ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሥራ ዓለምም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች የሠሩትና የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ሀይሉ ወልደጊዮርጊስ ይህን የገለጹት እሁድ ለህትመት ከበቃው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በ ዓባይ ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። “ የ ዓባይ ውሀ በህግ ላይ የሚያቀርበው ፈተና” በሚል ርዕስ በፈረንሳይኛ መጽሐፍ ያሳተሙት አምባሳደር ሀይሉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የምርጫ 97 የሰኔ 1 ሰማዕታት ታስበው ዋሉ
ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምርጫ 97 ወቅት “የተጭበረበረው የወላጆቻችች ድምጽ ይመለስ” በማለት ወደ አደባባይ ወጥተው በግፍ የተጨፈጨፉት የምርጫ 97 ሰምአታት 8ኛ አመት በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ውሎአል። በሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰኔ አንድ ቀን 1997 ዓም በአጋዚ ወታደሮች መጨፍጨፋቸው ይታወሳል። በተፈጥሮ ሞት ከተለዩት ከአቶ መለስ ዜናዊ በስተቀር ጭፍጨፋውን በመምራት የተባበሩት ሌሎች ባለስልጣኖች ዛሬም ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ በከፍተኛ የአስተዳደር ችግር ውስጥ መግባቱዋን የሀይማኖት አባቶች ገለጹ
ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ካህናት የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመሆናቸው ቤተክርስቲያኑዋን እየጎዱዋት ነው ሲሉ የሀይማኖት አባቶች ገልጸዋል ኢሳት ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀይማኖት አባቶች እንደገለጹት በስልጣን ላይ ያሉ አንዳንድ ካህናት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ትተው የገዢው ፓርቲ ካድሬ በመሆናቸው ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ለሚታየው የአስተዳደር መበላሸት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የሀይማኖት አባት “በከተማው፣ በገጠሩ በርካታ ...
Read More »አዋሳ እና ባህርዳር ከ 2006 ዓ.ም ጅምሮ በፌደራል መንግስት ሥር ሊሆኑ ነው
ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ርእሰ መዲና ሓዋሳ እና የአማራ ክልል ርእሰ መዲና ባህርዳር የክልል ርእሰ መዲናነታቸውን በማስረከብ በቀጥታ በፌደራል መንግስቱ አንደሚተዳደሩ ታውቋል፡፡ የሚኒስትሮች ም/ቤት ለውይይት ባዘጋጀው ሰነድ ላይ እንደገለጸው ከተሞቹ ከርእሰ መዲናነት ወደ ፌዳራል ከተማነት በመሸጋገር ለማእከላዊ መንግስት ግብር ይከፍላሉ፣ በማእከላዊ መንግስት ይተዳደራሉ። በአቶ አዲሱ ለገሰ መሪነት የብአዴን ባለስልጣናት ውይይት አድርገዋል። ባህርዳር የክልል ርእሰ መዲናነቱዋን ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ
ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት 30 በአዲስ አበባና በበርካታ የክልል ከተሞች “የሀይል እርምጃ ለህዝብ መልስ አይሆንም” በሚል ርዕስ የተጠራው የሙስሊሞች ተቃውሞ በደማቅና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ታውቋል። በአዲስ አበባና በበበርካታ የክልል ከተሞች ተቃውሞ ያሰሙት ሙስሊሞች ካስተጋቧቸው መፈክሮች መካከል፦” መብታችንን ለማስከበር የምናደርገው ትግል በሀይል እርምጃ አይጨናገፍም!፣ ለህዝብ የመብት ጥያቄ ሀይል መልስ አይሆንም! የታሰሩት መሪዎቻችን ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ይፈቱ! መንግስት ከሀይማኖታችን ...
Read More »የባለራእይ ወጣቶች የህዝብ ግንኙት ሀላፊ ከእስር ተለቀቀ
ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ግንቦት14፣ 2005 ዓም በደህንነቶች ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ በማእከላዊ እስር ቤት ያለ ፍርድ ሲሰቃይ የነበረው የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ በ5 ሺ ብር ዋስ ከእስር መፈታቱ ታውቋል። ወጣት ብርሀኑ ግንቦት27 ለ3ኛ ጊዜ ሜክሲኮ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፍርድ ቤት ቢቀርብም ፖሊስ ክስ ለመመስረት ባለመቻሉ ቀጠሮ ተጠይቆበት እንደገና ወደ እስር እንዲመለስ ...
Read More »በከረዩና አርጎባ ብሄረሰቦች መካከል የተፈጠረው ችግር ተባብሶ ቀጥሎአል
ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኙት በከረዩ ኦሮሞዎች እና አርጎባ ብሄረሰቦች መካከል በተፈጠረ ግጭት አርጎቦቹ ከ200 በላይ የከረዩ ብሄረሰብ ከብቶችን በመዝረፍ ወስደዋል። ባለፈው ማክሰኞ ግንቦት 27 ፣ 2005 ዓም ደግሞ ከረዩዎች ከ120 በላይ የአርጎቦችን ፍየል በመውሰዳቸው ግጭቱ ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል። የፌደራል ፖሊስ አባላት ግጭቱን እቆታጠራሉ በማለት ጣልቃ ቢገባም በአርጎቦቹ በኩል ተቀባይነት በለማግኘቱ ግጭቱ ሊበርድ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ለቀረቡት ጥያቄዎች በ3 ወራት ውስጥ መልስ እንዲሰጥ አሳሳበ
ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ግንቦት29 ቀን 2005 ዓም ባወጣው መግለጫ መንግስት በፓርቲው ላይ መሰረተቢስ ውንጀላ ከማቅረብ ይልቅ ለቀረቡለት ጥያቄዎች መልስ እንዲሰጥ ጠይቋል። የገዥው ፓርቲ ተወካይ ሰልፉን አስመልክቶ “የሐይማኖት አክራሪነት አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ድብቅ አጀንዳው ገሃድ ወጣ” በማለት የሰጡት አስተያየት መሰረተ ቢስ ፍረጃ መሆኑን የጠቀሰው ፓርቲው ፣ የገዥው ቡድን ...
Read More »የተለያዩ የግል ተቋማት የህክምና ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማቸውን ቀጥለዋል
ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ14 የግል ኮሌጆች የተሰባሰቡ ከ5 ሺ በላይ የሚጠጉ የህክማን ተማሪዎች ሰኔ 27፣ 2005 ዓም የጀመሩትን የትምህርት ማቆም አድማ የቀጠሉ ሲሆን መንግስት ለችግራቸው መፍትሄ የማይሰጥ ከሆነ በአድማው ለመግፋት መወሰናቸውን ተናግረዋል። የትምህርት ሚ/ር ባለስልጣናት ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ መጠየቃቸውን ፣ የተማሪዎች ተወካይም እስከትናንት ድረስ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሲነጋገር ከቆየ በሁዋላ ተማሪዎች ሊያገኙት አለመቻሉን ...
Read More »የ6ኛ ክፍል ተማሪው የመጀመሪያው ታዳጊ የኢሳት አስተያየት ሰጪ ሆነ
ግንቦት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአገራቸው ጉዳይ ላይ ላለፉት 3 አመታት ለኢሳት ስልክ በመደወል አስተያየታቸውን ሲሰጡ የቆዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቢኖሩም የ12 አመቱ የስድስተኛ ክፍሉ የወንድይራድ ተማሪ ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልእክት በማስተላለፍ በኢሳት ታሪክ የመጀመሪያው ታዳጊ አስተየየት ሰጪ ሆኖ ተመዝግቧል። ታዳጊው ግንቦት25 ፣ 2005 ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ የተመለከተውን ተናግሯል። በጣፋጭ ለዛና በአስደናቂ የቋንቋ አጠቃቀም ...
Read More »