የዐረና ለትግራይን ልሳን ያደሉ ሰዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በትግራይ ክልል ማይፀብሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ አረና ለትግራይ ፓርቲን ልሳን ያደሉ ሰዎች መታሰራቸው ተገለጸ።

ለ ኢሳት የደረሰው መረጃ እንደ ያመለክተው  ተሾመ ገብረመድህን እና ሰለሞን አባይ የተባሉ ሰዎች   ሚያዝያ13, 2005 ዓመተ ምህረት  አረና    ፓርቲ በምርጫው ለምን እንዳልተሳተፈ የሚያብራራ ጽሁፍ  በማይፀብሪ አካባቢ ሲያድሉ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል።

የፓርቲውን ልሳን ለህዝብ በማደላቸው ሳቢያ ወንጀል እንደፈፀሙ ተይዘው የታሰሩት ሁለቱ ግለሰቦች  በጣቢያ ብዙ እንግልት ደርሶባቸዋል።

ከብዙ እንግልት እና ከ ሰ ዓታት እስር በሁዋላ  በስተመጨረሻ መለቀቃቸው ታውቋል።