በኖርዌይ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠራ ስብሰባ ተበተነ

Norway

 

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ  ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከኦስሎ ወደ 700 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ስታቫንጋር ከተማ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ለማሰባሰብ የተጠራው ስብሰባ በአገሪቱ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  ከፍተኛ ተቃውሞ እንዲቋረጥ ከመደረጉም በላይ ኢትዮጵያኑ መንግስት የተከራየውን አዳራሽ በመረከብ የራሳቸውን ስብሰባ አካሂደዋል።

ኢትዮጵያውኑ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በአገሪቱ የተፈጸሙ ወንጀሎች ዘርዝረው ለባለስልጣናት አቅርበዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ በስፍራው የሚገኘውን ወጣት ጌዲዮን ደሳለኝን አነጋግረነዋል።