሰበር ዜናው ካቀረበ በሁዋላ ፣ ሶስቱም አመራሮች ማምሻውን ተለቀዋል። አመራሮቹ የታሰሩት ከፌደራል ...

Read More »

በኖርዌይ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠራ ስብሰባ ተበተነ

  ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኦስሎ ወደ 700 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ስታቫንጋር ከተማ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠራው ስብሰባ በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ ኢትዮጵያኑ መንግስት የተከራየውን አዳራሽ በመረከብ የራሳቸውን ስብሰባ አካሂደዋል። ኢትዮጵያውኑ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ የተፈጸሙ ወንጀሎች ዘርዝረው ለባለስልጣናት አቅርበዋል። በጉዳዩ ዙሪያ በስፍራው የሚገኘውን ወጣት ጌዲዮን ደሳለኝን አነጋግረነዋል።

Read More »

መንግስት ትችቶችን ወደ ሁዋላ በማለት ተጨማሪ መሬቶችን ለውጭ ባለሀብቶች ለመስጠት ማቀዱ ታወቀ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያዊያን ገበሬዎችን በማፈናቀል ለሃገር ውስጥና ለውጪ ባለሃብቶች ሰፋፊ መሬቶችን በማቅረቡ ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበበት ያለው የኢትዮጽያ መንግስት ይህንኑ ተግባሩን በማጠናከር ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች የያዘ ዞን ከማቋቋም በተጨማሪም የግብርና ኢንቨስትመንትን ብቻውን የሚመራ ራሱን የቻለ ተቋም ለመመስረት ማቀዱን ከግብርና ሚኒስቴር የተገኘ ሪፖርት አመለከተ፡፡ የግብርና ኢንቨስትመንትን በፍጥነት እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማስፋፋትና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳውን ለማጎልበት እንዲቻል የግብርና ...

Read More »